Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, July 23, 2017

ከቡራዩ አካባቢ የመጣ አበረታች ዜና


በትላንትናው እለተ አርብ መንግስት የአካባቢው ነጋዴዎች ላይ ከጫነው ግብር ጋር ተያይዞ ከባድ ተቋውሞ ገጥሞታል:: ምግብ ቤት ሱቅ መዝናኛ ስፍራ ሆቴሎች እና ጫት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸውን ሁላችንም በአይናችን በአይናችን አይተናል::
በተመሳሳይ መልክ ተቋውሞው እየተስፋፋ መሆኑ ታውቋል:: ይህን ተቋውሞ ለየት የሚያደርገው የብሄር ልዮነትን ሳይኖር ሁሉም ለሃቁ የሚያደርገው የመብት ትግሉ መመሳሰሉ ነው:: የሚከተለውም መልእክትም በቄሮ የሚመራ ልዩ ሀይል አንድ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ቢሮ አካባቢ ትእዛዝ በመጣስ አጋዚዮችን በማገልገል ላይ የሚገኝ ሆቴል ላይ በሚቀጥለው ሰአት የተቀናጀ እና ጥንቃቄ የተሞላበት ቅጣት እንዲወሰድበት የተላለፈ የማስጠንቀቂያ መልእክት ነው:: በመላው ቡራዩ ውስጥ የሚኖሩ ቄሮዎች ለአንዳንድ ሱቆች መጠንቀቅ እንደሚገባቸው የወንድማዊነት ጥሪያቸውንም አስተላልፈዋል::
በተጨማሪም የ ከታ ደሚቱ የቡራዩ ፀረፅዮን የካርቶን ፈብሪካ ቁልቁለት ላይ ለሚገኙ ነጋዴዎች እና ለመሳሰሉት ላደረጋቹት አኩሪ ተግባር ምስጋቸውን እና የበርቱ መልእክት አስተላልፈዋል:: በተመሳሳይ መልክ ሳኑሲ አካባቢ ከታ አቀበት ኢትዮ ሸክላ ማራያም ፊት ለፊት የተባበሩት ነዳጅ ማደያ እና ሱቆች እና መንገድ ውስጥ ለምትገኙ ጫት ቤቶች በሙሉ እንይ ሌሎችም ትግሉን እንዲቀላቀሉ አስቸኳይ ጥሪ በቁቤ ትውልድ ቀርቦላቸዋል:: ካል ህነ ግን ቄሮዎች ለሚወስዱባችሁ የቅጣት እርምጃ ራሳችሁን እንድታዘጋጁ ብለው ያስተላለፉት ወንድማዊ መልእክት እንድትሰሙ የተላለፈ ጥሪ ነው::
ከቡራዩ ከተማ እና አከባቢዋ ቄሮዎች (ወጣቶች)

No comments:

Post a Comment

wanted officials