Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, July 14, 2017

በቡሌ ሆራ የኦህዴድ ካድሬዎች ወጣቶችን አደራጅተው “ዘረኝነት የተሞላበት ቅስቀሳ” ሲያካሂዱ መዋላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ


ሐምሌ ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት እሁድ የኦህዴድ ካድሬዎችና የቀበሌው ሊቀመንበር ወጣቶችን አደራጅተው፣ በከተማዋ የሚኖሩ የሌሎች ብሄረሰቦች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጅተው እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በሙስሊሞች እና በአንድ ግለሰብ መካከል የቀብር ቦታን አስመልክቶ የ ድንበር ውዝግብ መነሳቱን የሚገልጹት የአይን ምስክሮች፣ የቀበሌው ሊቀመንበር ካቢኔዎችንና ታጣቂዎችን ሰብስቦ ወደ ቦታው ሲሄድ፣ በአካባቢው ከነበሩ ሙስሊሞች ጋር ተጋጭተዋል። ሊቀመንበሩ የገጠር ወጣቶችን ሰብስቦ በመምጣት፣ በከተማዋ የሚኖሩ የሌሎች ብሄረሰቦች ነዋረዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ የሚጠይቁ መፈክሮችን እንዲያሰሙ አድርጓል።
ምንም እንኳ በተቃውሞው በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም፣ ድርጊቱ ግን በህዝቡ መካከል አለመተማመንንና ግጭትን የሚፈጥር መሆኑን የአይን እማኞች ተናግረዋል።
አምና ተደርጎ በነበረው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ በቡሌሆራ ሁሉም ብሄረሰቦች ገጠርና ከተማ ሳይባል በአንድነት በመነሳታቸው የተበሳጩት ካቤኒዎች፣ ይህንን አንድነት ለማዳከም ሆን ተብሎ የተቀናበረ ሴራ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። በገጠሩ ክፍል የሚኖረው አብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች ሲሆኑ፣ በከተሞች ደግሞ ኦሮሞዎችን ጨምሮ የተለያዩ ብሄረሰቦች ይኖራሉ።
ከንቲባው ከሰኔ 18-20፣ 2009 ዓም በከተማዋ የሚገኙ መታወቂያ የሌላቸውን የሌሎች ብሄረሰቦች ወጣቶችን ሰብስቦ በአፋጣኝ ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ ከነገራቸው በሁዋላ ፣ ከ300-400 የሚሆኑትን እያሰፈረመ አስወጥቷቸዋል። ቡሌ ሆራ ወይም የቀድሞዋ አገረ ማርያም ከተማ ውስጥ ከ1961 ዓም ጀምሮ የተሰሩ ቤቶች ያለምንም ካሳና ተለዋጭ ቦታ በሌሊት ህዝቡን እያስለቀሱ ያፈረሱባቸው ሲሆን፣ ካቢኔዎቹ ቤታቸው የፈረሰባቸውን ሰዎች 01 ቀበሌ ጠርተው “ እናንተ እንግዶች ናችሁ፣ ውጡ፤ በእንግድነታችሁ ተከብራችሁ የምትኖሩ ከሆነ ኑሩ፣ ያለበለዚያ ውጡልን” በማለት ሆን ብለው ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ንግግር መናገራቸውንም ነዋሪዎች ተናግረዋል። አብዛኞቹ የንግድ ሱቆቻቸው የፈረሱባቸው የጉራጌ ተወላጆች ሲሆኑ፣ ሌሎችም ብሄረሰቦች እንዲሁ የኦህዴድ ባለስልጣናት የጥቃት ሰለባ ሆነዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials