Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 13, 2017

አዲስ አበባ መስተዳድር ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ለብክነት ተዳርጓል

Image may contain: skyscraper, sky, outdoor and text

የአዲስ አበባ መስተዳድር ምክር ቤት ሰሞኑን ጉባኤውን አካሂዷል’።የከተማዋ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የ2008 በጀት ዓመት ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ አቅርቧል።
ሪፖርቱ እንዳመለከተውም ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ያለ አግባብ ባክኗል።– 500 ሚሊየን የሚሆን የህዝብና የመንግስት ገንዘብ ደግሞ በወቅቱ መሰብሰብ አልተቻልም።
ከዚህም ሌላ በወቅቱ ያልተወራረደ 200 ሚሊዮን ብር፣ ለማን እንደተከፈለ ማስረጃ የሌለው  257 ሚሊዮን ብር እንዲሁም አዋጅና መመሪያን ሳይከተል ለውሎ አበልና ለደመወዝ የተከፈለ ከ353 ሚሊዮን ብር በላይ በኦዲት መገኘቱን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
ለበጀቱ መባከን የመንግሥት የግዥ መመሪያን ተከትሎ አለመስራት፣ በመመሪያና በህግ ከተፈቀደው በላይ የውሎ አበል ክፍያን መፈፀም የሚሉት በምክንያትነት ተቀምጠዋል፡፡
ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የከተማ አስተዳደሩ ዋና ኦዲተር ወይዘሮ ፅጌወይን ካሣ፤ ብክነትና ምዝበራ በፈፀሙ አካላት ላይ ከፀረ ሙስና እና ከፖሊስ ጋር በመተባበር እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ዶክተር ታቦር ገ/መድህን በበኩላቸው፤ የኦዲት ግኝት ያለባቸው ተቋማት ተለይተው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ለም/ቤቱ አባላት ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ መሥሪያ ቤቶች ያለው የግዥ መመሪያን ተከትሎ ያለመስራት ችግርና ሙስና መፍትሄ ያልተገኘላቸው ችግሮች መሆናቸው በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱ ይታዋሳል።ዘገባውን ያገኘንው ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ነው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials