Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 18, 2017

ጦሩ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙጋቤ በአደባባይ ታዩ

ጦሩ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙጋቤ በአደባባይ ታዩ
ሙጋቤ ሰማያዊ እና ቢጫ ቀለም ያለው ቆብ አድርገው ይታያሉ
የሃገሪቱ ጦር ከሶስት ቀናት በፊት ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ሮበርት ሙጋቤ በአደባባይ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የታዩት።
በዚምባብዌ መዲና በሆነችው ሃራሬ በተማሪዎች የምረቃት ፕሮግራም ላይ ለህዝብ የታዩት።
ላለፉት ጥቂት ቀናት ሙጋቤ በቁም እስር ላይ መቆየታቸው ይታወቃል።
አርብ ጠዋት የዚምባብዌው ሄራልድ ጋዜጣ ሙጋቤ የጦሩን መሪ ጀነራል ኮንስታኒቲኖ ቺዌንጋንና የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ(ሳድክ) ተወካዮች ጋር በቤተመንግሥት ሲነጋግሩ የሚያሳዩ ፎቶዎችን አውጥቶ ነበር።
ሙጋቤ ከሥልጣን አልወርድም እያሉ ነው
ሬውተርስ የዓይን እማኝን ጠቅሶ እንደዘገበው ሙጋቤ በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ካደረጉ በኋላ ከተመራቂዎች ሞቅ ያለ ድጋፍ አጊንተዋል።
ሙጋቤ ለቤት ውስጥ እስር ከዳረጋቸው የሀገሪቱ ጦር መሪ ጋር ሲጨባበጡና ሲወያዩ ቢታዩም እስከቀጣዩ ምርጫ ሥልጣኔን አልለቅም ማለታቸውን የመረጃ ምንጮች እየገለጹ ነው።
የሃገሪቱ ጦር ከሶስት ቀናት በፊት ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ሙጋቤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ታዩ።
BBC.COM

No comments:

Post a Comment

wanted officials