Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, October 7, 2017

የኦሮሞ ፖለቲከኞች ለሕዝብና አገር ደንታ የላቸውም፡፡ሰርጸ ደስታ

ነ! – ሰርጸ ደስታ



ዛሬ ምንም መጻፍ አልፈለኩም፡፡ “አክራሪ የኦሮሞ ብሄርተኞች አማራን እና አዲስ አበባ በሚመለከት ያላቸው አመለካክት” የሚል ጽሁፍ ሳንብ በውስጡ ፍጹም ሆን ተብሎ ሕዝብን ግራ ለማጋባት የተቀመረ ጽሁፍ እንደሆን አየሁት፡፡ አሁን እየቸገርን ያለው አክራሪ ኦሮሞ ሳይሆን ከዚህ በከፋ የአክራሪ አማራዎች ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ እርግጥ ነው ሁለቱም የወያኔ ተቀጣሪዎች እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ አሁን ላይ ከመቼውም በበለጠ አክራሪ ኦሮሞዎች እየተዳከሙ እንደሆነ እናቃለን፡፡ ችግሩ አሁንም ኢትዮጵያዊ ኦሮሞዎችና ከአክራሪነት የተፈወሱት ራሳቸውን ገልጠው እየተናገሩ አደለም፡፡ ስለዚህ አሁንም በዝቶ የሚሰማው የአክራሪዎቹ ድምጽ እንሆነ እናቃለን፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ለሕዝብና አገር ደንታ የላቸውም፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ብትበታተን ሁሉም አገር አለው አሮሞ ግን አገር የሌለው ተደርጓል፡፡ ይህ ማንም ሊያስተውል አልቻለም፡፡ ኦሮሞ በሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲጠላ ዘመቻ ነው የተከፈተበት፤፡ ይህን እወቁ፡፡ በራሱ ግን ምንም ውል የሌለውና በሌሎች ፍቃድ የሚያድር ሆኗል፡፡ ለዛም ነው ነገሮች ከዚህ በላይ ከማለፋቸው በፊት ኦሮሞ ራሱን ለማዳን ኢትዮጵያ ታስፈልገዋለች፡፡ አማሮቹ ብዙ ነገር ወጥነው ሊሆን ይችላል ኦሮሞ ግን ያለ እቅድ አንደተባለውም አክራሪዎችና ሆድ አደሮች በሥሙ የሚነግዱበት የኔ የሚለው ምንም አይነት ዋስትና ያለው አደረጃጀት የሌለው ሆኗል፡፡

ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ፡-
“አማራ ላይ ሊመጣ ያለው ጥፋት ከምትገምቱት በላይ ነው ~~ አማሮች የኦሮሞ ብሄርተኞችን አቋም እና ሊያመጣ የሚችለውን ጥፋት ሊያጤኑት ቀርቶ አያውቁትም!~~~ የኦሮሞ ብሄርተኞች በኦሮሚኛ ለቁጥር በሚታክቱ ሚዲያዋቻቸው ስለ አማራ ያላቸውን ጥላቻ የሚፅፋትን ጉድ ብታውቁ ትደነግጣላችሁ!~~~ምናልባት አንድ ቀን ከእንቅልፋችን ስንነቃ ያልጠበቅነው ነገር እንዳይከሰት እሰጋለሁ!~~~ንቁ!~~~ግብዛቢያችሁን አሳድጉ!~~~ራሳችሁን ጠብቁ!”
“የኦሮሞ ብሄርተኞች ነፃ ሀገራችን የሚሉትን ለመመስረት በመጠባብቅ ላይ ያሉት አሁን ያለው የትግሬ መንግስት እስኪንገዳገድ ወይም የሆነ ክፍተት እስኪፈጠርላቸው ነው”!
“የሁሉም ኦሮሞ ብሄርተኞች የትም ይሁኑ ከማንም ጋር ይስሩ፣ በሰላም ይሁን በጉልበት፣ በአንድነት ይሁን በልዩነት የሚሄዱበት መንገድ ይለያይ እንጂ የመጨረሻ ግባቸው አንድ ነው! ~~~ኦሮምያ የሚባል የታሪክ መሰረት የሌለው አዲስ አገር መፍጠር ነው!~~~ጉዟቸውም ቀስ እያሉና በመናበብ ነው እያደረጉ ያሉት!”
”የእኛ ሰው ይህ ዘመን በራሱ ግዜ እነደቀደሙት አስከፊ ዘመናት በቀላሉ የሚያልፍ ይመስለዋል። ወገኖቼ ስላላችሁበት ዘመን ግንዛቢያችሁን አሳድጉ፣ ብሔርተኞችን በስመ አብ ብቻውን አይመልሳቸውም!”

ለዶ/ር አሰፋ ለተባለው ግለሰብ በእርግጥ ይህን የተናገረው በሥም የተጠቀሰው ሰው ከሆነ፡፡ እንዲህ ያለ መልዕክት ዛሬ ቤተአማራ የተባለ የወያኔ ቡድን ለፈጠረው የአማራ ትውልድ ሥጋት ሊሆንበት ይችላል፡፡ የአገሪቱን በጋራዊ ሁኔታ ጠንቅቀን ለምናውቅ ይህ የአማራም ሆን የሌላ ሕዝብ ሥጋት ሳይሆን የራሱ የኦሮሞ ሕዝብ ሥጋት ሊሆን እንደሚችል አስተውል፡፡ በእርግጥ እንደነ ጸጋዬ አራርሳና ጀዋር ምናምን የሚባሉ ግለሰቦች ከላይ የተጠቀሰውን ሆኖ ማየት ቢመኙ አይገርምም፡፡ 26ዓመት እኮ ይሄንኑ ሲያደርጉ ነው የኖሩት፡፡ እባካችሁ መናገር የማንፈልገውን እንነግራችሁ ከሆነ አንናገርም፡፡ ኦነግ ብዙ ሞክሯል፡፡ ያኔ በጣም ተደራጅቶ ነበር፡፡ አማራ የተባለውም በእርግጥም ያኔ ብቸኛ ነበር፡፡ በወቅቱ ሁሉም ዘመቻ በአማራ በተባለው ላይ ነበር፡፡ አሁን እንደዛ አደለም፡፡ ጀዋር 80በመቶው እስላም ነው በሚሊለት ኦሮሚያ የሙስሊም አካባቢዎች ችግሩ እንዲህ እንምታወሩት አደለም፡፡ አስታውሱ በአለፈው አመት በተደረጉ የኦሮሞ አመጾች ሙስሊም በሚበዛባቸው የኦሮሞ አካባቢዎች ሌሎች ብሄረሰቦች ብቻ ሳይሆኑ ክርስቲያን ኦሮሞዎች ተሳታፊ አልነበሩም፡፡ ልብ በሉ፡፡ ይህ እውነት ደግሞ እጅግ የከፋ ታሪካዊ ክስተት ስላለ ነው፡፡ ይህ ተዳፍኖ ዝም የተባለን ጉዳይ እነ ኦነግ እንደገና አጫጭሰውት ሁለተኛ ጊዜ ሙከራም ተካሂዷል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በሀረር፣ ባሌና ከፊል አርሲ ያሉ ክርስቲያን ኦሮሞዎች አሳምረው ያውቁታል፡፡ ጀዋር እየመራው ያለው ቡድን ኦሮሞን ሁሉ እዚህ ቁማር ውስጥ ከቶ ያንን የራሱን የእስልምና አክራሪነት ህልሙን ለማሳካት ነው፡፡ ይህ ፖለቲካ አደለም፡፡ ይህ ሀይማኖታዊ ልዩ አጀንዳ ነው፡፡ ኦሮሞ በብዛት የዚህን ሚስጢር አይገነዘብም፡፡ ክርስትና የሚበዛባቸው ወለጋና ሸዋ የመሳሰሉት በተለይ አይገባቸውም፡፡ የአርሲ ክርስቲያን ኦሮሞ ግን አሳምሮ ይገባዋል፡፡ ጀዋር እኮ በግልጽ ተናግሯል እንዲህ ነው እያለ ያለው https://www.youtube.com/watch?v=RMLLmAMWdG8(link is external) ለመሆኑ ይሄ የኦሮሞ ስብሰባ ነው ወይስ …..;

