ዓረና ትግራይ ራኢዩን የትግራይ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ በማድረግ ወደፊት ይገሰግሳል እንጂ በህወሓት የሽብር ተግባር አይታጠፍም !!! (ከዓረና ትግራይ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)የዓረና ትግራይ 3ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ተግባራዊ ለማድረግ በትግራይ ከተሞች ተከታታይ የህዝብ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች በማካሄድ በክልሉ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር ምንጩና መፍትሄው፣ የዓረና ትግራይ ፓርቲ የፖለቲካ ራኢና ኣማራጭ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር የማስቀረት ብቃት ለማሣየት አስመልክቶ ከህዝብ ለመምከርና በትግራይ ከተሞች ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች ለማካሄድ እቅድ ተይዞ ከመጀመርያው የጥቅምት ወር 2006 ዓ/ም ጀምሮ በተከታታይ ለማካሄድ እንቅስቃሴ ተጀመረ። ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባው በቅደም ተከተላቸው በውቕሮ፣ በማይጨው፣ በዓብይ ዓዲ ከተሞች ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች ሲካሄዱ ህዝብ ወደ ስብሰባው እንዳይመጣ የማደናቀፍ ተግባር በገዢ ፓርቲው የአከባቢ ካድሬዎች የታየ ቢሆንም ህዝቡ የማዳመጥ ፣አስተያየት የመስጠት መብቱን ለመጠቀም ባሳየው ፍላጎት በስብሰባው አዳራሽ በመገኘቱ ውጤታማ የህዝብ ስብሰባዎች ማካሄድ የተቻለ ሲሆን በሽረ ከተማ የህዝብ ስብሰባ ለማካሄድ ህዝቡ ወደ ስብሰባ ኣዳራሽ እንዲመጣ በሚገባ ከተቀሰቀሰ ህዝቡም ጥሪውን ኣክብሮ ወደ ኣዳራሹ በጥዋቱ እንደመጣ የከተማው ኣስተዳደርና በፓርቲው መዋቅር በተደራጀ ረብሻ የህዝብ ስብሰባው ሳይካሄድ መቅረቱን ይታወሳል፡፡ በዕቅዱ መሰረት ፓርቲያችን በምስራቃዊ ዞን ዋና በዓዲግራት ከተማ ጥር 18 ቀን 2006 ዓ/ም የህዝብ ፖለቲካዊ ስብሰባ ለማካሄድ ኣዳራሽ እንዲሰጠን ለከተማው ኣስተዳደር ተጠይቆ ኣዳራሽ ተይዞኧል ኣይቻልም የሚል መልስ በመስጠታቸው እንግዲያው ስብሰባው በኣደባባይ እናደርገዋለን ሲባሉ ተመልሰው ኣዳራሽ ተፈቅዶላችኃል የሚል ምላሽ ተስጥቶን በስብሰባው ቀን ህዝቡ ተገኝቶ ዓረና ባዘጋጀው ኣጀንዳ እንዲመክር ለማስቻል የዓረና ከፍተኛ ወጣት ኣመራሮችና ኣባሎች በዓዲግራት ከተማና ኣከባቢዋ ተሰማርተው በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡ ሃሳብነ በነፃ የመግለፅና የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንቀሳቀሰ ነፃነት የሚያረጋግጡ መብቶች በመጠቀም በህዝባዊ ስብሰባው የሚመክርባቸው ኣጀንዳዎችና የስብሰባው ቀን፣ ስዓትና ቦታ የሚገልፀው ፅሑፍ በማደል ተሰማርተዋል፡፡
