https://andemta.com/
አሞራ … የዳዊት አሞራ” (ግጥም)

“አሞራ … የዳዊት አሞራ”
በዣን ተኵላ
.
[1400 ዓ.ም]
.






.
.
በዘመናችን አማርኛ …
(ትርጉምና አሰናኝ)
በዕውቀቱ ሥዩም
.
.
“አሞራ የዳዊት አሞራ
ተከተለኝ ከኋላ፤
.
ላቅርብልህ ሥጋ ብላ
ላጠጣህ ወይ ደም መራራ
ተከተለኝ እኔ ልምራ፤
.
እየመተርሁ በካራ
እየወጋሁ በጦር ጣምራ።
.
ብንበላብህ አደራ
በገላችን ጦር ይዘራ፤
ክንፍ አውጥተን ብንሸሽም
ቀስትህ ትውጋን ተወርውራ።
.
ምንም ሆድ ቢብሰን እኛ አንበላም መሐላ
ገላችን ይምሰል እንጂ የፈጠጋር አምባራ
አፋችን ይምሰል እንጂ ባልቴት ምትሞቀው እንሶስላ
ጣታችንም ይምሰል ጭራ የጎረሰ ደም አበላ፤
.
ጭፍሮች ነነ የዣን ተኵላ
እኛስ አንበላም መሐላ!”
.
.
.
[በ1400ዎቹ አማርኛ በድጋሚ]
.
“አሞራ የዳዊት አሞራ
ተኸተለኝ በኋላ፤
.
ሥጋ አበላኽ ሐበላ (ከበላ)
የደም አጠጣኽ ነተራ (መራራ)
ተኸተለኝ በኋላ፤
.
ወግዕቼ በቃራ (በካራ)
ሰኽቼ በጸመራ። (በጣምራ)
.
እኛስ ብንበልዓኽ መሐላ
ለጾር ይስጠን ለወርወራ፤ (ውርወራ)
የከንፍ ብናደርግ ጽላ
ለቀስት ይስጠን ለቀፈራ። (ለወጠራ)
.
ምን ከበአሰን ንበልአኹ መሐላ (እንበላለን)
ገላችን ከመሰል የፈጠጋር እምብላ (አምባር)
አፈችን ከመሰል በዓልቴት የገባች እንሶስላ
ፀዓታችን የመሰል በደም የዘራ ጭራ (ጣታችን)
.
ስማችን የዣን ተኵላ
አንበልዓም መሐላ። (አንበላም)
.
No comments:
Post a Comment