ሌላው ጸጋዬ የሚባ ግለሰብ በጣም የግል የሆነ አላማውን በኦሮሞ ሕዝብ እየነገደ ነው፡፡ ልብ በሉ ይህ ሰው ለወያኔ የሚያገለግለው ወዶ አደለም፡፡ አስተሳሰቡንም ተመልከቱን፡፡ ከአማር እናትና ኦሮሞ አባት ተወለድኩ እያለ አማራ ለተባለው ሕዝብ ያለውን ጥላች አዘል ንግግሮች፡፡ አይምሰላችሁ፡፡ ይህ ሰው ራሱን ለገንዘብ የሸጠ ጸያፍ ነገር ላለመናግር እተወዋለሁ፡፡ ሚስቱ ትግሬ መሆን ብቻም ሳይሆን ወያኔ እንደሆነች ደግሞ መዘንጋት ሌላው ይህን ሰው አለማወቅ ነው፡፡ ሰውዬው ታስታውሱ እንደሆነ ቀደም ሲል አሉ በተባሉ ሚዲያዎች ሁሉ ዋና ተንታኝ ነበር፡፡ እድሜ ለታዋቂው ድንቅ የኤስቢኤሱ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ፡፡ የሰውዬውን ማንነት ቀደም ብሎ አጥንቶት ስለነበር ሆን ብሎ ነበር ለሕዝብ ጸጋዬ የሚባል እናንተ እንደምሁር የምትከተሉት ግለሰብ ይህ ነው ብሎ በገዛ አንደበቱ ያስቀሳፈተው፡፡ ለዚህ ታላቅ ጋዜጠኛ ታላቅ ክብር ይገባዋል፡፡ አስታውሱ ኢትዮጵያዊ ማንነትን እንዲያብራራ ነበር የጠየቀው፡፡ ከዛ በኋላ ለመሆኑ ጸጋዬን ማን ሰው ብሎ ነው በኢትዮጵያ ጉዳይ ለትንተና የጋበዘው ፎረም 65ና ያው የአክራሪ ሙስሊሙ የሚመራው ኦኤም ኤን እንጂ፡፡ ፎረም 65 በግልጽ የወያኔ ሚዲያ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ ሁሌ ስለሚነገሩ ነገሮች ፎረም 65ላይ የማይጠፋውን አንድ አሉላ ሰሎሞን የሚባል ግለሰብን ስሙት፡፡ ይህ ግለሰብ ዝም አባይ ጸሀዬ በሉት፡፡ ሲናገር እራሱ ይገርመኛል፡፡ አንደም እውቀት የሌለው ነገሮችን እንደፈለገ በመዘባረቅና በማዘባረቅ የሰዎችን አስተሳሰብ የሚያምታታ ነው፡፡ በቃ የሰለጠነበት ይሄ ነው፡፡ እውቀትና አመክንዮ (ሎጂክ) እሱ ጋር የለችም፡፡ ሌሎች ደግሞ አሉ ከእሱ ተቃራኒ ተደርገው ሆን ተብለው እንዲከራከሩ የሚደረጉ ትግሬዎች፡፡ ፎረም 65 የኢትዮጵያ ምርጥ ልጅ የሆነውን መስፍን ፈይሳን ሁለት ጊዜ ጋብዞታል፡፡ መስፍንን ከዚህ በኋላ ለእነሱ ግብዣ ባይተባበር አላለሁ፡፡ በእርግጥ መስፍን አውቋቸዋል፡፡ አላማቸው መስፍንን ከሕዝብ ተሰሚነት ለማውጣት ነው፡፡ አሁን የወያኔ እግር እሳት የሆነባት እንደመስፍን ያሉ ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ የመጡበት አመጣጥ ደግሞ ሁለ ነገራቸውን የሚንድ ነው፡፡ ወደተነሳሁበት ልመልሳችሁና ጸጋዬን ከዚህ በኋላም ኦሮሞ ነው ብላችሁ የምታስቡ መቼም እንደሚገባችሁ እንጃ፡፡ እውነቱ ጸጋዬ የወያኔ ሚስቱን ተልዕኮ ነው እያካሄደ ያለው፡፡ ወያኔን መሳደብ ምናምን አትሸወዱ፡፡ ይህ ነው ስልቱ፡፡ እና ወያኔ መላዕክ ነው እያለ ኦሮሞ እንዲሰማው ትፈልጋልህ;

ሌላው ጀዋርና ቡድኑ እየሄደበት ያለውን ሂደት መስበር ያስፈልጋል፡፡ ይህ እኔን አይገባኝም፡፡ ጀዋር አሜሪካ ውስጥ ተቀምጦ እየዛተ የሚኖረበት ሕግ የለም፡፡ ኦኤም ኤን የሕዝብ ገንዘብ እንደሆን ይነገራል፡፡ ብዙ ሙስሊም ያልሆኑ ኦሮሞዎች ሳይቀሩ አስተወጾ አለን ባዮች ናቸው፡፡ ሚዲያው የኦሮሞን ሕዝብ እንዲያገለግል ከተፈለገ ከጀዋርና መሰሎቹ እጅ ማላቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ኦኤም ኤን የለንደኑንና የአትላንታውን ጉባኤ ጉዳይ ዋና ተሳታፊ እንደሆነ አስታውሱ፡፡ እነዚህ ጉባኤዎች የተደረጉበት መሠረታዊ ምክነያት ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ ወያኔን ሊጥል ከአማራ ጋር ተባብሮ አፋፍ ሲያደርሱት ነው፡፡ ወያኔን ለመታደግ የአሮሞንና አማራን ትብብር በማፍረስ ዋና አማራጭ የነበረው ደግሞ የጀዋር ቡድን ነበር፡፡ የጀዋር ቡድን በኦሮሞ ሥም የገንዘብ ንግድ ብቻም ሳይሆን እንግዲህ እንዲህ ያለ የሕዝብን ትግል ለማምከንም ሚዲያውን እየተጠቀሙበት እንደሆን አስተውሉ፡፡ በቅርቡ ስለ አዲስ አበባው አዋጅ የተለመዱትን አክራሪዎች ተሰብስበው ሲወያዩ የሚያወሩት ሁሉ የአዋጁን ሥውር ደባ ለማደባበስ ነው፡፡ ለምን ይህ አዋጅ አሁን ላይ መጣ የሚለው አጀንዳቸው አልነበረም፡፡ እንደ እውነቱ በዚህ አዋጅ ውስጥ የይዘት ጉዳይ ሳይሆን መወያያ መሆን ያለበት አዋጁ ለምን እስከዛሬ ዘግይቶ ዛሬ ሊታወጅ ተፈለገ፡፡ ማንስ ጠየቀ፡፡ እውን ዛሬ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ይሄ ነው; ይህን የምለው አዋጁን ምንም ችግር የለበትም ብለን እንውሰደውና ነው፡፡ አዋጁ ግን መጀመሪያውም መደምደሚያውም አዲስ አበባንና አካባቢዋን ከኦሮሞ የማጽዳትና መሬቱን መቀማት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ትልቁ የሕዝብ ጉዳይ ግን አስታዋሽ እንዳይኖረው ስለሚፈለግ እነጀዋር ያንን ለማውራት አይፈልጉም፡፡ ዛሬ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሕዝብ ልጆች ታስረው እየተሰቃዩ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ የአክራሪዎቹ አጀንዳ አደለም፡፡ ይህን ቦታ መነካካት ወያኔ ሰሞኑን የሰጠችውን ቤተሥራ ማጣጣልና ትቅም አልባ ማድረግ ነው፡፡ ተወያዮቹን አስተውሏቸው እንዲህ ያሉ ጥያቄቆችን አዋጁን እንደመነሻ አድርጎ ከማንሳት ጭራሽ ሕገ መንግስቱን ተሳስቷል ምናምን እያሉ እነመለስ የረሱት ጨምረውት ቢሆን ዛሬ እንዴት በጠቀማቸው የሚል አጀንዳ ከፍተው ያወሩብናል፡፡

እውነቱ አዲስ አበባ በትክክለኛ ፍትህ የኦሮሞ አደለችም፡፡ አዲስ አበባ የአዲስ አበቤዎች ነች፡፡ ዛሬ ከ7 ሚሊየን ሕዝብ የተጠጋ የሚኖረባት ከተማን የማይመለከተው ማረግ ነው አስተሳሰቡ (ውዥንብሩ)፡፡ አዲስ አበባ ኦሮሞ እንደ አንድ የማህበረሰብ አካል እንጂ ምንም አይነት የተለየ ጥቅም አያስፈልገውም፡፡ ኦሮምኛ የአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱም ተችማሪ ሥራ ቋንቋ ቢሆን ፍትሀዊ ነው፡፡ ኦሮሞዎችን ለማስደሰት ሳይሆን ከማህበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው አንጻር፡፡ አዲስ አበባ ግን ቢቻላት ኦሮምኛን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቋንቋዎችን በኦፊሴል ብታካትን የአገሪቱን ወካይነቷ ያሳያል፡፡ እንደነ ድሬዳዋ የመሳሰሉ ከተሞች የተወለዱ ልጆች ዛሬ አያርገውና በፊት አራት አምስት ቋንቋ የሚናገሩ ነበሩ፡፡ ጉራግኛና ትግሪኛ ሳይቀር፡፡ ልብ በሉ የቤተሰብ ቋንቋ ስለሆነ ሳይሆን የሕዝቡ አኗኗር እንደባሕል ነበር፡፡ ሀረር አማርኛና ኦሮምኛን ባልተጠበቀ ሰኣት እየቀያየሩ የሚያወሩ ሕዝብ የበዛበት ክፍለሀገር ነበር፡፡ አሁን ብዙ ሰው ኦሮምኛ እንጂ አማርኛ አይችልም፡፡ ማንንም አልጎዳም፡፡

