Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, January 24, 2014

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዛሬ የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ዋሉ Anti terror Demonstrations by Ethiopian Muslims


(ዘ-ሐበሻ) የእፎይታ ጊዜ ወስዶ የነበረው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንስቃሴ ዛሬ በኢትዮጵያና በአንዳንድ የዓለማችን ክፍሎች ቀጠለ። ‹‹730 ቀናት ለሃይማኖት ነጻነት›› በሚል ለዛሬ የተጠራው የአርብ (ጁምዓ) መርሀ ግብር በአዲስ አበባ የአንዋር መስጊድ ቁጥሩ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተገኝተው ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል። ይህ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች “የ730 ቀናት የሃይማኖት ነፃነት” እንቅስቃሴ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሚገኙባቸው የዓለም ክፍላት የሚቀጥሉ ሲሆን በሚኒሶታ ሴንትፖል ከ11:30 ጀምሮ እንደሚደረግ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
ድምፃችን ይሰማ ለዘ-ሐበሻ እንደላከው መረጃ ከሆነ ዛሬ በአንዋር መስጊድ የተደረገው እንቅስቃሴ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሕዝብ ወኔ የታየበትና ጥያቄውም እንደሚቀጥል የሚያሳይ ነው።
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እስር ቤት የሚገኙት ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱ ቢጠይቁም፤ ከመንግስት በኩል የተሰጠ ምንም ምላሽ የለም። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአደባባይ ድምጻቸውን እስከዛሬ ድረስ ቢያሰሙም መንግስታዊ ሚድያዎች “የሃይማኖት አክራሪነት ወንጀል ነው” የሚሉ ቪድዮችን ከማሳየት ውጭ አንዳችም ቀን ጥያቄያቸውን ዘግበው አለማወቃቸው ሙስሊሞቹን እያስቆጣ የሚገኝ ጉዳይ ነው ተብሏል።በዛሬው የሰደቃ እና ዱአ መርሀ ግብር በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የሚገኙ ሙስሊሞች በእስር ላይ የሚገኙ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላትን አስበው ውለዋል። እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሳትም ለፈጣሪያቸው ተመጽኖ አቅርበዋል።

በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጊድ በመቶሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ተገኝቶ ድዋ አድርጓል። መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ተቆጣጥሬዋለሁ በማለት መግለጫዎችን ሲሰጥ ቆይቷል። የተለያዩ ፊልሞችን በመስራትም የሙስሊሙን ተቃውሞ ከሽብርተንነት ጋር ለማያያዝ ሙከራ እያደረገ ነው። የዛሬው ተቃውሞ በመንግስት ሊመቀርበው የቅስቀሳ ፊልሞችና በ ቃሊቲ የሚገኙት አስተባባሪዎች ሙስሊሙ ትግሉን እንዲቀጥል ላቀረቡት ጥሪ የተሰጠ ምላሽ ይመስላል።
በአንዋር መስጊድ የነበረውን በትንሹ በቪድዮ ለማየት Video banned by youtube , Open your facebook to open link below

No comments:

Post a Comment

wanted officials