የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው አባላት በመንግስት ስራ ውስጥ ድርሻ አይኖራችሁም ተብለው መባረራቸውን የተባረሩ የፓርቲው አባላት ለኢሳት ገልጸዋል። አብዛኞቹ ለሱዳን እየተሰጠ ያለውን መሬት በተመለከተ ተቃውሞ በማሰማታቸው መባረራቸውን ገልጸዋል።
የምእራብ አርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው አቶ አንጋው ተገኝ፣ በድንበር ጉዳይ ጥያቄ በማንሳታቸው መባረራቸውን ገልጸዋል
ከተባረሩት የፓርቲው አባላት መካከል
አወቀ ብርሃኑ፣ አባይ ዘውዱ ፣ አንጋው ተገኝ፣ አብርሃም ልጃለም እና አለልኝ አቡሃይ ይገኙበታል።
እነዚሁ ግለሰቦች ሐምሌ 7 2005 ዓ ም የአንድነት ፓርቲ አዘጋጅቶት ለነበረው ሰልፍ ቅስቀሳ ውቅት ታስረው የነበሩ ናቸው ።የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአብዛኛዎቹ እንቅስቃሴው ባተኮረባቸው አካባቢዎች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የአንድነት አባላት ላይ ቅስቀሳ አድርጋችኋል በራሪ ወረቀት አሰራጭታችኋል በሚል የእስር፤ ዛቻ፤ ማስፈራራት፤ ድብደባ እና መሰል የመብት ጥሰቶች በብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ሠራተኞች፤ በፀጥታ ኃይሎች እንዲሁም በኢህአዴግ አባላት በተለይ በባለስልጣናት፤ ካድሬዎች፤ ሊግና ፎረም አደረጃጀቶች ተፈጽሞባቸዋል አሁንም ሂደቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ ሲ ል ፓርቲው የ አውሮፓ ተወካይ ና ሌሎች ጉዳዩ የሚያሳስባቸው አካላት በተገኙበት የቀረበው ሰባዊ መብት ጥሰት ሪፖርት ያስረዳል
በሰሜን ጎንደር ምዕራብ አርማጭሆ አብርሃጅራ ከተማ
1. አቶ አለልኝ አቦሀይ — ከሰኔ 22/2005— ሀምሌ 19/2005 ዓ.ም ጀምሮ
2. አቶ እንግዳው ዳኘው — ከሰኔ 22/2005 — ሀምሌ 19/2005 ዓ.ም ጀምሮ
3. አቶ አብርሃም ልጅአለም– ከሰኔ 22/2005 – ሀምሌ 19/2005 ዓ.ም ጀምሮ
4. አቶ አንጋው ተገኝ—– ከሰኔ 22/2005 — ሀምሌ 19/2005 ዓ.ም ጀምሮ
ለዛን ጊዜ መረጃው ይህን ሊንክ ይመልከቱ
No comments:
Post a Comment