Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, October 22, 2018

በውጭና በሃገር ውስጥ የሚገኙ ጳጳሳት ከ25 አመታት በኋላ በጋራ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ጀመሩ

    በውጭና በሃገር ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ከሩብ ክፍለ ዘመን በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋራ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ጀመሩ። በየአመቱ በጥቅምትና በግንቦት ወር የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከ25 አመታት በላይ ለሁለት ተከፍሎ ሲካሄድ ቆይቷል።

አዲስ አበባ ላይ የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቤተክርስቲያኒቱ ጉዳይ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሃገራዊ ሁኔታ ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር ግንኙነቷን ለማጠናከርም ኮሚሽን እንደሚቋቋም ተመልክቷል።
ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ለሁለት ተከፍላ የቆየችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ የተካሄደውን ለውጥ ተከትሎ በወረደው እርቅ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ ከ25 አመታት በኋላ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል።
በፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስና በፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ በጋራ እየተመራ ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ይጠናቀቃል ተብሎም ይጠበቃል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials