Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, July 19, 2017

የነጋሶ ጊዳዳ ጠማማ የታሪክና የፖለቲካ መነፅር ሲፈተሽ | ቬሮኒካ መላኩ


«ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ» ይላሉ አበው ነገሮች በፈርጅ በፈርጅ መቀመጥ እንዳለባቸው ሲያስገነዝቡ። ጠጅ በብርሌ ሲጠጣ ውበት እንደሚኖረው ሁሉ ነገርም በምሳሌ ሲሆን፤ ግልፅና ቀላል ይሆናል። የአበውን አባባል መሰረት በማድረግ የዛሬውን ፅሁፌን በምሳሌ ልጀምረው ።

ግሪክ አቴንስ መሀል ከተማ ነው ። አንድ ቀን ፈላስፋው ሶቅራጥስ ህዝቡ በተሰበሰበበት ሰንጠቆ ያልፋል ።ብዙ ህዝብም በከፍተኛ ድምፅ ” ሶቅራጥስ ?!ሶቅራጥስ ?! ሶቅራጥስ? ! ” እያለ ይጮሃል ።
አንድ ሥለ ፈላስፋው ሶቅራጥስ ዝና በጆሮዋ የሰማችና መልኩን አይታው የማታውቅ ሴት ቀረበችውና ፦

” ሶቅራጥሥ ማለት አንተ ነህ ? እንደዚህ መልከ ጥፉ አስቀያሚ ነህ ለካ ?” አለችው ።

ሶቅራጥሥም ወደ ሴቲቱ ዘወር አለና ፦ ” በጠማማ መንፅር ሥላየሽኝ እንጅ በትክክለኛው አይንሽ ብታይኝ ይሄን ያክል አስቀያሚ አይደለሁም ። ” ብሎ መለሰላት።

ዛሬ ስለ ድሮው “ነጋሲ ግደይ ” ስለዛሬው ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አስገራሚ የአዲስ አድማስ ቃለምልልስ ልጫጭር ተነሳሁ ።የዚህን ሀተታ ፅሁፍ በሶቅራጥስና በሴቷ መካከል በተደረገ የጠማማ መንፅር ዲያሎግ መጀመሬ ነጋሶ ጊዳዳ የገደገዱት የታሪክ መነፅር የኢትዮጵያን ታሪክ አንሻፎና አጣሞ ሲያስመለክታቸው ስላነበብኩኝ ነው ።

ለዚህ ፅሁፍ መነሻ ምክንያቱ ዛሬ ትንሽ ሰአታት ቀደም ብሎ አንድ ወዳጄ ነጋሶ ጊዳዳ አስገራሚ ቃለምልልስ ያደረጉበትን የአዲስአድማስ ጋዜጣ ፅሁፍ በመልክት መቀበያ ሳጥኔ አቀበለኝ ። ፅሁፉን ገና ከጅምሩ ማንበብ ስጀምር ግለሰቡ የደነቀሩት ጠማማ መነፅር ታሪክን እንደት እንዳንሻፈፈባቸው እየታዘብኩ አንብቤ ጨረስኩት ። ይሄን አስገራሚ ቃለምልልስ ስጨርስ ነጋሶ ጊዳዳ ታሪክም ፖለቲካም ሳይገባቸው ወይም በክህደት ወደማይቀረው አለም ሊሄዱ ይሆን ወይ በማለት ማሰብ ጀመርኩኝ ።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በዚህ ቃለምልልስ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በታሪክና በፖለቲካ ላይ ቶርቸር ፈፅመዋል። ታሪክን ገለባብጠው አቅርበዋል ። ምሁራዊ ስነምግባር ከሚፈቅደው ውጭ የታሪክ ነውር ፈፅመዋል ።

በአዲስ አድማሱ ጋዜጣ ላይ ያለው የዶክተሩ ቃለምልልስ ሙሉ በሙሉ በሀሰትና በእንቶ ፈንቶ የተሞላ ቢሆንም ለዚች ፅሁፍ ለመፃፍ ምክንያት የሆነኝ አንድ ከፖለቲካ አንፃር ሌላ አንድ ደሞ ከታሪክ አንፃር የተናገሩት ሸፍጥ የተሞላበት ንግግር ነው ። እነዚህም:

