የሱዳን መንግስት ተግባር እየተፈፀመ ያለው በምንሊክና በእንግሊዝ መንግስታት ድንበር ብለው ከከለሉት ቦታ 60 ኪሎሜትር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ገብቶ የሚገኝ ንጉዲ ከሚባል የኢትዮጵያ ሉኣላዊ ግዛት እንደሆነ የሑመራ ኑዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ በእንግሊዝና ምንሊክ ግዜ እንደ ተፈጥሮኣዊ ድንበር ተደርጎ የነበረው ቦታ ባህረ ሰላም የተባለ ሃይቅ እንደሆነ የገለፁት ኑዋሪዎቹ ኣሁን የሱዳን መንግስት ግዛቴ ነው ልቀቁልኝ እያለ ያለው ከድንበሩ ወደ ኢትዮጵያ 60 ኪሎሜትር ወደ ውስጥ ገብታ ከምትገኝ ንጉዲ የተባለች መንደር ኑዋሪ የሆኑት ኢትዪጵያውያንን ነው፡፡
ከቅርብ ኣመታት ወዲህ የሱዳን መንግስት ከባህረ ሰላም ወደ ውስጥ እየገባ ለእርሻ ልማት የሚውሉ ግድቦች እየገነባ እንዳለና የኢትዮጵያ መንግስት የሃገራችን መሬት እየተወረረ እያየ እነዳላየ መሆን ከማስገረም ኣልፎ እንዳበሳጫቸው ይገልፃሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰሙኑን ሰለ ኢትዮ- ሱዳን የድንበር ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ምንም የተፈጠረ ኣዲስ ነገር እንደሌለ መግለፃቸው በመንግስት የነበራቸው እምነት እንዲጠራጠሩ ማድረጉን ያብራራሉ፡፡
ከሑመራ ገዳሪፍ የሚወስደው የኣስፋልት መንገድ ግንባታ ኢትዮጵያ እንድታቆም በሱዳን የኣካባቢው ኣስተዳዳሪዎች ጠይቀው ስራው ቆሞ እንደነበርም ያክላሉ፡፡ የኢትዮጵያና የሱዳን መንግስታት በድንበር ጉዳይ በድብቅ ተደራድረው ሱዳን ከ30 እስከ 60 ኪሎሜትር ከኢትዮጵያ መሬት እንደተሰጣት ሲገለፅ መኖሩ የሚታወስ ነው፡፡
ዓረና ከሑመራና ኣከባቢዋ ኑዋሪ ህዝብ ውይይት ለማድረግ በጠራው ህዝባዊ ስብሰባ ህዝቡ በጉጉት ጠብቆ እንደነበር፣ የድንበር ጉዳዩ መፍትሄ እንዲያገኝ ተፅእኖ ያደርጋል ብለው ተስፋ ሲያደርጉ መንግስት ስብሰባው እንዳይካሄድ መደረጉ እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል፡፡ ይህ የተደረገውም መንግስት የህዝቡ መነሳሳት ኣይቶ እንደ ሆነ ብቁጭት ይገልፃሉ፡፡
እነዚህ ከመኖርያ ቤታቸውና ከሃገራቸው በባእድ ሃገር መንግስት ሊፈናቀሉ ቀነ ገደብ የተሰጣቸው ዜጎች ሳይንገላቱና ሳይፈናቀሉ ልንደርሰላቸው ይገባል፡፡
እንደነ ኣፄ ዮውሃንስ የመሰሉ ሃገር ወዳድ ዜጎች ውድ ሂወታቸው የሰዉለት ዳር ድንበር ለማስከበር መላ ኢትዮጵያዊ በኣንድነት መነሳት የግድ ይለናል፡
No comments:
Post a Comment