ወያኔ ኢትዮጵያዊ አለመሆኑን ያስመሰከረው ገና ከማለዳው ነው፡፡
ብዙውን ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግስት በዜጎቹ ላይ በሚሰራው ግፍና በደል አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እነዚህ ሰዎች ኢትጵያዊ ናቸውን? የሚል ጥያቄ ሲያነሳ ይሰማል፡፡ እኔ ግን ለዝህ ጥያቄ ጥርት ያለ መልስ አለኝ፡፡ ኢሕአዴግ ወያኔ ኢትዮጵያዊ አይደለም፡፡ ለዚህ በርካታ ምክንየቶችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ኢሕአዴግ ማንነት የሌለው በማንነቱ የማያምን ድርጅት ነው፡፡ ከፍተኛ አመራሩ ሟች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ስለኢትዮጵያዊነት ስለአንድነት ስለማንነትና ስለዜግነት በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ መልስ ከመስጠት ይልቅ ይህን ጥያቄ የሚያነሱ ፊውዳላዊ አመለካከት ያላቸው ወይም የደርግ ኢሠፓ ርዝራዦች በማለት የከሳሉ፡፡
ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ጋር ተያይዞ የሚነሳውን የማንነት ጥያቄ የአማራ የነፍጠኛ አስተሳሰብ በማለት ያጣጥላሉ፡፡ ህውሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግሥት በኢትዮጵያዊነት የማንነት ዙሪያ ላይ ያለው አቃም የወረደና የዘቀጠ በመሆኑ የሰው ዘር መገኛ የሆነችውን ሐገር ከሦሥት መቶ ዓመት የዘለለ ታሪክ የላትም በማለት ይደመድማል፡፡
ሶማሌው፣ አፋሩ፣ ኦሮሞው፣ አማራው፣ ትግሬው፣ ወላይታው፣ ከምባታው፣ አኝዋኩ፣ ጉምዙ ወዘተ……………. ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በኢትዮጵያዊነታቸው ሲኮሩ የመንግስቱ ባለስልጣናት በአብዛኛው ኢትዮጵያዊነታቸውን ይክዳሉ፡፡ ወያኔው ኢትዮጵያዊ አለመሆኑን ያስመሰከረው ገና ከማለዳው ነው፡፡ በኢትዮጵያዊነቱ አምኖ ከኢትዮጵያ ብሄረ ብሄረሰቦች ጋር በጋራ በአንድነት የመኖር ኢትዮጵያን የማልማት የጋራ እቅድ የለውም፡፡ ኢትዮጵያው የሆነ ህብረ ብሄር ድርጅትን ይቃወማል፡፡ በህብረ ብሄር ድርጅቶቸ ውስጥ ያሉ አባላትን ያሳድዳል ያስራል ያንገላታል፡፡ ኢሕአፓ፣ መኢአድ፣ ህብረት፣ ቅንጅት፣ መድረክና ሰማያዊ ፓረቲ የኢህአዴግን ዱላና ጡጫ የቀመሱ ብሔራዊ ድርጅቶች ናቸው፡፡ በኢህአዴግ መንግስት የኢትዮጵያውያን የማንነት ጉዳይ በከፍተኛ ደረጃ ወድቋል፡፡
በርካታ ኢትዮጵየውያንን ያውም በገዛ አገራቸው ለጨፈጨፈው ግራዚያኒ በጣሊያን አገ ር የመታሰቢያ ሃውልት ሊቆም በታሰበበት ወቅት በአለም ዙሪያ በርካታ ተቃውሞዎች ተሰምተዋል፡፡ የአለም የመገናኛ ብዙሃን አብይ ዜና ይህንኑ የተቃውሞ ሰልፍና ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ስብሰባዎችንና ንግግሮችን በማስተናገድ ተጠምደው ነበር፡፡ የበርካታ ሃገረ መንግስታት ዜጎችም ተቃውሞውን በመደገፍ ከኢትዮጵያውያን ጎን በመቆም ለጨፍጫፊው ግራዚያኒ የመታሰቢያ ሃውልት እንዳይቆም የጣልያንን መንግስት ሲያግባቡ ተስተውለዋል፡፡
የግራዚያኒ ሃውልት እንደዳይቆም የታቃወሙ ጭፍጨፋው በተካሄደባት አገር አዲስ አበባ የሚገኙ ኢትዮጶያውያን በመንግስት ዱላ ተደብድበዋል፡፡ ለከፋ እንግልትና እስር ተዳርገዋል፡፡ ኢሕአዴግ ወያኔ ህያው ከሆነው ኢትዮጵያዊ ይልቅ ለሞተው ግራዚያኒ ክብር ይሰጣል፡፡ የዚህ ዋናው ምክንያት ኢትዮጵያዊ ማንነትን የማጥፋት አቋም ነው፡፡ የመሪዎቻችን የዘር ግንድ ሲወርድ ሲዋረድ ግራዚያኒ ላይ የሚደርስ ይሆን? ሌላ ምን ምክንያት ሊኖር ይችላል? ኢትዮጵያውያንን በገዛ ሃገራቸው ጭፍጨፋ ላደረሰባቸው ግራዚያኒ አረመኔ ድርጊቱን ሥራውን በበጎ የሚዘክረ የመታሰቢያ ሃውልት መቆም የለበትም በማለት ድምጻቸውን ያሰሙ ንጹሃን ዜጎችን ሰብአዊነት በጎደለው ተግባር በፖሊስ ቆመጥ መደብደብ ያለሃጥያታቸው ማሰርና ማንገላታት ምን ይባላል? ወያኔዎች ከግራዚያኔ የተደቀሉ ዲቃሎች በመሆናቸው ብቻ እንጅ፡፡
