Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, January 5, 2014

የህወሀት ባለስልጣናት የመከላከያ አዛዥነቱ ከህወሀት እንዳይወጣ ለማድረግ ሲጥሩ መክረማቸው ተሰማ

የህወሀት ባለስልጣናት የመከላከያ አዛዥነቱ ከህወሀት እንዳይወጣ ለማድረግ ሲጥሩ መክረማቸው ተሰማ

ኢሳት ዜና :-በመከላከያ ውስጥ የሚገኙ ወታደራዊ አዛዦች ለኢሳት እንደገለጹት የህወሀት ባለስልጣናት ጄኔራል ሳሞራ የኑስን ለመተካት የተሻለ ቦታ ላይ የነበሩትን ጄ/ል አበባው ታደሰን አድማ ለማድረግ አስበዋል በሚል ሰበብ ማእረጋቸውን እንደያዙ የሚሰጣቸው ሃላፊነት እንዲቀነስና ከውድድር ውጭ እንዲሆኑ አድርገዋል። ለዚህም ስራ ጄኔራል ማሞ ሀይለማርያም እና ጄኔራል ሰሐረ መኮንን ተባባሪ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሶስቱ ጄኔራሎች “ጄኔራል ሳሞራ የኑስ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ሙስና ለመከላከል ብቃቱ ጎሏቸዋል በሚል እንደተነጋገሩና ጉዳዩ በወታደራዊ ደህንነት መምሪያ ክፍል ሲታይ ቆይቶ በመጨረሻም ይፋ ተደርጎ” ሶስቱም ጄኔራሎች በያዙት ማእረግ ሃለፊነታቸው ቀንሶ እንዲሰሩ ተወስኖባቸዋል። ይሁን እንጅ ጄ/ል ሞላ እና ጄ/ል ሳህረ ከጄኔራል አበባው ጋር በአድማው የተሳተፉት ሆን ተብሎ ጄ/ሉን ከስልጣን ተፎካካሪነት ለማስወጣትና ፍትሀዊ ውሳኔ የተላለፈ መሆኑን ለተቀሩት የሰራዊቱ አባላት ለማሳየት መሆኑን ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል።
ጄ/ል ሳሞራን ይተካሉ ተብለው የሚታሰቡት በቅርቡ የሌ/ጄ ማእረግ ያገኙት ጄ/ል ዮሃንስ ገብረመስቀል ናቸው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials