--------------------------------------------------------
ስብሃት ከወይን የህወሓት ኣማራር ልሳን ያደረገው ቃለመጠየቅ ክፍል ኣንድ በ7 /11 /2009 ዓ/ም ከፍል ማስተካከያ መልስ ለመስጠት ሞክሬ ነበር ። ዛሬ ደግሞ በ1969 ዓ/ም በህወሓት ተፈጥሮ የነበረ ሕንፍሽፍሽ ( ኣንጃ) እና ሰርጌን የትግርኛ እንደ ከዛ በፊት የነበሩ ወጋሕታና ኖላዊት ጋዜጦች ለማጥፋት ያናጣጠረ ሃሳብ እንዲሁም ሌሎች ማስተካከያ ሃሳብ ለመስጠት እሞክሯለሁ ።
1ኛ ስብሃት ነጋ የ1969 ዓ/ም ቀውስ ኣውራጃዊ ወይ ከባቢያዊ ኣልነበረም ።ያለመሆኑ መራጋገጫ ደግሞ የኣሽዓና የደቡብ ኣውራጃዎች ልዩነት ነው ። የኣካባቢያዊ ጠነሳሶችና ተዋናዮች ደግሞ 1ኛ ሓዱሽ ገዘኸይ ከኣድዋ ነው 2ኛ ተሸመ ጉዶ እንትጮ ነው እንትጮ ደግሞ ኣድዋ ነው ። ያነሱት ጥያቄ ደግሞ በህወሓት ዲሞክራሲ የለም የሚል ነጥብ ነው ። ያነሱት ጥያቄ ደግሞ ተጨባጭነት የለውም ይላል ። በመሆኑ ኣውራጃዊ የሚባል ቀውሲ ኣልነበረም ይላል ስብሀት ።
***- የተከበራችሁ ወገኖች ስብሓት ነጋ የሚተርክልን ያለ ድራማ 42 ኣመት ሙሉ በኣውራጃውነት ምክንያት ህዝብን እየከፋፈለ ከጓዶኞቹ የህወሓት ኣማራር ጋር ሆኖ ቡዙ ወገኖች እየጎዳ የኖረውና ኣውራጃውነት (ከባቢያውነት ) እንደ የማህደር ሞምልያ ነጥብ ተቀሙጦበት ፣ቡዙ ታጋዮች የእንደርታ ፣የራያ የተንቤን ፣የምስራቅ ኣካባቢ የመጡ በስብሃት ኣይን የማይታመኑ ጓዶች ነበሩ ። ኣሁንም በሂወት እነ ጀነራል መስፍን ኣማረ ፣ጀ/ታደሰ ወረደ ፣ ሓጎስ ገሞቹ ፣ ጌታቸው ኣሰፋ ወዘተ ኣሉ ። እነ ገብሩ ኣስራትና ጀ/ ጻድቃንም ለኣካባቢ ኣስተዋጽኦ ተብለ ለሽፋን በተጨማሪም በታጋይ ተቀባይነት ስለነበራቸው በኣይነ ቁራኛ ኖሮዋል ። እነዚህ ለማሳያ እንጅ ቡዙ ጅግና ታጋዮች የማይታመኑ ነበሩ ።በህወሓት ኣማራር ማለቴ ነው ።
ስለዚህ የህወሓት ኣማራር በሙሉ እና የማይናቅ ቁጥር ያላቸው የነስብሃት ታማይኝ ካድሬዎች (ሽንቧሾች) 40 ኣመት በላይ የ1969 የኣካባቢነት (ኣውራጃውነ ) እጨፈጨፉት ነው የኖሩት ። በመሆኑ ስብሃት ነጋ ኣውራጃውት የሚል ቀውስ ኣልነበረም ብሎ ሲነግረን ያየሰራው ጥቁር ታሪክ በወርቅ ተለውሶ ሊጻፍለት ስለፈለገ ነው ።
እነዛ ቀውሲ ፈጣሪዎች ብሎ ያስቀመጣቸው ሓዱሽ ገዘኸይ እስከዛሬ በኣካባቢያዊነት ተነሰቶ ኣያውቅም ። ስብሃትና ሓዱሽ ግን ከከተማ ጀምረው በቤተሰብ ደረጃ ቂምና ግጭት እንደነበራቸው የኣድዋ ልጆች ይነግሩን ነበር ። ሓዱሽ ኣምልጦ ነው እንጅ ይገባት ነበር ።