1~ <<ህውሓት በህገ መንግሥቱ አርቃቂ ኮሚሽን ተወካይ አልነበረውም” የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የአዲስ አድማሱ ጋዜጠኛ ” በመካከለኛው ኢትዮጵያ የነበረው የህዝቦች ታሪክ ምን ይመስላል?>> …ብሎ ሲጠይቃቸው:
2~ ” እኔ ልናገረው የምችለው ከአፄ አምደፅዮን ጀምሮ ያሉትን በተለይ ከአለቃ ታዬ መፅሐፍ ያነበብኩትን ነገር ነው፡፡ >> በማለት የመለሱት የኢትዮጵያን ታሪክ በውሸት ትርክት ቁም ስቅሉን ያሳዩበትን መልስ ነው ።
እንደዚህ ታሪክን አጣሞ ለፖለቲካ መሳሪያ ለማድረግ ሰው በዚህ እድሜው ሲንጠራወዝ ” እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ ” የሚያስብል ነው ። በእነዚህ አንኳር የታሪክና የፖለቲካ ሸፍጦች ላይ ትንሽ ዝቅ ብዬ እመለስበታለሁኝ በቅድሚያ ግን ስለዶክተር ነጋሶና የኦሮሞ ልሂቃን ትንሽ ነገር ለማለት ወደድኩኝ

እኔ በግሌ የኦሮሞ ልሂቃንን በተለይም የኦነግ ንክኪ ያለባቸውን የምሁርነት ደረጃ ንቄው ነው የማልፈው። ማንበብና መፃፍ ይችላሉ እንጅ ለአቅመ ምሁር ያልደረሱ የቀለም ሽፍቶች ናቸው።
ሙሁር ማለት ዲግሪ፡ ማስትሬት፡ ዶክትሬት፡ ወይም ሌላ የዘመናዊ ትምህርት ማእረግ ያለው ሰው ብቻ አይደለም። እንዲያውም አባ ባህሬይ ፣ ዘርአያእቆብ (ወርቄ)። እነሶቅራጥስ፡ አርስቶትል፤ ቅድስ አውገስቲን፡ ሩዙዎ፡ ማርክስ፤ አዳም ስሚዝ፡ ሌሎትቹም በታሪክ የታወቁት ፈላስፋዎች በኖሩብት ጊዜ ማስትሬት ወይንም ዶክትሬት የሚባል ነገር አይታወቅም። ከኦሮሞ ልሂቃን በመቶ እጥፍ ዊዝዴምን የታደለ የአገሬ ገበሬ ይልቃል ።

የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የታሪክና የፖለቲካ ሸፍጥ ፣ ክህደትና አላዋቂነት በአዲስአዲማስ ሳነብ ራሳቸው በሌላ ሰው ባፃፉት መፅሀፋቸው ስለራሳቸው የመሰከሩት ነገር ትዝ አለኝ።
ዶክተር ነጋሶ “የነጋሶ ጊዳዳ መንገድ ” በሚለው መፅሀፋቸው “መለስ ዜናዊ 2 +2= 4 መሆኑን የማታውቅ መሀይም ነህ ” ብሎ ሰደበኝ ይላሉ ። በዚሁ መፅሀፋቸው ገፅ 67 ደሞ እንደዚህ ይላሉ…
<< በ1967 ዓም መጀመሪያ ወደ ጀርመን እሄዳለሁ ብዬ ሌንጮ ለታ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲሸኘኝ: _
ሌንጮ ለታ~ << ምን ለመማር ነው የምትሄደው? >> አለኝ ።
ነጋሶ ጊዳዳ ~ << ታሪክ> > አልኩት
ሌንጮ ለታ << አንተ ሄደህ ታሪክ ተማር እኛ እዚህ ሆነን ታሪክ ሰርተን እንጠብቅሃለን ።>> ብሎ አሾፈብኝ ” ይላለ ነጋሶ ጊዳዳ ።
በዚሁ ሰኔ 3 2003, በታተመው “የነጋሶ መንገድ ” መፅሀፍ ፔጅ 251 ላይ
መለስ ዜናዊን ” ኢህአድግ የሚመራበት ሶሻሊዝም መቼ ቀረ? እንደት ታታልለናለህ ? ” ብዬ ስጠይቀው
” የ 1987 ፕሮግራምን አንብቦ አቅጣጫችን ካፒታሊዝም መሆኑን ያልተረዳና ተታለልኩ የሚል ሰው ሁለትና ሁለት አራት መሆኑን መደመር የማይችልና መሀይም ነው ” ብሎ ተሳለቀብኝ ። >> ይሉናል ።

