Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, July 19, 2017

ነቀምቴ በልዩ ኃይል ተወራለች * ሕዝባዊ እምቢተኝነት ጀምሯል * ከሆሮ ጉድሩ ወደ ከተማዋ ለሚገቡ ሾፌሮች ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

በነቀምት ራሳቸውን በሕቡእ ያደራጁት ወጣቶች (ቄሮዎች) መንግስት በሕዝቡ ላይ የጣለውን አግባብ ያልሆነ ግብር በመቃወም ሕዝቡን ማስተባበር መጀመራቸውና ሕዝባዊ እምቢተኝነቱም ንግድ ቤቶችን በመዝጋት እንዳስጀመሩት ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ጠቆሙ::
ከሆሮ ጉድሩ ወደ ነቀምቴ ለመግባት ለሚያስቡ አሽከርካሪዎች የሥራ ማቆሙ አካል የማይሆኑ ከሆነ እርምጃ እንደሚወስደባቸው ያሳሰቡት ቄሮዎቹ ለአደጋ ከመጋለጣቸው አስቀድሞ ሊያስቡበት እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል::
ነቀምቴ በዛሬው ዕለት በልዩ ኃይል ፖሊሶች ከተማዋ ተወሮ መዋሉና በውጥረት ውስጥ እንዳለች ለማወቅ ችለናል::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ በአምቦ ዛሬም ውጥረቱ እንዳየለ ነው:: ከአምቦ መረጃዎች እንደደረሱን እናቀርባለን::

No comments:

Post a Comment

wanted officials