ተሾመ ጉዶም ያየኣውራጃውነት ቀውስ ተጣርቶ ጉባኤ እንዲደረግ የጉባኤ ኣዛጋጅ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስለነበር ተሸመ ጉዶም በከሚቴ ተመርጦ ስለነበር ፣ነገር ግን ከኮሚው ውስጥ በኣውራጃውነት እየተፎረጁ እንደ እነ ጀነራል መሰፍን ኣማረ በመታሰራቸው ሌሎችም የእንደርታ ።የራያ ፣የተንቤን ፣ የምስራቅ ልጆችና ከሌሎች ኣውራጃዎች ከነሱ ንክክ የነበራቸው ተብለው እየተጠረ ጠሩ በብዛት ይታሰሩ ስለነበሩ በኮሚቴ ውስጥም ቡዙ ስህተቶች ሰላዬ ኣምልጦ ወደርግ ገብቶ ከዛ ኣመሪካ ገባ ። እስከ ኣሁን ወደ ኢትዮጱያ ኣልገባም ምክንያቱም ይፈጸም በነበረ ጸረ ዲሞክራሲ ስለደነገጠ ነው ይመስለኛል ።
የ1969 ዐ/ም ኣውራጃውነት ( ከባቢያውነት ) ለምን ተነሳ ? ምን ኣላማስ ነበረው ?
---------------------------------------------------------
በመሰረቱ ኣውራጃውነት የሚል ስም የሰጡት የህሓ ኣማራር ናቸው እንጅ በዛን ገዜ ይዘዋቸው የተነሱ ጥያቀዎች እጅግ ኣበይት ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎችና ። የሃገር ሉኣሏውነት ይከበር የሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ ። ጥያቄዎች ያነሱም ምንም እንኳን ከመቀሌና ከተቤን ከኣጋሜ የመጡ ከፍተኛ ሙሁራንና ብዝዎቹ ቢሆኑም ከኣድዋ ከኣክሱም ፣ከሽሬም የማይናቅ ቁጥር ያላቸው ነበሩ ። ጥያቂያቸውም የሚከተሉ ነበሩ ።
1ኛ ህውሓት የኣንድብሄር ፓርቲ ነኝ እያለ ለምን የኤርትራ መገንጠል ያምናል ሃገራችንስ ለቡዙ ሽ ኣመታት የቀይባህር ባለቤት የነበረች እንዴት የባህር በር የሚያሳጣት ኣቋም እንይዛለን ??
2ኛ ነጻ ሀገራዊት (ነጻ ሪፓብሊክ ትግራይ ) የሚለው ኣቋም ( ፕሮግራም ) በዮተኛው የታሪክ መስፈርት ነው? 3ኛ በትግራይ የነበረ ከ4ኣመት በላይ ከህወሓት በፊት የነበረ ፓርቲ ግ ግ ሓ ት ( ግንበር ገድሊ ሓርነት ትግራይ ) ኢዲሞክራሲያዊ የሀነ እርምጃ ነው የወሰዳችሁ ማነው ተጠያቂ ? በነፍጥ ከመደብደብ በፊት በውይይት ሊፈታ ኣይችልም ነበርን ? የግግሓት መሪዎችስ ለምን ተረሸኑ ?
4 ከኢህኣፓ ከኢዲዩ ለምን ያለን ግጭት በክብ ጠረቤዛ ውይይት ኣንፈታውም ?
