Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, February 21, 2014

አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው bare foot demonstration request

andent ena meadaeup
aeup
በዛሬው እለት 14/06/2006 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የአንድነትና የመኢአድ አባላት በሞንታርቦ በመቀስቀስ ላይ ሲሆኑ በራሪ ወረቀት የሚያድሉ አባላት በፍፁም ቁርጠኝነት የብአዴኑ ባለስልጣን የተናገሩትን በመቃወም በባዶ እግራቸው በከተማዋ በመዘዋወር ለህዝቡ ግንዛቤ እየፈጠሩና በራሪ ወረቀቶችን እያደሉ ሲሆን የከተማው ነዋሪ በቁጭት አጋርነቱን እየገለፀ ይገኛል።
bahir5
bahir6
በረዳት አንስፔክተር ክንፈ ሀይሌ ጉልላት የሚመራ የፖሊስ ሀይል በተለምዶ ከአባይ ማዶ በሚባለው አካባቢ የመኪና ላይ ቅስቀሳ እናዳይደረግ ማይክራፎን መበስበር ጭምር ሙከራ ቢያደርግም የከተማዋ ነዋሪዎች የፖሊሶቹንና የትራፊኮቹን ህገወጥ ድርጊት አስቁመዋል፡፡ አካባቢው “ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም” በሚለው ዜማ ደምቋል፡፡ ፖሊሶቹ ከህጉ ይልቅ ለአለቆቻቸው ታማኝነታቸውን እያረጋገጡ መሆናቸው ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል፡፡ ህዝቡ ቀስቃሾቹ ሊነኩ አይገባም በማለት ተቃውሞውን እያሰማ ይገኛል ረዳት ኢንስፔክተሩ ተጨማሪ ሀይል እንዲመደብላቸው ትዕዛዝ ቢያስተላልፉም በህዝቡ ጫና የቅስቀሳ ቡድኑ ስራውን ቀጥሏል፡፡
የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባላት ዛሬ ባህር ዳር ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በመኪና ከሚደረጉ ቅስቀሳዎች በተጨማሪ ፣ ሜጋፎን በመያዝ በርካታ አስተባባሪዎች በ እግር ሕዝቡን እየቀሰቀሱ ሲሆን፣ የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶችን ሕዝቡ እየተሻማ ነው እየወሰደ ያለዉ።
ኢሕአዴግ የራሱን በራሪ ወረቀቶችም እየበተነ ሲሆን፣ «ኢሕአዴግ ወረቀቶችን የመበተን፣ የሚነሳበትን ክስ የመከላከል ሙሉ መብት አለዉ» ያሉት የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ ፣ ሕዝቡ የሁለታችንንም ሰምቶ የመፍረድ አቅምና ችሎታ እንዳለውም ይናገራሉ። «እኛ የምንቃወመው፣ ሕገ መንግስታዊ መብታችን ተረግጦ ‘ሕዝቡን አትደርሱ፣ ሰልፍ አትዉጡ፣ ሕዝቡን አታስተምሩ …፤ ሕዝቡን ደግሞ ሰልፍ ከወጣህ እንዲህ ትሆናለን ፣ እንደዚያ ትሆናለህ .. እያሉ ሲያስፈራሩት ነዉ» ያሉት አቶ ሃብታሙ ለሕዝብ በሰላም አማራጭች ሲቀርቡለት ከማየት በላይ የሞኢአስይደስታቸው ነገር እንደሌለም ያስረዳሉ።
በባህር ደር የተጀመረዉም ቅስቀሳ ከወዲሁም ከፍተኛ ዉጤቶችን አስመዝግቧል። ያለ ፍርሃት ሕዝቡ ድምጹን ማሰማት መቻሉና የፍርህት ቀንበር መሰበሩ አንዱ ትልቁ ድል ነዉ። በተደረገው ቅስቀሳም ኢሕአዴግ ምላሽ እንዲሰጥ የተገደደበት ሁኔታም አለን። አቶ አልመነህ መኮንን በኢቲቪ ቀርበው እንዲታስተባብሉ መድረጉና እና ፣ ሕዝቡን ለማግባባት ወረቀቶች መበተናቸው ፣ የሕዝብ ዉስጣዊ ግፊት መጨመሩ የሚያመላክት ሌላዉ ሁለተኛ ድል ነዉ።
ቅስቀሳዉ በስፋት ዛሬ እና ነገ ይቀጥላል። የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ አስፈላጊና ወሳኝ ነዉ። ባህር ዳር የምንገኝ ሁሉ፣ እንዉጣ፣ ድምጽችንን እናሰማ፣ ከየመንገዶቹ አረንግውዴ ቢጫ ቀይ ስንደቅ አላማችንን እያወለበለበን፣ «ተከበርሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሰ ይዉደም» እያልን ድምጻችንን አናሰማ። በባህር ዳር ርቀን ያለን፣ በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ ያለን፣ በሶሻል ሜዲያ ቅስቀሳ፣ በግንዘብ ድጋፍ፣ በጽፉህ፣ በምክር ድጋፋችንን እናሰማ።
በአገር ቤት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለመከታተል እና ለማገዝ የሚከተሉት ይጎብኙ፡
የሚልየመን ድምጽ ለነጻነት ፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/MillionsOfVoicesForFreedomUdj

No comments:

Post a Comment

wanted officials