Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, January 6, 2014

የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሆነ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለኢሳት ቃለምልልስ እንዳይሰጡ ታዘዙ / Stop using ESAT


የኢህአዴግ ባለስልጣናት  ሆነ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለኢሳት ቃለምልልስ እንዳይሰጡ ታዘዙ / Stop using ESAT

         የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለኢሳት ቃለምልልስ እንዳይሰጡ መታዘዛቸውን  ኢሳት በ ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓም ዜናው አስታውቆአል :: ባለስልጣናቱ ማንኛውንም ቃለምልልስ ለኢሳት ቢሰጡ በአሸባሪነት ይከሰሳሉ።  አንደኛው መገምገሚያም ለኢሳት መረጃ በመስጠት እንደሚወሰን ከኢህአዴግ የመረጃ ክፍል ያመለክቷል። መመሪያው ለህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች፣ ለደህንነት ሰራተኞች፣ ለመንግስት ባለስልጣናት እና ለ ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች መተላለፉ ታውቋል።
የመንግስት ባለስልጣናት ለኢሳት መረጃ በመስጠት ድርጅቱን ህጋዊነት እያላበሱትና ሌሎችም ዜጎች አንዲናገሩበት እያደፋፈሩ ነው የሚል ምክንያት መሰጠቱ ታውቋል። ባለስልጣናቱ ከኢሳት በተጨማሪ ለአሜሪካ ድምጽ እና ለአንዳንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ ድረገጾችም መረጃ እንዳይሰጡ ታዘዋል። መመሪያውን ያወጡት የብሄራዊ የመረጃ ደህንነት እና ኮሚኬሽን መስሪያ ቤት በጋራ በመሆን ነው።
በተጨማሪም በብሔራዊ መረጃ ና ደህንነት አገልግሎት የፌዴራል ፖሊስ የጋራ  የጸረ ሽብር  ግብረ ሃይል የተዘጋጀ ፐሮግራም አንዳንድ በሃገር ውስጥ በህጋዊነት የሚንቀሳቀሱ ፖለቲካ ፓርቲዎች የአሸባሪ ድርጅቶችን መዋቅር ለምሳሌ ያህል የግንቦት ሰባቱን የኢሳትን  ቴሌቭዝን ህግ በመጣስ ሲጠቀሙበት ይታያሉ በማለት የውሽከተ ሲሆን ለዚህም ማስረጃ የ ሰማያዊ ፓርቲና የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላትን ፎቶ በኢቲቭ ፕሮግራሙ ከማሳየቱም በላይ ኢህአዴግ በአሽባሪነት የሚፈርጀው የግንቦት ሰባት መዋቅር ንብረት ብቻ የሆነ ያህል በመቁጠር ለኢትዮጵያውያን አይንና ጆሮ ከሆነው ከኢሳት ጣቢያ ጋር መታየትና የመንግስቱን አፈና ማጋለጥ ወንጀል መሆኑን ተናግረዋል::
በጸረ ሽብር ህጉ ከየትኛውም እነሱ ከሚፈሩት ድርጅት ጋር ግንኙነት ማድረግ በህግ ያስጠይቃል; በተለይ በአገር ውስጥ በህጋዊነት እየተንቀሳቀሱ የዉጩን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንኢሳትን/ መጠቀም ከህጉ ጋር መላተም ስለሚያስከትል ኢሳትን መጠቀም ይቅርባችሁ ሲሉ አስፈራርተዋል:: ፕሮግራሙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሃገር ወስጡን ሚዲያ ለምሳሌ ኢትቭን በአማራጭነት መጠቀም ይችላሉ አላለም:: ይባሱኑ ከዚህ ይልቅ በግላቸው ድረ ገጽ ጋዘጣ የሚከትቡ ወጣቶችን በማሰር አሽባሪ በማለት የፈረጃቸውን ፍርደ ገምድል ሂደት አብራርቶአል:: ሙሉውን ለማዳመጥ ይሕንን ሊንክ ይጫኑ:: TPLF warns any Ethiopian political party not to use ESAT

No comments:

Post a Comment

wanted officials