Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 11, 2017

ሰሜን ሸዋና ወሎ ህዝባዊ አመፅ ተቀስቅሷል – “የቺፑድ ፋብሪካ ተቃጥሏል”






ሙሉነህ ዮንሃስ

ጥቅምት 28 2010

ሰሜን ሸዋ ምንጃር ላይ ትናንትና የጀመረው ህዝባዊ አመፅ ዛሬ ተባብሶ ቀጥሏል። ለሁለት ሳምንት መናብራት መጥፋትን ምክንያት አድርጎ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመፅ ዛሬ ወደ ሃይል እርምጃ እንደተሸጋገረ የደረሰን መረካ ያመለክታል። ዛሬ የተኩስ እሩምታ አለ። ትናንት በተደረገው ተቃውሞ አንድ የመንግስት ባለስልጣን መሞቱ እየተነገረ ነው። ሰሜን ሸዋ የወያኔ አገዛዝ “ገዥው የሽዋ አማራ” የሚል ፍረጃ ለጥፎባት ከፍተኛ በደል ሲያደርስባት የቆየች ምድር ናት።

ከስፍራው ሁኔታውን ያሳወቁን የአይን እማኞች የህዝቡ ቁጣና እልህ ለዘመናት የታመቀውን ብሶቱን እያሳየ ነው።

በተያያዘ ዜናም የግብር ክምር የተጫነባቸው የወሎ ነጋዴዎች ሱቆቻውቸን ዘግተው የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል። የህዝብን ጥያቄ መፍታት የማይችለው ወያኔም ሱቆችን እያሸገ ነው።

በጎንደርና በጎጃም ተቀጣጥሎ የከረመው ህዝባዊ አመፅ ሰሞኑን ወደ ሰሜን ሸዋና ወደ ወሎ ተዛምቶ በአማራ ክልል ሙሉ ለሙሉ ህዝባዊ አመፁ ተዛምቷል።

በሌላ በኩል ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው “በደብረ ብርሃን ከተማ ተገድለው የሚገኙ ሰዎች አሳሳቢ ሆኗል” ሲል ዘግቧል::

ሙሉቀን “በዚህ ዓመት ብቻ በከተማው የተለያዪ አካባቢዎች ከ10 በላይ ተገድለው የተገኙ ሰዎች አሳሳቢ መሆኑን የሚገልጹት ምንጮች ዛሬም ማምሻው የደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት የላብራቶሪ ተማሪ ጠፍታ ከሰነበተች በኋላ ተገድላ መገኘቷ ተሰምቷል፡፡ ተገድላለች የተባለችውን ተማሪ በተመለከተ ከዩንቨርሲቲውና ከገለልተኛ አካል ለማጣራት አልቻልንም፡፡” ሲል ያስረዳል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ የአማራ ክልል የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በፌስቡክ ገጻቸው የሚከተለውን አስፍረዋል::

“ዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በክልላችን ሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአረርቲ ከተማ አስተዳደር መብራት ለ15 ቀናት በመቋረጡ ጥያቄ ለማቅረብ ሰልፍ ተደርጎ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተነሳ ግርግር ሁኔታው መልኩን ቀይሮ በቅርቡ ስራ ጀምሮ የነበረ ከአረርቲ ከተማ ከ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ቺፑድ ፋብሪካ የቃጠሎ ጉዳት ደርሶበታል። በሂደቱም ሁለት ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። ጉዳት የደረሰባቸው በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው ነው።”

አቶ ንጉሱ ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል:-
“አሁን በደረሰኝ መረጃ መሰረት በምንጃር ወረዳ አረርቲ አካባቢ በነበረው ሁከት በአካባቢው በመገንባት ላይ የሚገኘውን ኢንዱስትሪ ፓርክም ጀነሬተሮች ለማቃጠል ሙከራ የተደረገ ሲሆን ይህ ህብረተሰቡ በመከላከሉ ምንም ጉዳት አልደረሰም። የችፑድ ፋብሪካው ግን ከመኪናዎቹ ጭምር ጉዳት ደርሶበታል። ሁለቱ ጉዳት የደረሰባቸው ወጣቶች በአረርቲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛሉ። የፀጥታ መዋቅሩ ሁከቱን በቁጥጥር ስር አውሎ ወጣቶቹን በማወያየት ላይ ነው።”

No comments:

Post a Comment

wanted officials