5 የህወሓት ኣማራር በቤተሰብ በጋደኝነት የተሰባሰበነው ።በተጨማሪ በመተዳደሪያ ደንባችን የለለ ያየተመረጠ ማእከላይ ኮሚቴ በስልጣኑ የኣማኣራሩ ወኪል ኣማራር ኣድርጎ የማእከላይ ኮሚቴ ስልጣን መስጠቱ ጸረ ዲሞክራሲ ከመሆኑ በዘለለ እነዚ ወኪሎች ምንም ብቃት የሌላቸው ወኪል ሆነው ቆይተው በሚቀጥለው ጉባኤ እንዲመረጡ ዝግጅት ማለት ነው ። ስለሆነ ይህ ፓርቲ ጸረ ዲሞክራሲ እየሆነ ኣይደለምን ?
6ኛ ያለው ማእከላይ ኮሚቴ ብቃት የለለው በቤተሰበና በጓደኝት የተሳሰረ በመሆኑ በከተማ ሆነው የፓርቲው ኣስካል የነበሩ ቡዙ ቡቁ ሙሁራኖች ስላሉ ጉባኤ ይደረግ ?
7ኛ ኣማራሩ ብቃት ማኸል ያደረገ ከሁሉም የትግራይ ኣስተዋጽኦ ያለው መሆን ኣለበት ?
8ኛ ኣማራሩ የኤርትራ ፓርቲዎች በተለይ የሻብያ ተላላኪ ይሆናል ። ታጋያችን ለሸኣብያ ኣምላኪ እንዲሆን እየተደረገ ነው ለምን ?
9ኛ በህወሓት የህግ ኣማካሪ ለምን ኣይነርም ? የህወሓት ኣማራር ራሱ ከሳሽ ፣ራሱ ፈራጅ ዳኛ ፣ ራሱ ፖሊስ ፣ራሱ እርምጃ ወሳጅ ነው ለምን ?ወዘተ የሚሉ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ያነሱ ነበሩ ።
ጥያቄ ያቀረቡ እነማን ነበሩ ?
---------------------------------------------
ጥያቄ ያነሱ በሞቶ የሚቆጠሩ ቢሆኑም ዋናዋናዎቹ ፣
1ደጉተር ኣበበ ተሰማ ከተንቤን በኣሁኑ ጊዜ ኣመሪካ ኒዮርክ ኣለ ።
2ኛ መምህር ዳዊት ገብሩ ከዓጋመ ሰሔታ ።
3ዕቁባዝጊ በየነ ከኣክሱም ። (ረዘነ በዬነ )
ኪዳነማርያም በላይ (ቀበሮ) ከኣክሱም ።
4 ተስፋይ 08 ( ክፍሊ ህዝብ ) ከኣድዋ
5ኛ ካሳ ለማ ከመቀሌ ።
6ኛ ተኪኤ ካሕሳይ ከመቀሌ ።
7 ኪዳነ ግርማይ ከመቀሌ ።
8ኛ ኣበራ ማንካ ከመቀሌ ።
9 ኛ ከበደገብረመድህን ከዋጅራት ደቡብ ።
10 ሃይለ ገሰሰ ከተንቤን ።
11ኛ ተክለማርያም ተሰፋይ ( ኣወተ ) ። ከተንቤን
12ኛ ሰሎሞን (ሓዬት ) ገብረእግዚኣብሄር ከዓድዋ ወዘተ ።
በ1969 ዓ / ም በህወሓት ተነስቶ የነበረ ቀውስ ወይ ግጭት ስብሓት ነጋ እጅግ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ነው የተፈታ ብሎዋል ። ዋዋ ኣቶ ስብሃት የደደቢት ቀውሲም የተፈታው በዲሞክራሲያዊ ኣገባብ ተፈትዋል ብለህ ውሼት ተናግረሃል ። የ1969ኙም እንደዚሁ በዲሞክራሲ ተፈትቷል ብለሃል ።