መለስ ዜናዊ ለሎሌነት የሚመለምላቸውን ሰዎች የንቃተ ህሊና ደረጃ የሚያውቅ ሰው በመሆኑ ነጋሶን ” ሁለትና ሁለት ሲደመር አራት መሆኑን አታውቅም በማለቱ ልወቅሰው አልችልም። ቢያንስ በዚህ የአዲስ አዲማስ ቃለምልልስ የመለስ ዜናዊ “መሀይም ነህ ” አባባል ብዙም የተሳሳተ እንዳልነበር መገመት ይቻላል ።

ነጋሶ ጊዳዳ በፖለቲካውም መስክ ባለፉት 25 አመታት ያሳዩት መገለባበጥ ምን ያክል የርእዮተአለም መሳከር ውስጥ እንዳሉ አመላካች ነው ። ነጋሶ ከኦነግ ጀምሮ እስከ የአንድነት ሊቀመንበር ተገለባብጠዋል ። ከኦነግ ወደ ወያኔ፣ ከወያኔ ወደ አንድነት ሲዘለ ምንም አልተደናቀፉም።” ብሏቸዋል ተስፋዬ በአንድ ወቅት ። መርህ ያለው ሰው እንዲህ በቀላሉ ከአንድ ጫፍ ወደ ሌላ ጫፍ መዝለል አይቻለውም። ጨለንቆ ላይ ጉድጓድ አስቆፍረው አፅም እየሰበሰቡ “ነፍጠኛውን” ያወግዘ እንዳልነበር፣ አኖሌ ላይ ስለ “ጡት መቆረጥ” ታሪክ ሲያስተምሩ እንዳልነበር አሁን 180 ዲግሪ ተገልብጦ የአንድነት ሊቀመንበር ሆኑ ። አሁንም ወደ ቆሾሾ ቅርጫት ከተወረወረበት ወጥቶ ወደ ኦነግ ምሽግ ለመግባት እየተንደረደሩ ይመስላል።

በ1967 ላይ ቦሌ አየር ማረፊያ ላይ ሌንጮ ለታ እንደፎከረው ሌንጮም ታሪክ አልሰራም ነጋሶም ታሪክ ተምሮ ታሪክ አልገባውም።
በአለም ታሪክ በታሪክ PHD አለኝ ብሎ ማእረጉ እየተጠራበት ” ያነበብኩት የአለቃ ታዬን አንድ መፅሀፍ ነች “የሚል ሰው ብቸኛው ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ መሆን አለባቸው።

አሁን አጠር አድርጌ ዶክተሩ በአዲስ አዲማስ ላይ “አይኔን ግንባር ያድርገው ” በማለት የካዱትን ሁለት ዋና ጉዳይ እንፈትሸው ።
1~ <<ህውሓት በህገ መንግሥቱ አርቃቂ ኮሚሽን ተወካይ አልነበረውም” ይሄ ነ ግግር ከአንድ አገሪቱነ በአንድ ወቅት በአሻንጉሊትነትም ቢሆን በፕሬዚደንትነት ከመራና ህገመንግስቱን አርቅቄለሁኝ ከሚል ሰው የማይጠበቅ ነጭ ውሸት ነው ። ግን ለዶ/ር ነጋሶ መዋሸት ማለት ተራ ነገር ነውና በአዲስ አዲማስ ጋዜጣ ላይ ተናግረውታል።

እውነታው ሲፈተሽ ግን አሁን ያለው የህውሃት መራሹ መንግስት ህገመንግስት ገና ደርግ ከመውደቁ በፊት ከለንደኑም የሰላም ኮንፈረንስ በፊት በበጋ 1983 አም በሸአቢያ ፣በህውሃትና በኦነግ መካከል ኤሪትራ ውስጥ ተሰነይ የሚባል ቦታ እንደፀደቀ አገር ያወቀው ፀሃይ የሞቀው ሃቅ ሆኖ እያለና የዚህ የተሰነይ ጉባኤ ዶኪመንቱም ከእነቃለጉባኤው በተደጋጋሚ ወጥቶ እያለ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ልክ በ1986/7 እንደተፃፈ እና የህውሃትም ተወካይ እንደሌለ ለመናገር መድፈራቸው ሰውዬው ወይ አርጅተው ነገሮችን ማስታወስ አቅቷቸዋል አልያም መለስ ዜናዊ እንዳለዎት “ሁለት ሲደመር ሁለት አራት መሆኑን የማያውቁ መሀይም” ነዎት ማለት ነው።

