የአርበኞች ግንቦት 7 ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እዝ መቋቋሙን ስለማሳወቅ!
በአሁኑ ሳዓት የጀመርነው የነፃነት ትግል ፍሬዎችን እያፈራ ማየት ጀምረናል፡፡
የምንታገለው አደገኛ ከሆነው ጠላታችን ህወሐትና እንዲሁም ለሆዳቸው ካደሩ ከሀዲና ባንዳዎች ጋር በመሆኑ የትግል ስልቱ እንደየ አካባቢው ይለያያል ማለትም ተለዋዋጭ ይሆናል፡፡
በመሆኑም ላለፋት 8 ወራት አግ7 የሰሜን ዕዝ በርካታ ስራዎችን በከተማ እና በገጠር ሲሰራ እደቆየ እና አሁንም በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት ጠላት በሰሜን ዕዝ ላይ ያለ የሌለ ኃይሉን በመጠቀም ትግሉን ለማኮላሸት እየሰራ ይገኛል፡፡
ባሐፈው ግምገማችን ስርዓቱ (ጠላት) አግ7 የሰሜን ዕዝ የሚለውን በከፍተኛ ደረጃ እደሚሰጋው እና በልዩ አወቃቀር ለማጥፋት ከፍተኛ እቅስቃሴ ሲያደርግ ተስቶውላል፡፡
ስለሆነም አሁን ባለው 2 ተጨባጭ ነጥቦች ማለትም 1፡ የትግሉ እንቅስቃሴ ወደ መሀል መድረሱ 2፡ የሰሜን ዕዝ ብቻውን መቀጠሉ በመሀል እና በአዲስ አበባ ዙሬያ ያሉ አባሎቻችን ሌላ ዕዝ በተጨማሪ እዲቋቋም መጠየቃቸው ታውቃል፡፡
በመሆኑም የትግሉ ደረጃ ከፍ ማለቱና መሀል እና ዙሪያው ያለው እንቅስቃሴ በጥሩ ደረጃ መገኘቱን ገምግመናል በዚህ መነሻ ከዛሬ ጥቅምት 10 /2010 ዓ/ም ጀምሮ "አርበኞች ግንቦት 7 ማዐከላዊ ኢትዮጵያ ዕዝ" በይፋ ተመስርቷል፡፡
ለጊዜው ከልምድና ከትስስር አኳያ እንዲሁም የመሀሉን ትግል እየመሩና እየሰሩ ያሉት የአግ7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ታጋዬችና የድርጅታችን ከፍተኛ አመራሮች በመሆናቸው አመራሩ ለጊዜው በዚህ ይቀጥልና በቀጣይ ጠንካራ አመራሮች ይመደባሉ፡፡
የአግ 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ!
No comments:
Post a Comment