ለህዝቡ የሚታደለው ፅሑፍ የሚፈነዳ ቦንብ ኣልነበረም ወደ ህዝቡ ህሊና ዘልቆ የሚገባ ሓሳብ ብቻ ነበር፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ዓረና ትግራይ የመሬት ባለቤትነት የመንግስት መሆኑ ቀርቶ የህዝብ/ዜጎች እንዲሆን የመሬት ሊዝ ኣዋጅ እንዲሻር፣ ዜጎች ለመኖርያ የሚስፈልጋቸው ቦታ በሕገ መንግስቱ መሰረት ያለ ሊዝ የማግኘት መብታቸው እንደሚረጋገጥ፣ ለወጣት ሴቶችና ወንዶች በግፍ ለስደት መዳረግ ምክንያት የሆነው ብልሹ ኣስተዳደር በማስወገድ በሃገራቸው ሥራ የማግኘት መብታቸው እንደሚረጋገጥ፣ የሙያ ብቃት መስፈርት መሰረት ባደረገ መርህና የሙያና የኣካዳሚ ነፃነት በማረጋገጥ የመመህራንና የመንግስት ሠራተኞች ችግር ለማስወገድ እንደምንሰራ፣ በኣስገዳጅ የማዳበርያ ግዢ ለገዢው ፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ብዝበዛ የተጋለጡና በእዳ ተጭነው ለጎስቋላ ኑሮ የተዳረጉት የትግራይ ገበሬዎች ችግር ለማስወገድ የማደባርያ ግዢ በውዴታ እንደሚሆንና ግብርናውና ገበሬው ለመደገፍ ለገበሬው ድጎማ ማድረግ እንደማያስፈልግ፣ ትምህርት ቤቶች ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ እንደሚሆኑ ዋና ስራቸው የፓርቲ ኣባል ምልመላና በትምህርት ቤቶች ለሚነሱ የመብት ጥያቂዎች ማኮላሸት የሆነ የህ.ወ.ሓ.ት (ኢህኣደግ) የ 1-5 የትምህርት ኔትወርክ እንደሚቀር፣ በትግራይ ህዝብ ደምና ኣጥንት የተገኘው ሙሉ በሙሉ የትግራይ ህዝብ ሃብትና ንብረት የሆነው ት.እ.ም.ት ከህወሓት መንጋጋ ኣውጥቶ ተጠሪነቱ ለክልሉ መንግስት በሆነ በነፃ የባለሙያ ቦርድ እንዲተዳደር በማድረግ የክልሉን ማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት እነዲውል የማደረግ መሆኑ፣ በት.እ.ም.ት ሥር የሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶች ሠርተው የሚያገኙት ትርፍ በትግሉ ለተጎዱ ታጋዮችና ሲቭል ኣርበኞች እንዲሁ የሻዕብያን ወራራ ለመመከትና ሃገራቸውን ለመጠበቅ ለጉዳት የተዳረጉ ኣርበኞችና ቤተሰባቸውን ለመደገፍ እንደሚውል፣በሕገ-መንግስቱ እንደተደነገገው ገዢው ፓርቲ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንዲያቆም የሚጠይቁ ነበሩ፡፡ እነዚህ የአማራጭ ፖለቲካዊ ፕሮግራም ኣጀንዳዎች ሙሉ በሙሉ ሓሰቦች እንጂ የሚፈነዱ ፈንጂዎች ኣልነበሩም ! እነዚህ በጠራራው ፀሃይ ለህዝቡና ለህ.ወ.ሓ.ት ኣባላትና ደጋፊዎች ጭምር የቀረቡ ኣጀንዳዎች ነበሩ፡፡
እነዚህ ለህዝቡ የቀረቡ የአማራጭ ፖሊሲ ኣጀንዳዎች በሳዕሲዕ ፃዕዳ እንባ ወረዳ ዋና ከተማ ዕዳጋ ሓሙስ ለህዝቡ ሲታደሉ አንዲት ወረቀት ሳትቀደድ ኣንድ ሰው እንኳን ኣልቀበልም ሳይል ሁሉም በደስታ ተቀብሎ ለወጣት ኣመራሮቹ በኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ሙሩቕና የዓረና የሥራ ኣስፈፃሚ ኣባልና የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ ኣቶ ዓምዶም ገ/ስላሴና መም/ ሃይለ ገብረፃዲቕ ያሳየው አክብሮት የሚደነቅ እንደነበረ ይመሰክሩለታል፡፡ በሻዕብያ የወደመችው የጎሎመኸዳ ወረዳ ዋና ከተማ የነበረችው ውብዋ ዛላንበሳን በመተካት የከተመችው የፋፃ ከተማ ነዋሪዎችና የኣካባቢው ገበሬዎች የስብሰባው ኣጀንዳ፣ ጊዜና ቦታ የሚገልፀው ፅሑፍ ሲታደላቸው ህዝቡ በሰላም ተቀብሎ እንዳስተናገዳቸው ” ቀድመን መመጣታችሁ ብናውቅ ኖሮ ሻይ ቁርስ ኣዘጋጅተን እነቆይ ነበር” በማለት በኣክብሮት እንደተቀበላቸው በኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሩቅና የዓረና ትግራይ የድርጅት ጉዳይና የፅሕፈት ቤት ሓላፊ የሆኑት ኣቶ ስልጣኑ ሕሸ ና ኣቶ ሃይለኪሮስ ተፈሪ የህዝቡ ጨዋነት እንግዳ ተቀባይነትና ለኣማራጭ ሓሳብ ያለው ጥማት ይመሰክሩለታል፡፡ የዓዲግራት ከተማ ህዝብ ኣቀባበልም ተመሣሣይ ነበር፡፡
የህዝቡን የልብ ትርታ ያለማራቸው የዘኑ የገዢው ፓርቲ ኣስተዳዳሪዎች ዓረናና ህዝቡ የማይገናኙበት፣ የህዝቡ ስብሰባ የማካሄድበትና የዓረና ወጣት ኣመራሮች ሞራላቸው ተጎድቶ የሚያርፍበት እኩይ ብልሃት መዘየድ ጀመሩ፡፡ በዕዳጋ ሓሙስ የህ.ወ.ሓ.ት መታወቅያቸውን በማሣየት ለህዝቡ የስብሰባ ጥሪ የሚያድሉ የዓረና ኣባላትን ማቆም ጀመሩ፤ በፓርቲ መታወቅያ የመንግስት ሥራ መስራት ኣትችሉም ሲባሉ ሁሉም በእጃቸው ሁሉም በደጃቸው የሆነላቸው የህወሓት አባላቱ ወድያው ፖሊስ ጠርተው የዓረና ኣባላትን ኣቶ ዓምዶም ገ/ስላሴንና መም/ሃይለ ገ/ፃድቅን ወደ ፖሊስ ጣብያ በእስር ወሰዱ፡፡ አባላቶቻችን መታወቅያቸውን እንዲያሳዩ ተጠየቁ ኣሳዩ፡፡
(1) መመ/ሃይለ ገ/ፃድቅ የዓረና መታወቅያ ስለሌህ የዓረና ፅሑፍ ማደል ኣትችልም ተባለ
(2) የሚታደሉት ፅሑፍ የዓረና ማህተም ስለሌለው ለህዝብ መሰጠት ኣትችሉም ተባሉ
(3) ፅሑፍ እያደላችሁ የመኪና መንገድ ትዘጋላችሁ ኣሉ የህወሓት ካድሬዎቹ በድፍረት !
(1) መመ/ሃይለ ገ/ፃድቅ የዓረና መታወቅያ ስለሌህ የዓረና ፅሑፍ ማደል ኣትችልም ተባለ
(2) የሚታደሉት ፅሑፍ የዓረና ማህተም ስለሌለው ለህዝብ መሰጠት ኣትችሉም ተባሉ
(3) ፅሑፍ እያደላችሁ የመኪና መንገድ ትዘጋላችሁ ኣሉ የህወሓት ካድሬዎቹ በድፍረት !
በስንት ንትርክ ለሚያጋጥማቹሁ አደጋ በራሳችሁ ሓላፊነት ተብለው ሥራቸውን ቀጠሉ፡፡ በራሳችሁ ሓላፊነት? ሲባል ብትደበደቡ ብትዋረዱ ብትገደሉ የሕግ ከላላ ኣንሰጥም ማለት ነበር፡፡ ያለምንም እንከን ህዝቡ በሰጣቸው ሞራል ስራቸውን በሚገባ ፈፅመው በደስታ ወደ ዓዲግራት ተመለሱ። ይህ የሆነው ዕለት ሓሙስ ጥር 15 ቀን 2006 ዓ/ም ነበር፡፡ በዓዲግራት ኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴና ኣቶ ኣብርሃ ደስታ እንዲሁም መም/ፍፁም ግሩምና መመ/ገዛኢ ንጉሰ ኢሉ፡፡ ሓሙስ ጥር 15 ቀን 2006 ዓ/ም የስብሰባ ጥሪ የሚገልፀው ፅሑፍ በዓዲግራት ማደል ማደል ተጀምረዋል፡፡ ዕለተ ዓርብ ጥር 16 ቀን 2006 ዓ/ም የዓዲግራት ከተማ ሰፊ በመሆኑ ኣቶ ስልጣኑ ሕሸ፣ ኣቶ ሃይለኪሮስ፣ መም/ገዛኢ ንጉሰ፣ መመ/ፍፁም ግሩም በቀበሌ 01 ሲንቀሳቀሱ ህዝቡ ምግብና ውሃ እየሰጠ የስብሰባው ጥሪ እየተቀበለ በክብር እንዳስተናገዳቸው ይመሰክራሉ።