2 ~ የአዲስ አድማሱ ጋዜጠኛ ” በመካከለኛው ኢትዮጵያ የነበረው የህዝቦች ታሪክ ምን ይመስላል?>> ብሎ ለጠየቃቸው ጥያቄ ነጋሶ ጊዳዳ
” እኔ ልናገረው የምችለው ከአፄ አምደፅዮን ጀምሮ ያሉትን በተለይ ከአለቃ ታዬ መፅሐፍ ያነበብኩትን ነገር ነው፡፡ >
በማለት ነጋሶ ጊዳዳ ” አይኔን ግንባር ያድርገው ” በማለት የኢትዮጵያን ታሪክ መአከላዊ እንዳሉት የአጋዚ መርማሪዎች በሀሰት ቁልቁል ሰቅለው ይገርፉታል ።

እስኪ የዶክተሩን የታሪክ ቅጥፈት አጠር አድርገን እንፈትሸው ።
የኦሮሞ ልሂቃን እንደ መካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚፈሩት የታሪክ አውድ የለም። ለዚህም ይመስላል የአዲስአበባ ዩንቨርሲቲን የታሪክ ድፓርትመንት ከህውሃት ጋር በመተባበር እንደዘጋ ያደረጉት።

የታሪክ ተመራማሪዎች ለአጠናን እንድያመች የአለምን ታሪክ በሶስት ዘመን ይከፋፍሉታል:
1 ~ የጥንት ዘመን ታሪክ ( Ancient Histroy)
2 ~ የመካከለኛው ዘመን ታሪክ ( Medival Histroy)
3~ የዘመናዊ ዘመን ታሪክ ( Modern period Histroy)የኢትዮጵያም ታሪክ በዚሁ የታሪክ ዘመን የተከፋፈለ ነው ።

በኢትዮጵያ የታሪክ ክፍፍል Ancint Histroy(የጥንት ዘመን ታሪክ) የሚባለው ቅድመ አክሱምና የአክሱም ዘመነ መንግስት እስከ ውድቀቱ ያለውና ከውድቀቱም በኋላ ያለው ዘመን ሲሆን ስለዚህ ዘመን የሚያስረዳ ከሃውልት ላይ ፅሁፎችና የመገበያያ ገንዘቦች ቅሪት በስተቀር በፅሁፍ የተገኘው ማስረጃ ዞስካለስ የተባለው ፀሃፊ የፃፈው “The periplus of Eritrean sea ” የሚባለው መፅሀፍ ብቻ ነው እንደ ቀጥተኛ ማስረጃ የሚቆጠረው ።
ሁለተኛው የታሪክ ዘመን ወይም የኢትዮጵያ የመካከለኛው ዘመን ታሪክ የሚባለው (Medival histroy of Ethiopia) የሚባለው የሚጀምረው በታሪክ ፀሃፊዎች አጠራር ” የሰለሞናዊ ስርዎ መንግስት ወይም የአማሮች መንግስት ” የሚባለው ከ1268 ጀምሮ እስከ አፄ ቴዎድሮስ ዘመን ድረስ ያለው የ700 አመታት የታሪክ ዘመን ነው።
እንደመታደል ሆኖ ይሄኛው የታሪክ ወቅት የሰለሞናዊ ስርወመንግስት ንጉሶች እጅግ የተማሩ የተመራመሩ ስለነበር እጅግ ብዙ የፅሁፍ ማስረጃዎች ፣ ክሮኒክሎች ትተው ያለፉበት ዘመን ስለነበር በዚህ ዘመን ስለነበረው የአገሪቱ የፖለቲካ ፣ማህበራዊ ፣ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚያስረዱ የፅሁፍ መዛግብት ብዙ ናቸው።

