ዜጎች በኩልነት የሚኖሩባትና ዲሞክራሲያዊትና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚታገለውን አርበኞች ግንቦት 7 ለመደገፍ የወጣው የናዝሬት ህዝብ ነው። በኦሮሚያ ክልል ህዝቡ በነቂስ አደባባይ በመውጣት የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮችን በደመቀ ሁኔታ ተቀብሏል።
በአዳማ ስታዲየም በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች በተገኙበት በተደረገው በዚሁ አቀባበል ላይ የንቅናቄው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተገኝተዋል:: ፕሮፌስሩ በስታዲየሙ ባደረጉት ንግግርም "የብሄር ፓለቲካ የነጻነትና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ዋስትና ቢሆን ኖሮ የሶማሌ ክልል ተወላጆች በገዛ 'ወገናቸው' አብዲ ኢሌ ፍዳቸውን ባልቆጠሩ ነበር። ከእኔው ' ዘር ' ብሄር የሆነ ዕብድ ይጨቁነኝ ብሎ ፓለቲካ አይሰራም ፤ ዜጎች በመላ ሀገሪቱ በነጻነት የሚኖሩበት ስርዐት መገንባት ምርጫ አይደለም ግዴታ ነው።" ብለዋል:: የአዳማ ከተማ ህዝብ ዘረኝነትን በጽኑ የሚያወግዙ መፈክሮችን አንግቦ ኢትዮጵያዊነትን በማወደስ ላይ ነበሩ።
No comments:
Post a Comment