በርካታ በሸዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳኡድ አረቢያ መንግስት እየደረሰባቸው ያለውን እንግልት እና ለህልፈተ ህይዎት መዳረግ መንግስታችን አላሳሰበውም፡፡ እናት ምድራቸውን እየለቀቁ ወደ አረቡ አለም የሚሄዱት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከአገር የመውጣታቸው ምክንያት ድህነት ብቻ ሳይሆን የመንግስት ሰብአዊነት የጎደለው አገዛዝ ጭምር ነው፡፡ አብዛኛው የገጠሩ አካባቢ ስደተኛ የኢሕአዴግ ሹሞች መሬቱን ስለነጠቁት በምርጫ 97 ወቅት ኢሕአዴግን አልመረጥክም በማለት እያሳደዱት በመሆኑ አገሩ ላይ መስራት ስላልቻለ ስደትን አማራጭ አድርጓል፡፡ /መረጃውን ያገኘሁት ከስደተኛ ወገኖቻችን ነው፡፡/ ሳውዲ የቀሩ ወገኖች ወደ ሃገር ብንመለስ ከዚሀ የባሰ ስቃይና መከራ ይገጥመናል፡፡ ለስደት የዳረጉንን የኢህአዴግ ሹመኞችን አናይም፡፡ እነሱን በማየት የሚደርስብን የሞራል ውድቀት አረቦች እያደረሱብን ካለው እስራት እንግልትና ስድብ የበለጠ ስለሆነ እዚሁ መቅረት የሚል ምላሽ አላቸው፡፡
እስካሁን ባለኝ መረጃ መሰረት አስራሦሥት ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ህይዎታቸውን አጥተዋል፡፡ ወያኔው ኢሕአዴግ የተቃውሞ ድምጽ አላሰማም፡፡ የጣሊያን ውልድ ነኝ የሚለው ወያኔ ከአረብም የተገኘ ዲቃላ ይሆን? የዜጎቻችንን መንገላታትና መሞት በመቃወም ሰልፍ የወጡ የሰማያዊ ፓረቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ መንግስት የተለመደውን የሃይል እርምጃ ወስዶል፡፡ ሳውዲዎች ምን ያርጉ ኢትዮጵያውያን በገዛ አገራቸው ሲጋዙና ሲሰደዱ አይተዋል ሰምተዋል፡፡ /የቤንሻጉሉን ማስታወስ በቂ ነው፡፡/ አገሩ ላይ ሥርዓት ማስከበር ያልቻለ መንግስት ውቂያኖስ አቋርጦ የዜጎቹን መብት ማስከበር እንደማይችል ያውቁታል፡፡
የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያውያንን ከኤርትራ ግዛት ሲያስወጣ የወያኔው መንግስት በምትኩ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የተወለዱ ኤርትራን በስም እንጅ በአካል የማያውቋትን ዜጎች አስዎጥቷል፡፡ እንዲያውም አብዛኛው የወያኔ ህውሃት መሪዎች የኤርትራ ደም እያላቸው፡፡ የሳውዲ ዜግነት ያላቸው ዜጎች ለምን እንዲወጡ አላደረገም? ሌላው ቢቀር የሳውዲ መንገስት በዜጎቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን ድብደባና ግድያ አቁም ለማለት ለምን ድፍረት አጣ? ወያኔ ከግራዚያኒ እንደተገኘ ሁሉ ሌላኛው ወገኑ አረብ ይሆን? ወያኔው ወደደም ጠላም ሊተገብራቸው የሚገቡ ጉዳዮች……….
• በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት ባስቸካይ እንዲቆም ማድረግ
• ደመወዛቸውን ሳይቀበሉ የተባረሩ ኢትዮጵያውያን ደመወዛቸውን እንዲያገኙ ማድረግ
• በሞት ለተለዩን ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች የህዎት ካሳ እንዲከፈል ማድረግ
መንግስት ይህን ለመፈጸም ፈቃደኝነት የሚጎለው ይሆናል፡፡ ለኢትዮጵያዊ ከኢትዮጵያዊነት ማንነት የሚበልጥበት ጉዳይ ስሌሌለ ኢሕአዴግ ሊያስብበት ይገባል፡፡ የሳውዲ ዜግነት ያላቸው አረቦች ይውጡ!! የሚል አቋም ከተነሳና ከጎለበተ ለራሱ ለወያኔም ያስፈራዋል፡፡

SOURCE : freedom4ethiopian
No comments:
Post a Comment