በነጭ ሳር ፓርክ ታጣቂዎች ተጣቂዎች ቢያንስ 4 ሰዎችን ገደሉ
በአርባምንጭ ከተማ ዙሪያ በሚገኘው የነጭ ሳር ፓርክ ውስጥ የመሸጉ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ 4 ሰዎች ሲገደሉ 3 ሰዎች ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ጥቃቱን የኦነግ ታጣቂዎች እንዳደረሱት ይናገራሉ
ኢሳት የአካባቢውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካለትም።
በሌላ በኩል የነጭ ሳር ፓርክ ብሄራዊ ጽ/ቤት ለደቡብ እና ኦሮምያ ክልሎች በጻፈው ደብዳቤ “ በፓርኩ ምስራቃዊ ክፍል በፓርኩ ውስጥ የሚኖሩ የጉጂ ማህበረሰብ በተፈጥሮ ሃብቱ ላይ እያደረሱ ያለው ውድመት ከፓርኩ ጽ/ቤት አቅም በላይ ከመሆኑም ባሻገር በጥበቃና ቁጥጥር ሰራተኞቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጫና ከአቅም በላይ በመሆኑ እንዲሁም ከፓርኩ ጥበቃና ቁጥጥር ሰራተኞች በተሻለ መልኩ በሚገባ የጦር መሳሪያ የታጠቁ አካላት በመሆናቸው ችግሩን አስከፊ አድርጎታል” ብሎአል።
የሚመለከታቸው አካላት በአመት እስከ 4 ሺ የውጭና አገር ውስጥ ጎብኝዎችን የሚያስተናግደውን ፓርክ እንዲታደጉት የፓርኩ ጽ/ቤት ጥሪ አቅርቧል።

No comments:
Post a Comment