Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, October 14, 2018

በቡራዩ ነጋዴዎች የንብረት ካሳ አለማግኘታቸውንና ስራም አለመጀመራቸውን ገለጹ


በቡራዩ ነጋዴዎች የንብረት ካሳ አለማግኘታቸውንና ስራም አለመጀመራቸውን ገለጹ
ባለሆቴሎቹ ለኢሳት ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ለደረሰው የንብረት ውድመት የከተማው መስተዳድር የወደመውን ንብረት ምዝገባ እና ግምት ቢያካሂድም እስካሁን ወደስራ እንዲመለሱ ለማድረግ ይህ ነው የሚባል ተግባር አላከናወነም፡፡
የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሃላፊ በበኩላቸው የወደመውን ንብረት የመመዝገቡ ስራ በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል፡፡
ለተፈናቃዮቹ ማቋቋሚያም ሆነ ለደረሰው የንብረት ውድመት ካሳ ተብሎ የተሰበሰበው ገንዘብ ለታለመለት አላማ እንዲውል ከሚመለከተው አካል ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials