Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, November 3, 2017

ገጣሚ፣ መምህር፣ ጋዜጠኛ እና የፍልስፍና ሊቅ ሠሎሞን ዴሬሳ አረፈ፡፡





‹‹በአንድ በኩል ስታስበው ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀምጦ እኔ የትግራይ ሰው ነኝ፣ እኔ አማራ ነኝ ብሎ አፍ ሞልቶ መናገሩም አለማወቅ ይመስለኛል፡፡ በሴት አያቶቻችን በራፍ ላይ ማን እንዳለፈ ስንቶቻችን ነን የምናውቀው? የኔን ጥሩ ኦሮሞነት እግዚአብሔርና የሴት አያቶቼ ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ የሁሉንም እንዲሁ፡፡››
…....................……ይህ ንግግር በአንድ ወቅት የተናገረው ሰለሞን ዴሬሳ ነው፡፡
ጥቅምት 23/2010 ዓ.ም. በሰማንያ ዓመት ዕድሜው ያረፈው ጋሽ ሠሎሞን ዴሬሳ የሚኔሶታ ነዋሪ የነበረ ሲሆን ከሥራው ገበታ በ ሕመም እስከተለየ ድረስ በሚኔሶታ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ሆኖ ሲሠራ ቆይቷል። ታናሽ ወንድሙ የቀድሞው የአዲስ አበባ ባለአደራ አምባሳደር ብርሃነ ዴሬሳ ለቪኦኤ እንደገለፀው ጋሽ ሠሎሞን ዴሬሳ ከሰባት ወራት ህመም በኋላ ያረፈው በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ነው።
ሠሎሞን ዴሬሳ የተወለደው ከእናቱ ከወይዘሮ የሺመቤት ዴሬሳና ከአባቱ ከአቶ ዴሬሳ ላንኪ በቀድሞው ወለጋ ጠቅላይ ግዛት ከጊምቢ ስምንት ኪሎ ሜትር ያህል ወጣ ብላ በምትገኝ ጩታ ቀበሌ ነበር።
ፈጣሪ ነፍሱን በገነት ያሳርፍ!Image may contain: 1 person, sitting

No comments:

Post a Comment

wanted officials