Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, January 5, 2014

ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለመታደግ የተቋቋመው ዓለም ዓቀፍ ትብብር የመጀመሪያ $30 ሽህ ዶላር ለዓለም ዓቀፉ የስደተኞች መርጃ ተቋም/ IOM አስረከበ

ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለመታደግ የተቋቋመው ዓለም ዓቀፍ ትብብር የመጀመሪያ $30 ሽህ ዶላር ለዓለም ዓቀፉ የስደተኞች መርጃ ተቋም/ IOM አስረከበ

በሳዑዲ አረቢያ ስቃይና ግፍ የደረሰባቸው ኢትዮጵያዊያንን ለመታደግ የተቋቋመው “ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት በሳዑዲ አረቢያ” የተሰኘው ማህበር $30 ሽህ ዶላር ለኢትዮጵያዊያን ይደርስ ዘንድ ለዓለም አቀፍ የስደተኞች መርጃ ድርጅት  በታህሳስ 25 ቀን 2006 አ.ም  ለገሠ::
የትብብሩ ሊቀመንበር አርቲስት ታማኝ በየነ ማህበሩ የጀመረው የገንዘብ ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ በተቀናጀ መልኩ እንደሚቀጥል አስታውቋል ። በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል ።
በሳውዲ አረቢያ ስቃይና እንግልት የደረሰባቸውን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለመታደግ የተቋቋመው ዓለም ዓቀፍ ትብብር የመጀመሪያ የገንዘብ ድጋፍ ለዓለም ዓቀፉ የስደተኞች መርጃ ተቋም በእንግሊዘኛው ምህፃር IOM ዛሬ አስረከበ ። የትብብሩ ሊቀመንበር አርቲስት ታማኝ በየነ ማህበሩ የጀመረው የገንዘብ ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ በተቀናጀ መልኩ እንደሚቀጥል አስታውቋል ። በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል ። የገንዘብ ድጋፉን የተረከበው የዓለም ዓቀፉ የስደተኞች መርጃ ተቋም የውጭ ግንኙነት ሃላፊ በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የማቋቋሙን ተግባር ለመቀጠል መጠነ ሰፊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል ።
Saudi Arabien Riad Unruhen
DW

No comments:

Post a Comment

wanted officials