በእኔ እምነት የህወሃት መሪዎች ከበቀሉባት 1967 ዓ /ም ጀምረው እስከዛሬ እለት ኣንድቀንም ዲሞክራሲያዊ ባህሪ ይሁን ተፈጥሮ ንሮዋቸው ኣያውቅም ። በመሆኑም በ1969 ዓ / ም እጅግ ቡዙ ሙሁራኖች በግፍ ታስረዋል ፣ተገርፈዋል ፣ ተሰውረዋል ። በተለያዬ ጊዜ ሰብሃት ራስ ድርጅትን እንዲኖር ታሳቢ በማድረግ የገደልናቸው ተጋዮች ነበሩ ብለሃል ።ስለዚህ ዲሞክራሲያዊ የግጭት ኣፋታት እንከተል ነበርን የሚለው ውሼትህ ነው ።
የህወሓት መሪዎች በ1977 በነ ኣረጋዊ በርሀ ፣ግደይ ዘርኣጽዬን ፣ ተክሉ ሃዋዝ ሌሎች በተከታዮቻቸው የተወሰደው እርምጃ ፣
በ1981 ፤82 ዓ /ም የነበረ ብጅምላ የታጋዮች ማሰር መሰወር ፣ መሰቃየት ፤
በ1984 ፤85 ዓ/ም ከ1969 ዓ/ ም ተመሳሳይ 16 ወሳኝ ሃገራዊ ጥያቄዎች ያነሱ
32 000 ታጋዮች ታስረው ተገርፈው ከአንድ ኣመት እስከ ሰወስት ኣመት ተኩል ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ህጋዊ ባልሆኑ እሱር ቤቶች ያለከሳሽ ታስረው ያለይቅርታ ተጥለው ቀርተዋል ፣ በእሱር ቤቶ ሞተዋል ታመው ወጥተው በዬሄዱበት መቶዋል ፣ ወደ ትወልድ ቃያቸው ሄደው ከቤተሰቦቻቸው እንዳይ ኖሩ ታግለው ባመጡት ድምጽ ወያኔ እነ ሰብሃት ነጋና ሌሎች ሽንባሾችና ልቁባሾች ፣ፎርሞታሪዎች ባገር ቤት ያለው ህዝብ ወላጆቻቸው ጭምር እንዳያስጠጉዋቸው ኣድርገዋል ።
ታድያ ስበሃት ነጋ ሊቀመንበር ሁነህ በምትመራው ፓርት እጅግ ቡዙ ወገኖች የተበሉበት ዲሞክራሲያዊ ነበርን ማለትክ ግዜ ተረስቷል እና ኣሁን ያለ ትውልድ ኣያውቀውም ብለህ መዋሸት እጅጉን ኣሳፋሪ ነው ። በኣሁኑ ጊዜ ያለ ወጣት ሙሁር እኮ ኣንድቀን እንደሚዘምታችሁ ከወዲሁ በጫ ካርድ እየሰጣችሁ ነው ።
ስብሃት ነጋ የገለበጠው (የወረረው ) የ1977
ዓ ም የነግደይና በሪሁ ወይ ኣረጋዊ በርሀ የተባረሩበት ዲምክራሲያዊ ኣሰራር ተከትለን ፈትተናል ብለሃለ ።
----------------------------------------------------------
ኣቶ ግደይ ለነበረው ሁኔታ የሚያውቁ ከኣስርሸ በላይ ታጋይ የነበሩ ኣሁንም በመንግስት ስራ ያሉ ኣሉ ። ሁሉም ነገር ያውቃሉ ።ብቻህን ያለህ ይመስልሃል እንጅ ለምስክርነት የሚበቁ ኣሉ ። ግደይ ዘርኣጽዬን ሃብታም ኣርሶ ኣደርና ብሄራዊ ብርጅዋ ጠላት ነው ብሎ ተረትቶ ወደህዝብ ወርጆ ኣስተምራለሁ ብሎ ገንዘብ ጠይቆ ሰጥተነዋል ብለሃል ።