ይህንኑ እውነት እየተከታተሉ ይታዘቡ የነበሩ የጥፋት መልእክተኞች የዓረና መመራርና ኣባላት ለማወክ ተዘጋጅተው ኖረው የስብሰባው ጥሪ ለህዝቡ የሚያድሉ ወደ ሆስፒታል ኣከባቢ ሲደርሱ የቀበሌ ካድረ የሆኑ ሴቶች ወረቀቱን ተቀብለው መቅደድ ጀመሩ፡፡ ዕድሜኣቸው ከ12-16 ዓመት እንደሆኑ የሚገመቱ ህፃናትም መሰብሰብ ጀመሩ ሆ! እያሉ መረበሽ ጀመሩ፣ ሴቶቹ መብታቸው በማለት አደፋፈሩ። የማወክ መብት? ህፃናቱ የተላኩ እንጂ የራሳቸው ኣጀንዳ የሌላቸው መሆኑ በተግባር ለመፈተን የወዳደቁ የስኳርና የቡና መጠቃለያ የደብተርና የጋዜጣ ፅሑፎች ሲሰጣቸው የዓረና ፅሑፍ መስሎአቸው ሳያዩት ተቀብለው ወድያው ይቀዱታል ልክ የስብሰባው መጥሪያ ፅሑፍ ተቀብለው እንደቀደዱት፡፡ ለህፃናቱ መብታችሁ ነው እያሉ የሚያጅቡ ትላልቅ ወንዶችና ሴቶችም ነበሩበት ። ህፃናቱ ሁሉም ሊባል በሚችል ሲጋራ ያጤሳሉ ፣ ስትቀርባቸው መጠጥ መውሰዳቸው የሚሳውቅባቸው በእጅጉ ጠጅ ይሸቱ ነበር። የአከባቢው ሰዎች በሰጡት መረጃ መሰረት የተለያየ ሱስ ተጠቃሚዎች ለመሆናቸው በከተማው ፖሊስ የሚታወቁ ናቸው።በዚህ የውንብድና ተግባር በዓረና ከፍተኛ ወጣት አመራሮችና አባሎች የአካልና የሞራል ጉዳት ተፈፅሞአል ፣ የቀበሌ ሴቶች በፌስታል አፈር እያቀበሉ ህፃናቱ በአዓረና አባላት በላያቸው ላይ አፈር በማፍሰስና እክታ በመትፋት አሳፋሪ ወንጀል ሲፈፀም በዓዲግራት ከተማ የሚገኙት የከተማው አስተዳደርና ፖሊስ የዞኑ አስተዳደርና ፖሊስ መብታቸው ነው እያሉ ያሳዩት የወንጀል መተባበር አሳፈፋሪ ተግባርና መንግስታዊ ውንብድና የሚያሰኝ ነው።
በዛው ጨዋ ህዝብ ፊት እነደዚህ ያለ የውንብድና ተግባር ተፈፀመ፡፡ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ተግባሩ የተቀነባበረው በዞኑ በከተማው መስተዳድር ስለመሆኑ ኣስተዳዳሪዎች፣ ፖሊስ ያሳዩት ተግባራቸው ይመሰክርላቸዋል፡፡
በነዚህ ጥቂት ቀናት የዞኑ መስተዳድር የፀጥታ ኣደጋነቱን በተግባር ሲያስመሰክር ህዝቡ ደግሞ የሕግ ኣስከባሪነት ሚናው መወጣቱን በገሃዱ ዓለም ቁጭ ብሎ ታይቶኣል፡፡ መስተዳደሩ በራሳችሁ ሃላፊነት የህግ ከለላ ኣንሰጣችሁም ሲል በዓረና ኣመራሮችና ኣባላቶች ሊያወርዱት የከጅሉት ወንጀል ጠቋሚ ነበር። የህዝብ ስብሰባው እንዳይካሄድ የተፈጠረው ውንብድና የመስተዳድሩ እጅ እንዳለበት የሚያሳየው -የዞኑና የከተማው መስተዳደርና ፖሊሲ በኣባሎቻችን የተፈፀመውን በዓይናቸው ያዩት ወንጀል ማጠራትና ማስቆም ሲገባቸው ፍርደ ገምድል እንዲሉ በሞባይል ስልክና፣በካሜራ ቀርፃችሁናል ህፃናቱም ቀርፃችሁኣል ትፈተሻላችሁ ብለው የሁሉም አባሎቻችን ሞቫይልና ካሜራ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ መቦርበራቸው፣ በተደራጀና በህፃናት ከለላ የተደበቀ የወንብድና ተግባር ሲፈፀም መስተዳደሩና ፖሊሱ እያዩ በጠራራ ፀሃይ በኣባላቶቻችን ላይ ኣሰቃቂ ግፍ እነዲፈፅሙ ሙሉ ፍቃድ ማሳየታቸው የሚያስቆጥራቸው በመሆኑ ፣በሕግ የተቋቋመ ፓርቲ የቆመለትን ራኢና ፖሊሲ ለህዝቡ ለማስተዋወቅና በክልሉ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር የሚገራበት መንገድ ከህዝቡ ለመምከር ያደረግነው ጥሪ እንዳይሳካ ለማወክ የተላኩ ህፃናት መብታቸው ነው እያሉ የሕገ-ወጥ ተግባር ከለላ መስጠታቸውና ለባሰ ጥፋት እንዲዘጋጁ ማበረታታቸው የወንጀሉ ተሳታፊ የሚያደርጋቸው መሆኑንየከተማ ፖሊስ የኣረና ኣባላት ባረፉበት ሆቴል ማታ አልጋ በያዙበት ሆቴል ከምሽቱ 4፣00 ሰዓት ተገኝቶ እሁድ ለሚካሄደው ስብሰባ የእግር ኳስ፣ የብስከሌታ ውድድር ስላለ በቂ የፖሊስ ሃይል የለንም በማለቱ ስብሰባው እንዳይካሄድ በማደናቀፍ ምክንያት መሆኑን በተደራጀ ወንብድና የኣካል ጉዳት የደረሰባቸው የኣረና ኣባላት በከተማው ጤና ጣብያ ተመርምረው የራጀ ምርመራ እንደሚያስፈልጋቸውና ሆስፒታል እንዲወሰዱ በሃኪም የተሰጠ ትእዛዝ በፖሊስ ኣለመፈፀሙን፣ የተፈፀመው የወንብድና ተግባር ለማድበስበስ በሃሰት ክስ፣ በኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴና መም/ፍፁም ግሩም የተቀነባበረው ወንጀላ እየተፈፀመ መሆኑን ነው ።
ህ.ወ.ሓ.ትና መስተዳድሩ ወደዚህ የፖለቲካ ቅሌት የሚገፋፋቸው ያለው በዓረና የኣማራጭ ፖሊሲ ልዕልና መርበትበቱንና ወደ እራቆቱ የወጣ በጠራራ ፀሃይ የኣማራጭ ፓርቲ ወጣት መሪዎችን በማፈን ማንበርከክ መምረጡንና የትግራይ ህዝብና ወጣት ልጆቹ የከፈሉት መስዋእትነት ጭራሽ ከምድረ ትግራይ ጠራርጎ ለማጥፋት መቑረጡን የሚያሳይ እኩይ ተግባር በመሆኑ የዓረና ትግራይ ፓርቲ የተቃውሞ ድምፁን ከፍ በማድረግ ለትግራይ ህዝብና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያሰማል፡፡ ዓረና ትግራይ የትግራይ ህዝብ የከፈለው የ17 ዓመታት የትግል ዘመን ብህ.ወ.ሓ.ት ተቀብሮ እንዳይቀር በማደስ የተነሳ ፓርቲ እንደመሆኑ በህ.ወ.ሓ.ት የሽብር ተግባር የማይታጠፍ መሆኑን በማረጋገጥ በህዝባችን ፊት የሚከፈለውን ሁሉ መስዋእትነት እየከፈልን ብፅናት የምንቀጥልበት መሆኑን ለመግለፅ ይወዳል፡፡
የዓዲግራት ከተማ ወጣቶች የተደረጁ ኣሸባሪ ወንጀለኞችን በመመከት የኣባለቶቻችን ህይወት ለመታደግ ያሳየው ድፍረት እንዲሁም የዕዳጋ ሓሙስ ከተማ ነዋሪዎችና የፋፂ ከተማ ነዋሪዎች ዓረና ለህዝቡ የቀረበው ጥሪ በማክበር ያሳያችሁት ኣክብሮትና ፍላጎት ኣክብሮታችን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ዓረና ትግራይ ፓርቲ በዚሁ የወንብድና ተግባር ሳይንበረከክ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ህዝብ በኣጠቃላይና በዓዲግራትና ኣከባቢዋ የህዝብ ስብሰባ በመጥራት ከህዝቡ መምከር በፅናት እንደንቀጥልበት በእርግጠኝነት ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
ጥር 18 ቀን 2006 ዓ/ም
መቐለ
መቐለ
No comments:
Post a Comment