Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, February 14, 2014

የጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ መቱ


የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታክሲ ሹፌሮች አድማውን የመቱት አዲሱን የትራፊክ የቅጣት ደንብ በመቃወም ነው።
በከተማው መሃል ላይ አሽከርካሪዎቹ ተሰብስበው የመኪና ጥሩምባ ማጮሃቸውን የገለጸው የኢሳት ወኪል፣ ከሰአዓታት በሁዋላ ታክሲዎቹ ከአደባባይ ላይ በመሰወራቸው ነዋሪዎች ታክሲዎችን ለማግኘት ሲቸገሩ ታይቷል።
የገዢው ፓርቲ ሰዎችና ትራፊኮች፣ በመንገድ ላይ ያገኙትን ታክሲ በማስገደድ ሰዎችን እንዲጭን ለማድረግ ሞክረዋል። ፈቀደኛ ያለሆኑ ሾፌሮች ጥያቄዎች ይቀርቡላቸው ነበር። አዳመው ለምን ያክል ቀናት እንደሚቆይ ግልጽ የሆነ ነገር የለም።
በሌላ በኩል በነዳጅ ምርቶች ላይ ሰሞኑን የተጣለው እጅግ ከፍተኛ ጭማሪ በቋፍ ላይ የሚገኘውን የህብረተሰቡን ኑሮ ይበልጥ አስከፊ እንዳደረገው የኢሳት የ አዲስ አበባ ሪፖርተር ዘግቧል።
በቤንዚን ምርቶች ላይ በ አንድ ሊትር እስከ 45 ሳንቲም፣ ለማገዶነት በሚውለው በኬሮሲን ምርት ላይ በ አንድ ሊትር እስከ 75 ሳንቲም የተጣለው የሰሞኑ ይፋዊ ያልሆነጭማሪ፣ በነዳጅ ጭማሪ ታሪክ እጅግ አስደንጋጭና ከፍተኛ ጭማሪ እንደሆነ ነዋሪዎች በምሬት እየተናገሩ ነው። የታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት ከ0.5 ሳንቲም እስከ 0.15 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጎበታል፡፡
ሀቁ ይህ በሆነበት ሁኔታ የመንግስትና የድርጅት ሚዲያዎች አስደንጋጩን የነዳጅ ጭማሪ “መጠነኛ ጭማሪ” እያሉ ሲያወሩ መሰማታቸው፤ በህብረተሰቡ ቁስል ላይ ተጨማሪ እንጨት እንደመስደድ ነው ይላሉ ነዋሪዎቹ።
http://ethsat.com/amharic/

No comments:

Post a Comment

wanted officials