Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, December 6, 2018

በቀድሞው የስለላ እና የጥርነፋ አሰራር የተዋቀረውን የኢትዮጵያን ኤምባሲዎች ሰራተኞች ላይ ቁጥር ቅነሳ እንዲካሄድ በጀርመን ኢትዮጵያውያን መግለጫ አወጡ



“በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን እና የኢትዮጵያን ኤምባሲዎች ግንኙነት በሚመለከት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠው መግለጫ በተግባር እንዲተረጎም እንጠይቃለን አብረንም ለለውጥ እንተጋለን።” ሲሉ በጀርመን በርሊን እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  መግለጫ አወጡ::
መግለጫው እንደሚከተለው ይቀርባል::
በዋናነት የፍራንክፈርቱ ቆንስላ ጽ/ቤት እስከ ቅርብ ጊዜ ለውጡ እስከመጣበት ወቅት ድረስ ታዋቂ ተግባር ኢትዮጵያውያኖች ለዲሞክራሲ እና ለሰባዊ መብት መከበር በሚያደርጉዋቸው ሰላማዊ ሰልፎች ዝግጅቶች ስብሰባዎች ላይ የተሳታፊዎችን አስተሳሰባቸውን በነጻ የገለጹትን ለመብት እና ለህግ የበላይነት የታገሉትን በተለያየ አጋጣሚ ሃሳባቸውን በግል በነጻ የሚገልጹትን በወኪሎቻቸው አማካኝነት በመስማት መረጃ በመሰብሰብ ድምጾች በመቅዳት ፎተግራፎች በማስነሳት ቪዲዮ በማስቀረጽ ኢትዮጵያውያንን በጥቁር መዝገብ ላይ በማስፈር ወደ አገር ቤት የአገር ውስጥ እና ውጭ ደህንነት መስሪያ ቤት ማስተላለፍ ነበር። 
ብዙዎች የደረሰባቸው የስነልቡና ጭነት እና የመብት ጥሰት ብናስታውስ ፍርሃት እንዲሰፍን አገራቸውን እንዳያዩ ቤተሰብ እንዳይገናኙ ዘመድ እንዳይቀብሩ ማስፈራሪያዎች ለዘመድ ለጓደኞቻቸው ለቤተሰቦቻቸው እንዲደርስ የተደረጉ እና የተሞከረባቸው ጥቂት አይደሉም።
የፍራንክፈርቱ ቆንስላ ጽ/ቤት በዚህ ተግባር ተሳታፊ የነበረ ሲሆን ከለውጡ በኋላ በይቅርታው ጉዞ በዝምታ ቢታለፍም ስነልቦናዊ ለውጥ ያልታየበት አሰራሩን ቀጥሎበት በፍራንክፈርት ጠ/ሚኒ አብይ አህመድ ከኢትዮጵያውያኖች ጋር በአደረጉት ስብሰባ ዝግጅት ላይ ተሳታፊዎችን ቁጥር የቀነሰ ያጒላላ እና የተሰራ ዝብርቅርቅ እስከ አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ ዋናው ተጠያቂው የፍራንክፈርቱ ቆንስላ ጽ/ቤት ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ ሃላፊነት አልወሰደም። ሙሉ በሙሉም ይቀርታ እስከ አሁን ድረስ በግልጽ አልጠየቀም።
ከዚህ በታች እንደሚከተለው ከ1-5 ያሉ ጥያቄዎችን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እናቀርባለን።
(1).በጠ/ሚ አብይ አህመድ የፍራንክፈርት ስብሰባ ላይ በተሳታፊዎች ላይ ለደረሰው መጉላላት እና የዝግጅቱ መተረማመስ የፍራንክፈርቱ ጀነራል ካውንስለር ጽ/ቤት ሙሉ ሃላፊነት እንዲወስድ በግልጽ በዋናነት ሙሉ ይቅርታ እንዲጠይቅ እንጠይቃለን።
(2.)የፍራንክፈርቱን ጀነራል ካውንስለር ጽ/ቤት የሃገር ሃብት ብክነት አስራር  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲመረምር እንዲሁም ለዝግጅቱ የወጣው ጠቅላላ ወጭ በፍራንክፈርቱ ጀነራል ካውንስለር ጽ/ቤት በዝርዝር በግልጽ ባስቸኳይ ይፋ እንዲደረግ እንጠይቃለን።
(3.)የሃገር ሃብት አውዳሚ የሆነው በቀድሞው የስለላ እና የጥርነፋ አሰራር የተዋቀረውን በርሊንም ኤምባሲ ሆነ በፍራንክፈርት ቆንጽላ ጽ/ቤት ሰራተኞች ላይ ቁጥር ቅነሳ እንዲካሄድ እንጠይቃለን።
(4.) በበርሊንም ኤምባሲ ሆነ በፍራንክፈርት ቆንጽላ ጽ/ቤት እውቅና በሌለው የጎንዮሽ ግንኙነት ያለ ሃቅ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት እንዲቀር እና የድብቅ ጥሪ ሆነ ወይንም ማንኛውም የድብቅ ማደራጀት እንዳይኖር እንጠይቃለን።
(5.)በቅርቡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሹመት የተሰጣቸው ዳይሬክተር ጄኔራሎች እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች መካከል እኚሁ የፍራንክፈርት ቆንስል ጀነራል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ አገሮችና የአውሮፓ ህብረት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ሆነው መሾማቸው አጠያያቂ ነው እንላለንል። የፍራንክፈርት ቆንስል ጀነራሉ ለሃገር እና ለወገን በዚህ ቦታ የሚሰሩትን ዲፕሎማሲ ካሳለፍነው ልምድ በከፍተኛ ጥረጣሬ እንመለከተዋለን። ለተቃና የውጭ ግንኙነት በቦታው በማሳደድ ዲፕሎማሲ የልተካፈሉ ሙያተኞች እንዲመደቡበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን እንጠይቃለን።
የበርሊን እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን

No comments:

Post a Comment

wanted officials