Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, December 1, 2018

“በ21 አክሱም ጺዮን በ22 ደብረጺዮን!”


ከደብረ ጺዮን ወደ አክሱም ጺዮን | ክንፉ አሰፋ
መቀሌ ለደበቀቻቸው “ጀግኖች” ባለ ውለታ ናቸው። ከዚህም በላይ ይገባቸዋል የሚሉ አሉ። እምነት ለነሱ ኢምንት ነው። ሃይማኖት ደግሞ ፖለቲካ። ልብ ያለው ፈጣሪን ያስባል። ይሉኝታ ያለው አምላኩን ይፈራል። ህሊና ያለው ደግሞ የእግዚአብሄርን ስም ይጠራል። ይህ ሁሉ የሌለው ግን በባዶነቱ ዝም ብሎ ይቁነጠነጣል። ይህ አዲስ አይደለም። ራስ እንጂ ጭንቅላት ከሌለው ሰው ተቃራኒው ቢፈጸን ነበር የሚደንቀው።
አንዱ ሰው ጓደኛውን ይጠይቀዋል። “እስኪ ለአፍታ አስበው በጫቃ መሃል ውስጥ ነህ። አንበሳ ሊበላህ አሰፍስፎ ይጠብቅሃል። ምን ታደርጋለህ?”
ልጁ መለሰ። “ማሰብ አቆማለሁ!”
እያወራን ያለነው በአንበሶች ተከብበው ማሰብ ስላቆሙ ሰዎች ነው።
ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካዔል የቤተ ክርስትያንዋን ካባ ይልበሱ። ባለ ልዩ ማዕረጉን አክሊልም ይድፉ። ይህ የሆነው ከንሰሃ በፊት ይሁን ወይንስ ከንስሃ በኋላ ግልጽ አልሆነልንም። ከካይሮ እስከ ቡሳን፤ ከባንኮክ እስከ ዱባይ፣ ከናይሮቢ እስከ ቬጋስ በጉዞ ላይ የፈጸሙዋቸው የዝሙት ነውሮች ለዚህ ሽልማት ሊያበቁ እንደማይችሉ ቤተ ክርስትያን ሳታውቅ ቀርታ አይደለም። ከቶውንም ዝሙት እና ሌብነት ለተክሊል የሚያበቁ ጀብዶች እንደማይሆኑ ግልጽ ነው።
አክሱም ጺዮን በኢትዮጵያ ክርስትና ታሪክ ውስጥ ትልቁን ስፍራ ትይዛለች። ሰለሞናዊው ስርወ መንግስት ንግስና የሚጸናውም በዚያ ስፍራ ነው። የታሪክ መዛግብት እንደሚነግሩን፤ ሁለት መቶ ሃያ አምስቱ የሰለሞናዊ ነገስታት ከንግስናቸው በኋላ ወደ አክሱም ጺዮን መሄድ እና ስልጣናቸውን ማጽናት ግድ ነው።
አቡነ ማትያስ ስለ ዶ/ር ደብረጺዮን ንግስና የነገሩን ባይኖርም፤ በዚያ ታሪካዊ ቀን ይህንን የማድረጋቸው ምክንያት ግልጽ ይመስላል። ንጉሰ ነገስት ህወሃት ዘማሌሊት።
ነብሳቸውን ይማርና አቡነ ጳውሎስ ቢዮንሴን ባስተናገዱ ግዜ
“በ7 ስላሴ፣
በ8 ቢዮንሴ
በዘጠኝ እኔ ራሴ” እያለ ሕዝብ ሲቀልድባቸው ነበር።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዶ/ር ደብረጺዮንን በህዳር ጺዮን ማርያም ሲያነግሱ፤
“በ21 አክሱም ጺዮን
በ22 ደብረጺዮን!” ተብሏል።
ችግሩ ከአልባሳቱ ላይ አይደለም። ስብዕናው የወረደ፤ በሙስና እና በዝሙት የሚከሰስን አንድ የፖለቲካ ድርጅት መሪ፤ በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ በዚህች ታሪካዊ ስፍራ ላይ ያላግባብ ከፍታ ላይ ማስቀመጡ የማድረጉ እንደምታ ነው። ቤተ-ክርስትያንዋን ለማርከስ ከመሞከር በላይ ይህ ጉዳይ ትልቅ ትርጉም አለው።
ጠባብ የክልል አስተሳሰብ ይዘው መጡ። ሰላማዊ ሕዝብ ላይ እንደ ማሽላ ዘሩት። በሲስተሙ ሰው ሲባላ እነሱ ግን ኖሩበት። በመጨረሻ የለኮሱት እሳት ራሳቸውኑ መብላት ሲጀምር፤ ዳግም መቀሌ ላይ ተሰበሰቡ። ገዳዩም፣ ዘራፊውም፣ ቄሱም፣ ጳጳሱም፣ …. መክረው የመጀመርያ የሆነውን ንግስና እውን አደረጉት።
እርግጥ ነው ነፍጥ አንጠንጥሎ እንደፈለጉ የማድረጉ ሰዓት አሁን ረፍሮበታል። በዳዩ፣ ከሳሹ፤ ምስክሩ እና ዳኛው አንድ የነበረበት ዘመን እንደ ዋዛ አልፏል። የፖለቲካ ቁማራቸውን በቤተ-እምነትን ውስጥ ይዞ ብቅ ማለት ግን ወንድ ልጅን አስገድዶ ከመድፈር የላቀ ወንጀል መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት የለብንም።
አይቶ የማይመለከት፣ ረግጦ የማይቆምና ይዞ የማይጨበጥ የዥዋዥዌ ፖለቲካውን ባናቱ ላይ ተሸክሞ ሲቁነጠነጥ የነበረው ሰውዬ፤ ዛሬ ወደ አክሱም ጺዮን ብቅ ብሏል። አካሄዱ ረጋ ያለ የኤሊ ጉዞ ቢሆን ኖሮ ከጀርባ ያዘለውን ጉድ በጥርጣሬ የሚያየው አልነበረም። ሩጫው የብርሃን ፍጥነት ሆነና ሕዝበ አዳምን “ጉድ” ማሰኘቱ አልቀረም።
አሁን ለታ ቤተ-ክርስትያንዋ ዶ/ር አብይ እና ባለቤታቸውን ጠርታ የክብር ካባ አልብሳ ሸልማቸው ነበር። አግባብ ያለው ሽልማት። በሁለቱ ሲኖዶስ እርቅ ላይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነበር የተሸለሙት።
ዶር ደብረ ጺዮን የግፈኞች እና ሌቦችን እየተንከባከቡ በመቀሌ ዋሻ ከማቆየት ውጭ። ተጠርጣሪን አሳልፌ አልሰጥም ከማለት ውጭ የትኛውን ጽድቅ ስራ ሰርተው ለዚህ ክብር እንደበቁ ግልጽ አይደለም።
የማሌሊት መጥምቀ-ዮሃንስ፣ የአልባንያ ኮምኒዝም ሃዋርያ፣ የሂትለሩ ጎብልስ ደቀ መዝሙር ናቸው ደብረጺዮን። በርዕሰ አድባራት ፅዮን ማርያም በር ላይ እንኳ ለመድረስ ይዳፈራሉ ብሎ ማሰብ አይቻልም። ጽዮን ማርያም ታሪካዊ ናት። ኢትዮጵያ ክርስትናን ለመጀመሪያ ይዞ በገባው በአቡነ ሰላማ ዘመን የተገነባች ጥንታዊ ቤ/ክርስቲያን። አስርቱን የፈጣሪ ትእዛዛት የያዘው የሙሴ ጽላት በሚገኝባት።
በሃይማኖት ሸፋን የፖለቲካ ጨዋታ ለመጫወት መሞከሩ አንድ ነገር ነው። ገና መዳህ ሳይጀምር በማርክሲዝም ሌኒንዝም ርዕዮት ደደቢት በረሃ ለተጠመቀ ሰው የተክሊል ቆብ መጫን፤ ከፖለቲካ ውጭ ሌላ ትርጉም አይሰጠውም።
ኮምፒዩተሩ ሃክ ተደርጎ የሰውየው መረጃ መንገድ ላይ ተሰጥቶ ባየን ግዜ አማትበናል። አሁን ግን ሃክ የተደረገው ኮፒዩተር ሳይሆን የዘውድ አክሊል የጫኑለት አባቶች ጭንቅላት ነው። መቼም አንጎላቸው ሃክ ተደርጎ ካልሆነ በስተቀር በጽድቅ እና በኩነኔ፤ በሃላል እና በሃራም መሃል ያለው ልዩነት አይጠፋቸውም። አልያም የዘር ካርድ ከልመዘዙ በአንድ ፖለቲከኛ ክንድ ብቻ አይዘወሩም።
በመጀመርያ ለዝሙቱ እና ለሌብነቱ ሃፍረት መሸፈኛ መንገድ ሳይቀይስ የህዝብን አንጀት መብላት መሞከር በራሱ ጅልነት ነው።
ብዙ የፖለቲካ ዚግዛግ አይተን ይሆናል። የደብረ ጺዮኑ አይነት ግን የተለየ ነው። በፖለቲካ ግራና ቀኝ እርግጫ አስገርሞን ሳያበቃ ቤተ ጸሎት ዘው ብለዋል። ሁለት ባላ ትከል። አንዱ ሲነቀል ካንዱ ተንጠልጠል አይነት ነው። ንጋት ላይ ሌባን ስለማጥፋት ሲነግሩን ቆይተው ምሽት ላይ “የምን ሌባ” ይሉናል። በዚህ ተደንቀን ሳንጨርስ ደግሞ የሌቦችን ቀን መቀሌ ያከብሩልናል። በአድዋና በአዲግራት ላይም ይደግሙልናል። ግራ ገብ ነገር!
አበው ሲተርቱ ሳይቸግር ጤፍ ብድር ይላሉ። ሰዎቹ መቀሌ ላይ በሸሸገቻቸው ግፈኞች ሳብያ ትልቅ አጣብቂኝ ውስጥ ናት። ችግሩ በጫጫታና በትእይንተ ሕዝብ አይፈታም። የጦርነት ከበሮ መደለቅም መፍትሄ አይሆንም።
ደብረጺዮን በዚህ አቋማሜ የት ድረስ ልሄድ እችላለሁ የሚለው ጥያቄ ሃሳብ ሊገባቸው ይችላል። የሚሄድበትን ለማያውቅ፤ ሁሉም መንገድ ይወስደዋል። ግራ ገብ ተጓዥ ወደ ጥፋትም ይሁን ወደ ልማት፣ ሽቅብ ይሁን ቁልቁለት ዝም ብሎ ይሄዳል። ምክንያቱም አይን የለውም። ልብም የለውም። ሕዝቡን እሱ ወደሚጓዝበት ይመራዋል። ወደየት እና የት ድረስ እንደሚሄድ ግን የሚይውቅ የለም።
የቱንም ያህል ይወዛወዝ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጋር መጻፈጡ ግን ወጋ ከማስከፈል ውጭ ትርፍ አያመጣለትም። የመኒ-ቴክ (ይቅርታ ሜቴክ) ሃላፊን ለማስመለጥ ሞክረው አልተሰካም። ሌላዎቹን እስከ መቼ መደበቅ እንደሚችሉ ይታያል።
እንደ ናይጄሪያው የሽብርተኛ ቡድን መሪ ቦኮ ሀራም በረሃ ካልገባ በቀር ሁሉም የፍትህን ደጃፍ ይረግጣታል። መተናነቁ ያለው ከመቶ ሚሊየን ከሕዝብ ጋር መሆኑን ለአፍታም ባይዘነጉት መልከም ነው። ጆ ቢደን እንዳሉት “ሌብነትን መዋጋት መልካም መስተዳደር ማምጣት አይደለም። ራስን መከላከል እንጂ”
ካልተያዙ በስተቀር ሌብነት ሥራ ነው የሚለው የሙዚቃ ሪትም አሁን ሲያከትም፤ እነሱ በተራቸው ሰልፍ ተማሩልን። ቅኝቱን ሲለውጡት ደግሞ የዶክተር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤልን ንግስና አበሰሩን።
እስቲ ይሁና። የጀርመኑ ፈላስፋ ፍሬድሪክ ኒቼ እንዲህ ይላል። “ቢያስሩን እና ሊገድሉን ካልቻሉ የበለጠ ጠንካራ ያደርጉናል።”
ሌላው ጎርፍ ነው። ይሄዳል
Image may contain: 3 people

No comments:

Post a Comment

wanted officials