ሃቁ ግን ኣሁንም ታሪኩ ሰርቀኸዋል ።ግደይ የነበረው ኣቋም ብሄራዊ ብርጅዋ ሀበታም ገበሬ ወዳጅ ነው በኣሁኑ ጊዜ የኣልባኒያ መስመር የእስታሊን መሰመር ተከትለን መሄድ ኣይጠቅመንም ብሎ ነው በሃሳብ የተለዬ ።ሁለቱ ኣማራሮች ከነልዩነታቸው ጉባኤተኛ ወደ ማእከላይ ከምቴ ሞርጧቸዋል ። ብዛሃኑ ዲሞክራቲክ ስለነበሩ ። እናንተ ግን በጉበኤ የተመረጡ የፓርቲ ቁጥጥር ኮሚቴ ሳይ ዳኛቸው በጉባኤ የጸደቀው የፓርቲ መተዳደርያ ህገ ደንብ ጥሳችሁ ወደ ተራ ታጋይነት ጥላችሁ ከታጋዮችና ህዝብ በማይገናኙበት ለነሱ በማይመጥን ስራ የቁም እስሮኞች ሆነው ነው የኖሩ ። ለግደይ ገንዘብ ሰጥተን ለቅስቀሳ ተሰማርቶ ነበር የሚለውም በመሬት ያልነበረ ሀቅ ነው ። በሪሁም ኣንተ በምትለው ደረጃ የወረደ ኣልነበረም ። ኣንተና መለስ ፣ኣባይ ጸሃዬ ተወለ ወለማርያም ፣ኣለም ሰገድ ገብረኣምላክ ሌሎች ሎሌዎቻችሁ ተበድናቹ የሰራችሁ ውዲት ነው ።
ለዚሁ ሃቅ ግን ግደይና ኣረጋዊ በኣውሮፓ ስላሉ መልስ ቢሰጡት መልካም ነው ።
ስብሓት ነጋ ንሰርጌን ትግርኛ መጽሄትም እሱ ለሚደጉማት ውራይና መጽሄት ስለተወዳደረቻት ፣ሰርጌን ብነጻ ሳንባዋ ስለምትተነፍስ ለህወሓት ኣማራር ሰለደፈረችና ስላወደሰች ሊያጠፏት ነው መሰለኝ ?
-------------------------------------------------------
ስብሃት ነጋ ከኣጀንዳ የማትገናኝ እንደ ለመደው በኣውራጃውነት (ከባባውነት ) ሽፋን በማድረግ ስም ማጥፋት ኣገርሽቶባቸው ነው መሰለኝ ።
ሰው ሲጨልመው ሳለ ኣውራጃውነት እንደ ሽፋን ተጠቅሞ አንደ ሰርጌን የምትባል የግል መጽሄት ፍጹም የፓለቲካ ብልሽት ነው በማለት የመጽሄቷ ኣዛጋጆች በኣውራጃውነት (ከባባዊነት) ፈርጆዋቸዋል ።
ይህ ውንጀላ ስብሃት ነጋ ኣሁን ያሳየው ባህሪ ኣይደለም ለ42 ኣመት ሙሉ እየሰራበት የመጣ ነው ። ከመጀመሪያ ጀምሮ እስከ ኣሁን በህወሓት ውስጥ የተፈጠሩ ቀውሶች ሰም እየሰጠ መጥፎ እርምጃ ያስወሰደባቸው ስብሃት ነጋ ነው ።
የህወሓት መሪዎች ሊወስዱት እና ሊወስኑት የሚፈልጉ ወይ የሚደርሱት ድምዳሜ ስብሃት ነጋ እንደዋዛ ዋዛ በጋዜጣ ፣መጽሄት ፣በሬድዮ ፣ተለብዥን ፣ በስብሰባ ቀስ ኣድርጎ ከኣጀንዳው የማይጣበቅ ጣል ኣድርጎ ነው የሚያልፈው ።