ዶክተር ነጋሶ ስለዚህ ዘመን ሲጠየቁ ጭንቅ ጥብብ ሲላቸው ከአንድ በታሪክ ትምህርት ዶክትሬት አለኝ ከሚል ሰው የማይጠበቅ ” እኔ የአነበብኳት አንድ የአለቃ ታዬን መፅሀፍ ነው ” በማለት አስቂኝ መልስ ሰጥተዋል ።
በዚህ ዘመን እኮ የተለያዩ የውጭ አገር ፀሃፍት እንደገለፁት እነ አፄ ዘርአያእቆብ ከመላው አለም ተወዳዳሪ የሌለው ቤተመፅሃፍት እንደነበራቸው ተረጋግጧል ።

ዶክተሩ በዚህም ሳያበቁ አንዲት መፅሃፍ አንብቤለሁኝ ብለው ዝሆን የሚያክል ስህተት ይፈፅማሉ ። ” የአፄ አምደፂዮን ግዛት ከሰሜን ቀይ ባህር ሲሆን በደቡብ በኩል ደሞ ደብረብርሃን ነው ።” በማለት እጅግ አሳፋሪ ክህደት ይፈፅማሉ። የአፄ አምደፂዮን ሚስት እኮ አሁን ደቡብ ክልል ከሚባለው ከሃዲያ የተገኘች ነበረች። አፄ አምደ ፂዮን ግዛቱ በደቡብ ደብረብርሃን ላይ ካቆመ እንደት ከሃዲያ ሚስት ሊኖረው ቻለ ? ዶ/ር ነጋሶ ለዚህ መልስ ይኖራቸው ይሆን? እርግጠኛ ነኝ የላቸውም።

በዚህ ዘመን ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ያለው የኢትዮጵያ ታሪክ ምንድነው ?
ሀቁ ኢትዮጵያና የኦሮሞ ህዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቁት በ1530 አካባቢ ነው። ከዛ በፊት ኢትዮጵያ ኦሮሞ የሚባል ህዝብ አይታም ሰምታም አታውቅም ። ፖርቱጋላዊው አልቫሬዝ በአፄ ልብነድንግል ዘመነ መንግስት መጥቶ ኢትዮጵያ ሲዘዋወርና በመፅሃፉ አሁን ያሉትን ብሄርብሄረሰቦች ሲጠራ ከ500ገፅ በላይ ባለው መፅሃፉ ኦሮሞ ወይም ጋላ የሚል ስም አልጠቀሰም ። ዶ/ር ነጋሶ ለመናገር የሚተናነቃቸው ሀቁ ይሄ ነው።

አንዱ ለኢትዮጵያ ውድቀት ምንጭ የታሪክ አተረጓጎማችን ይመስለኛል:: ታሪክ ለኛ ”ያለፈ ክስተት ” ከሚለው በላይ የተወሳሰበ ትርጉም አለው:: ለራስ እንዲመች አርጎ መተርጎምን ጭምር አካቶ ይዟል:: ሆደ ሰፊውን የኢትዮጲያ ታሪክ ሆደ ጠባብ በማድረግ ዘመኑ ተሳክቶለታል:: በተለይም በኦሮሞና ልሂቃን ይሄ የተለመደ ነው ። ድንቅ ሰዎች ግን ታሪክን የሰውን ተፈጥሮ መገንዘቢያ መስክ ያረጉታል :: በኛ አገር ያለው ጥናት ግን ጤነኛ ነው ለማለት ይከብደኛል:: እንደ ነጋሶ ጊዳዳ አጥንት እየቆጠሩ የሚጽፉና የሚናገሩ እልፍ የታሪክ ኮማኪዎች እየታዘብን ነው።
ዘመንና ሁኔታዎች ቢቀያየሩም ታሪክን እንደፈለጉ መለዋወጥ አይቻልም፡፡ በእርግጥ ታሪክን የምናይበት የፖለቲካ መነፅር ነገሮችን ለዋውጦና አቀያይሮ (አንሸዋሮ) ሊያሳየን ይችል ይሆናል። ያኔ ከታሪኩ ባሻገር ፖለቲካዊ ሸር እና ተንኮል ይኖረዋል።ታሪክን እውነታን የምናይበት መነፅሩ ግን ሁሌም መስተካከል ይኖርበታል ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials