Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 25, 2014

የመስጊድ ኢማሞች የሚሾሙት በመንግስት በራሱ መሆኑን መንግስት አመነ!!! government's too much interferance against religion.

The Ethiopian government interfers with religons against thier constitution.The court paper attached here with is the evidence that  cadre mosque imams are assigned by the government.It states "why the muslims in custody didnot solat/pray respecting the recite of the Cadre muslim imam that is assigned by the government"
There are many muslims in jail in Ethiopia specailly since 2 years becuase the muslims revolt they dont like government cadres assigned to lead them.
መንግስት ‹‹እኔ በሾምኳቸው የመስጊድ ኢማሞች (አሰጋጆች) አልሰገዳችሁም›› በሚል ንጹሀን ሙስሊም ግለሰቦች ላይ ክስ ያቀረበበት ሰነድ ተገኘ!!!
ከፍርድ ቤት የውስጥ ምንጮቻችን የተገኘውና በፌደራል አቃቤ ህግ አቶ ብርሀን አለባቸው ፊርማ በታህሳስ 4/2006 የተጻፈው ይኸው የክስ ሰነድ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ የቀረበ ሲሆን ሁለት መስጂድ ውስጥ በኢማምነት ያሰገዱ ሙስሊም ግለሰቦችንም ተከሳሽ አድርጎ አቅርቧል፡፡
ሰነዱ እጅግ አስገራሚውን ክስ ሲያብራራ አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሽ በቁባ መስጂድ የአህባሽ ተከታዩን ኢማም ተከትሎ ለመስገድ ፍቃደኛ ያልሆነውን ህዝበ ሙስሊም ማሰገዳቸውንና በዚህ ተግባራቸውም ‹‹የሃይማኖት ሰላም ስሜት›› መንካታቸውን ገልጿል፡፡ ቃል በቃልም ሁለተኛ ተከሳሽ ‹‹መንግስት በሾመው ኢማም ቦታ ላይ በመቆም ሳይፈቀድለት የእነሱን ተከታዮች በማሰገድ ሰላማዊው ሙስሊም እንዳይሰግድ በማድረግ…›› ወንጀል መስራቱን ገልጿል፡፡
እስካሁን ‹‹መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገ መንግስታዊ መርህ አልጣስኩም›› እያለ ሲከራከር የቆየው መንግስት በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲጋለጥ የቆየ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን መከራከሩ እንደማያዋጣው አውቆ በማን አለብኝነት ‹‹እኔ የሾምኩትን ኢማም አልተከተላችሁም›› በሚል ፍርድ ቤት ችሎት ማሰየም መጀመሩ ‹‹ህገ መንግስቱ አንድ ቀን ይከበር ይሆናል›› ለሚሉ ወገኖች ትልቅ መርዶ ይዞ መጥቷል፡፡
Source : Zehabesha news

No comments:

Post a Comment

wanted officials