Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, July 23, 2017

‹‹በሴትነቴና በማንነቴ ላይ ተመስርተው ስድብና ማንቋሸሽ ፈጽመውብኛል›› ቀለብ ስዩም



ስም፡- ቀለብ ስዩም
ዕድሜ፡- 28
አድራሻ፡- አማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ምዕራብ አርማጭሆ
አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡- በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት፣ ቃሊቲ እስር ቤት
ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በሽብር ወንጀል ተጠርጥረሻል ተብዬ ነው የታሰርሁት
በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- አርበኞች ግንቦት ሰባት ከተባለ የሽብር ድርጅት አመራሮች ጋር ግንኙነት በማድረግ ድርጅቱን ለመቀላቀል ልትጓዝ ነበር በሚል የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 7(1) በመተላለፍ በማናቸውም መልኩ በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ መሳተፍ የሚል ክስ ነው የፌደራል አቃቤ ህግ ያቀረበብኝ፡፡
በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል:
1. ለእስር ሲዳርጉኝ የፍ/ቤት ማሰሪያ ትዕዛዝ አላሳዩኝም፡፡
2. ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ ካሰሩኝ በኋላ ለቤተሰቤ ያለሁበትን ሁኔታ ለማሳወቅ ተከልክያለሁ፡፡
3. ቤተሰቦቼ መታሰሬን ከሰሙም በኋላ ለአንድ ወር ያህል በፍጹም እንዳላገኛቸው/እንዳይጠይቁኝ ተደርጌያለሁ፡፡
4. በመርማሪዎቼ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡
5. በሴትነቴና በማንነቴ ላይ ተመስርተው ስድብና ማንቋሸሽ ፈጽመውብኛል፡፡
6. በግዳጅ ቃል እንድሰጥ አድርገውኛል፡፡
7. በይፋ ክስ ተመስርቶብኝ ቃሊቲ እስር ቤት ካዛወሩኝ በኋላም የጠያቂ ገደብ ተጥሎብኛል፡፡ እኔን መጠየቅ የፈለገ ሰው ሁሉ እንዲጠይቀኝ አይፈቀድም፤ ቀድሞ ስማቸው በእስር ቤት አስተዳደሩ ከተመዘገቡት ውጭ አይፈቀድም፡፡
8. የመጠየቂያ ሰዓት ገደብም ተጥሎብኛል፡፡ እኔ መጠየቅ የሚፈቀድልኝ ከ6፡00-6፡30 ለሰላሳ ደቂቃዎች ብቻ ነው፡፡
ለእስር የተዳረግሁት ልክ የዛሬ ሁለት አመት ነው፡፡ ለስራ ፍለጋ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ በመጣሁበት ወቅት ነው ተይዤ የታሰርሁት፡፡ ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት ደካማ እናቴንና የስምንት ወር ህጻን ልጄን ትቼ ነበር፡፡ ምክንያቴ ደግሞ እራሴንም ቤተሰቦቼንም ለመርዳት የሚያስችል ስራ አገኝ ይሆናል በሚል ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ባላሰብሁት መንገድ ታሰርሁ፡፡ አሁን ላይ በተከሰስሁበት ክስ የአራት አመት እስር ቅጣት ተፈርዶብኝ ቃሊቲ እገኛለሁ፡፡
ትምህርት እስከማስተርስ ዲግሪ ተምሬያለሁ፤ ማስተርሴን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ነው የሰራሁት፡፡ ጎንደር አርማጭሆ በመንግስት መስሪያ ቤት የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ውስጥ እሰራ ነበር፡፡ ሆኖም በፖለቲካ አመለካከት ልዩነቴ ምክንያት ተባርሬያለሁ፡፡ የአንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ ፓርቲ አባል ነበርሁ፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials