Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, October 11, 2018

አቶ ሌንጮ ለታ ወጣቱ በባዶ እጁ ታንክ ፊት በሚጋፈጥበት ጊዜ የኦነግ ሰራዊት የት ነበር አሉ

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ሊቀመነበር አቶ ሌንጮ ለታ ኦነግ ትጥቅ አልፈታም ማለቱ ተገቢ አይደለም አሉ።
ወጣቱ በባዶ እጁ ታንክ ፊት በሚጋፈጥበት ጊዜ የኦነግ ሰራዊት የት ነበር ሲሉ አቶ ሌንጮ ለታ በሀገር ውስጥ ከሚሰራጨው አሀዱ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል።
ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ከፈለግን በሀገር ውስጥ መኖር ያለበት ሰራዊት የመንግስት ብቻ መሆን አለበት ያሉት አቶ ሌንጮ ለታ የኦነጉ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የተናገሩት ግራ የሚያጋባ ነው ብለዋል።
የኦነግ ሰራዊት የት ነበር? በማን ነው የሚታዘዘው? የሚሉ ጥያቄዎችን ያነሱት አቶ ሌንጮ ለታ ሰራዊቱ አለ ከተባለም ትጥቅ አልፈታም ማለት አይችልም ሲሉ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል።
ኦነግ ትጥቅ አልፈታም የሚለው ማንን ለመውጋት ነው ሲሉ ይጠይቃሉ አቶ ሌንጮ ለታ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials