አንጎላ በሀገሯ የእስልምናን እንቅስቃሴ አገደች ተባለ!
በትላንትናው ዕለት የግብጹ የሃይማኖት ሙፍቲ ሻውቂ ዓለም አንጎላ እስልምናን ከሀገሯ እንደሃይማኖት ተቋም ማገዷ በ 1ነጥብ 5 ቢሊዮን ሙስሊም ላይ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ልታውቅ ይገባታል ሲሉ አስጠነቀቁ። ይህም ትልቅ ዋጋ ያስከፍላታል ሲሉ ማስፈራሪያቸውንም አክለዋል።
ይሁን እንጂ 83% የክርስትና እምነት ተከታይ ያለባት አንጎላ በሃይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬቷ በኩል በሰጠችው መግለጫ በቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በታች የሆነው የሙስሊም ቁጥር በነጻነት እየኖረ መገኘቱን በመግለጽ የሚታዩት አንዳንድ የእስልምና እንቅስቃሴዎችን ግን በትኩረት እየተከታተሉ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በየቦታው እየሄዱ መስጊድ መገንባት፤ የሃይማኖት ትምህርት ቤት መስራትና እስልምናን ለማስፋፋት የሚደረጉ የእጅ አዙር እንቅስቃሴዎችን ግን መንግሥታቸው በፍጹም እንደማይቀበልና እንደማይታገስ ሳይገልጹ አላለፉም። አንጎላ ከየትኛውም የእስላም ሀገራት ጋር የትብብር ስምምነት ስለሌላት በውስጥ ጉዳያቸው የትኛውም የእስላም ሀገር እጁን እንዳያስገባ አሳስበዋል።
እስልምና በተስፋፋባቸው የአፍሪካ ሀገራት ሁከት፤ ብጥብጥና ግድያ እየተስፋፋ እያየን ቁጥሩ ምንም ትንሽ ቢሆን በሌላው ያየነው ሁኔታ በሀገራችን እንዲታይ በምንም መልኩ እድል አንሰጥም ያሉት የአንጎላው የሃይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክተር ያለንን ሰላም ለማስጠበቅ የምንወስዳቸው እርምጃዎች ከሃይማኖት ዲሞክራሲ ጋር በፍጹም አይያያዝም ሲሉ የሃይማኖት ነጻነትን ትጋፋለች በማለት ለሚጮሁ ክፍሎች አስረድተዋል።
ንግግራቸውን በማያያዝም እንደተናገሩት፤ ማንም አንጎላዊ በእምነቱ ሳቢያ በግሉ አይጠየቅም፤ አድልዎም አይደረግበትም። ነገር ግን ገንዘብና ነጻነት አለኝ ብሎ የትም እየዞረ መስጊድ ለመትከልና ከራሱ አልፎ በሌላው አካባቢ ላይ የማስፋፋት መብት የለውም። በቂ የአምልኮ ስፍራና የእምነቱ መግለጫ ስፍራ እያለው ተጨማሪ የመስፋፋት እንቅስቃሴ ሲደረግ በማግኘታችን አንድ ያልተፈቀደ መስጊድ ዘግተናል፤ አፍረሰናል፤ ይህንንም ቁጥጥር አጥብቀን እንገፋበታለን ሲሉ ጨምረው ገልጸዋል።

No comments:
Post a Comment