ሌላው አሁንም ይሄው ጸጋዬ የሚባል ግለሰብ አዲስ አበባን ለቆ ፌደራል መንግስቱ ሌላ መቀመጫ ይፈልግ ይላል፡፡ ልብ በሉ ይህ የሕዝብን አላማና አስተሳሰብ ለማዛባት እንጂ ሀሳቡ እንደማይሆን ያውቀዋል፡፡ አዲስ አበባ የኦሮምያ ከተማ መሆን አይገባትም ነበር፡፡ ኦሮሞዎችን ለመደለል ተብሎ እንጂ የኦሮሚያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ መሆኑ ለኦሮሞ ሕዝብ የጠቀመው ምንድነው; ሁሉም ክልል ቢያንስ የእኔ የሚለው አንድ የራሱን ከተማ አልምቷል፡፡ ኦሮሚያ ግን አዲስ አበባ ላይ ደባልነት ተቀምጦ አንድም የሚረባ የከተማ ልማት ሊያካሂድ አልቻለም፡፡ እንድ ሰሞን አዳማ ቢሄድ እሱም በስንት ጣጣ ከተማዋ ምን ያህል እንደተለወጠች አስታውሱ፡፡ ሌላውን የታሪክ እውነት ትተን አሁን ያለው እውነታ አዲስ አበባን ለኦሮሞ የሚል አይደለም፡፡ በዙሪያዋ ያለው የኦሮሞ ክልል ነውና ከዚህ በአለፍ አዲስ አባባ ክልል ወደ ክልሌ አይመጣም የሚለው አስተሳሰብ ትክክለኛው ነው፡፡ ይህ ጥሩ መደራደሪያም ነው፡፡ አዲስ አባባ ውስጥ ግብር መሰብሰብ ይሉታል፡፡ መቼም ትልቁን የአዲስ አበባን ግብር ከአገኘን ሌላውን አንፈልግም እንደሆን ይገባኛል፡፡ ልብ በሉ የአዲስ አበባ ግብር ከፋይ ለሌላ ሶስተኛ መንግስት ግብር ሊከፍል ነው ማለት ነው፡፡ አዲስ አበባ የራሱ መንግስ ነው፡፡ ፌደራል መንግስቱ ዋና ዋና የተባሉ ግብር ከፋዮች የኔ ናቸው ባይ ነው፡፡ የሚሆነውን ማሰብ ጥሩ ነበር፡፡ አንድ ጥያቄ ላንሳ፡፡ አዲስ አበባ ላይ ይህ ሁሉ ሲሆን ሀረር ከተማ ያለው የኦሮሞ ባለቤትነት እንዴት ነው; ኦሮሞ በመሳከር ለ26ዓመት ያጣው መብትና ማንነት አልበቃ ብሎ ለተጨማሪ ኪሳራ መዳረግ ያሳዝናል፡፡ በነገራችን ላይ ለዘብተኛ የሚባሉትም የእነዚህን ሆን ብለው ለራሳቸው ሴራ የሚዘውሩትን ፕሮፓጋንዳ እየተከተሉ ገደል እየገቡ ነው፡፡ በሚሆን ነገር ወደፊት፡፡ የምትችሉ አስተውሉ፡፡

ጀዋርን አስመልክቶ አሁም አነሳለሁ፡፡ በህግ መጠየቅ አለበት፡፡ እሱ አሜሪካውስጥ ተቀምጦ የሰውን አንገት በሚጫ የመጨፍጨፍ ፕሮፓጋንዳ ሊነዛ አይችልም የአሜሪካ ሕግ እንዲህ ይላልና Section 802 of the USA PATRIOT Act (Pub. L. No. 107-52) expanded the definition of terrorism to cover “”domestic,”” as opposed to international, terrorism. A person engages in domestic terrorism if they do an act “”dangerous to human life”” that is a violation of the criminal laws of a state or the United States, if the act appears to be intended to: (i) intimidate or coerce a civilian population; (ii) influence the policy of a government by intimidation or coercion; or (iii) to affect the conduct of a government by mass destruction, assassination or kidnapping. Additionally, the acts have to occur primarily within the territorial jurisdiction of the United States and if they do not, may be regarded as international terrorism.

አመሰግናለሁ!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ልጆቿን ይጠብቅ

አሜን

ሰርጸ ደስታ

No comments:

Post a Comment

wanted officials