Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, February 10, 2014

የኢትዮጵያ ህሊና እስረኞች መታሰቢያ ቀን በጀርመን ተካሄደ የግንቦት ሰባት የኑረምበረግ ከተማ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በይፋ ሰራ ጀመሩ

የኢትዮጵያ ህዝብ ሲቪክና ፖለቲካ ተቋማት አንድነት ድርጅት EPCOU አዘጋጅነት በኑረምበርግ ከተማ ጀርመን የሚገኙ አትዮጵያውያን  በግፍ የታሰሩ የህሊና እስረኞችን ፌብሯሪ 8 ቀን አስበው ዋሉ፤ በዕለቱ ከ 300 በላይ ታዳሚዎች ና  የኢሳት ጋዜጠኞች፤ 17 ዓመት ታስረው የተፈቱት ጋዜጠኛ አበራ የማነ አብ ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞችን ለመዘከር የተካሄደው ስብሰባ በደመቀ ሁኔታ ነበር። አብዛኛው ተሳታፊዎች ወጣቶች   በነበሩበት በዚህ ስብሰባ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮች የየድርጅታቸውን መልዕክት አስተላልፈዋል።
እነዚሁ የ ኢህአፓ፤የግንቦት ሰባት ንቅናቄ፤ የ አርበኞች ግንባር ተራበተራ ሰለታሰሩት ወገኖች ፥ሰለሚያስፈልገን የሃገር ነጻነት ቅስቀሳ የተደረገ ሲሆን በተለይ የግንቦት ሰባት የኑረምበረግ ከተማ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በይፋ ሰራ መጀመሩ ተበስሮ ድርጅቱን የሚያሰተዋውቁ ብሮሸሮች ታድሏል።
በመቀጠልም የ ኢሳት የጀርመን ተወካይ ወያኔ እንዳማረረን ሁሉ አምርረን ልንታገለው እንደሚገባ የሚያስገነዝብ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የዕለቱ ተጋባዥ አንግዳ የነበሩት በለንደን የ ኢሳት ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት አቀንቃኝ አቶ ውንድማገኝ ጋሹ ኢሰበዊ ድርጊት የተፈጽመባቸውን ኢትዮጵያውያን የሚያሳይ ሰቆቃ ፊልም ያሳዩ ሲሆን ነጻነት ያለመስዋዕትነት አይገኝም የታሰሩ ወገኖቻችንን ለማስፈታት ጥረታችንን አናቋርጥም ብለዋል።
ከ 17 ዓመት በላይ ታስረው የተፈቱት ጋዜጠኛ አቶ አበራ የማነ አብ ከቤልጂየም በስካይፕ በወያኔ እስር ቤት ያሳልፉትን የትግል ተሞክሮ አካፍለው ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
Memorial day of Ethiopian Prisoners in Germany

004005

No comments:

Post a Comment

wanted officials