ኣሁንም ሰርጌን መጽሄት የህወሓት ኣማራሮች ለሰርጌን ትግርኛ መጽሄት ሊቦላት ስለፈለጉ በስብሃት ነጋ የተለመደ ቋንቋ በኣንዲት ቃል ጣል በማድረግ ማስጠንቀቅያ ሰጥቷቷል ። በመሆኑ የሰርጌን መጽሄት ኣዛጋጆች የተባለ ይባል በርቱ እንዳትንበርከኩ ።
ትምክህቲ እና ጠባብነት የመረተሙሁር ።
ኣስተሳሰብ ነው ።
--------------------------------------------------------
የህወሓት መሪዎች ስብሃት ነጋ ኣሁን ሽልኮበት ብሄራዊ ብርጅዋ ጠላታችን ነው ብሎ የግደይና የኣረጋዊ ኣቋም ቢሰርቅ ሃቁ ግን ሸልቦታል።
የህወሓት መሪዎች ከጅምሩ ኣነደኛ ጠላታችን ኢንፐራሊዝም ፣ካፒታሊዝም ፣ ያገር ውስጥ ብሄራዊ ብርጅዋ ፣ ሃብታም ኣርሶ ኣደር ፤ ከፍተኛ ሙሁር ማለት ከዲፐሎማ በላይ ያለው በኣንደኛ ጠላትነት ፈርጆት የመጣ ። በሁለተኛነት ደግሞ መካከለኛ ሙሁር ፣መካከለኛ ኣርሶ ኣደር ፤ መካከለኛ ብርጅዋ ሲሆን ፣ይህ ደግሞ ኣንድ ግዜ የሚከዳ የማይታመን ሃይል ነው ብሎ ነው የመጣ ።
ኣስተማማኝ ወዳጆች የሚባሉ ፣ ድሃ ገበሬ ፣ ታችኛው ሙሁር ድሃ ነጋዴ ፣ ላብ ኣደር ነበር በንስብሃት ኣስተሳሰብ ።
ከላይ በተጠቀሰው የመደብ ኣሰላለፍ በ42 ኣመት ውስጥ በተለይ በ17 ኣመቱ የትጥቅ ትግል ጊዜ በጠላትነት እና በተዋላዋይነት የተቀመጡ ወገኖች እጅግ ቡዙ ወገኖች ታስረዋል ፣ተገድለዋል።
ኣሁንም ስብሃት ነጋ እያረጋገጠልን ያለው የጠባብነት እና ትምክህት የተባላሸ ኣገር የሚበታትን ያለው ሙሁር ነው ይህ ደግሞ የኢትዮጱዪ ህዝብ ጠላት ነው እያለን ነው ።
በእኔ እምነት ግን ጠባብነትና ትምክህት ያባላሸው የህወሓት ኢህኣደግ ኣማራር ነው ። ከህወሓት ኣማራር ውስጥም በጠባብነት ስብሃት ነጋ ግንባር ቀደምትነት ይሰለፋል ። ስብሃት ነጋ ትግራይን ለመገንጠል ከሚጠነስስ ዘመናት ኣድርጓል ። ይህ ደግሞ ከሽንቧሾችና ሉቁባሾች የወረሰው ኣስተሳሰብ ነው ።
እኔ የሚያሳዝነኝ ግን የሃገራችን ሙሁራን በተለይ የትግራይ ሙሁራን ባለሃብቶች ለነዚህ ተገዥ ሆነው መኖራቸው ነው ። ስብሃት እንበላቸው ኣለን ሲላቸው ማንቀላፈታቸው ነው ።
እባካቹ ለራሳችሁና ሳይማር ላስተማራችሁ ህዝብ ስሩ ።
ከኣስገደ ገብረስላሴ ፣
8 /11 / 2009
No comments:
Post a Comment