Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, December 29, 2018

ኢትዮጵያና ሱዳን በሶስት ሳምንት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ተገናኙ



የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በተቃውሞ እየታመሰች ባለችው ሱዳን ዛሬ ቆይታ አድርገዋል፡፡ በካርቱም ቆይታቸውም ከሱዳኑ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚነስትር ዶ/ር አል ድሪር ሞሃመድ ጋር መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ገልጿል።
ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በውይይቱ ወቅት ሱዳን በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጣት አገር ናት መሆኗን ጠቁመው ሁለቱ አገሮች ለሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች ፍላጎት መሳካት ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩና የሁለቱ አገሮች ህዝቦች መፃኢ ዕድልም ተመሳሳይ መሆኑን ገልፀዋል።
ጨምረውም ‹‹በሁለቱ አገሮች መካከል በከፍተኛ ደረጃ የተደረጉ የፖለቲካ ምክክሮች ሁለቱ ወገኖች ከፊት ለፊታቸው ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና ለህዝባቸው ጥቅሞች በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ማሳያ ነው›› ብለዋል። የሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዶ/ር አል ድሪር ሙሀመድ በበኩላቸው ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው አዲስ አመራር ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ለውጥ ሱዳን ታደንቃለች›› ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም በሱዳን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
እንዲሁም ባለፈው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሱዳን ጉብኝት ማድረጋቸው የሁለቱን አገሮች ወንድማማች ህዝቦች ፍላጎት ለማሳካት በጋራና በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡
ሕወሓት ሱዳንን በሰላማዊ ሰልፍ ጭምር አጋሩ መሆኗን ከገለጸ በኋላ በሁለት ሳምንት ውስጥ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ሱዳንን ሲጎበኝ ይህ ሁለተኛው መሆኑ ነው:: አልበሽር አዲስ አበባ መጥተዋል”” ከሳምንት በፊት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለሁለት ቀናት ሱዳን ሄደው የነበru ሲሆን ዛሬ ደግሞ ዶ/ር ወርቅነህ እዛ ናቸው:::
ኢትዮጵያና ሱዳን በሶስት ሳምንት ውስጥ ሶስት ጊዜ ተገናኝተዋል ማለት ነው::

No comments:

Post a Comment

wanted officials