Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, October 29, 2017

አፈወርቅ ተክሌ እና “ቪላ አልፋ”


አፈወርቅ ተክሌ እና “ቪላ አልፋ”



የ“ቪላ አልፋ” አዲሱ መልክ

ከበዓሉ ግርማ

(1961 ዓ.ም)

.

[በደራሲው ቤተሰብ መልካም ፈቃድ ለአንድምታ የቀረበ]

.

አዲስ አበባ ውስጥ የተደረገውን፣ በመደረግ ላይ ያለውንና ወደፊት የሚደረገውን ሁሉ እንደመጠጥ ብርጭቆ አንስተው የማስቀመጥ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ከተሜዎች አሉ። ሰሞኑንም ከሰላምታ በኋላ አርዕስተ ነገር አድርገው የያዙት ትችት ቢኖር ስለ አፈወርቅ ተክሌ (ወልደ ነጐድጓድ) አዲሱ የቪላ አልፋ መልክ ነው።

ትችቱ እንደተቺዎቹ የበዛ ቢሆንም አንዳንዶቹ፣

“ተርፎት፣ የሚሠራውን ቢያጣ ለመመጻደቅ ያደረገው ነገር ነው” ይላሉ።

ሌሎች ደግሞ (በተለይ የፍሮይድን ሳይኮሎጂ ከእጅ ጣታቸው እንደዋዛ የሚያንቆረቁሩት ተቺዎች) የዚህን ዓለም ጉዳይ ወደጎን ብለው፣

“አፈወርቅ ከአካባቢው ውጭ ወይም በላይ ሆኖ በራሱ የፈጠራ ዓለም ውስጥ ለመኖር የሚጥር ሰው በመሆኑ ነው እንዲህ ያለውን ቪላ የሠራው” በማለት ይናገራሉ።

“ግላዊ ልዩነቱን ለመግለጽ ያደረገው ነገር ነው” የሚሉም አሉ።

ያም ሆነ ይህ የነቀፌታዎቹ መነሾ ሠዓሊው አፈወርቅ ቪላ በመሥራቱ አይደለም። ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎችን የገነቡት በሰው አፍ አልገቡም። በግል መኖሪያቸው የሰማኒያና የመቶ ሺህ ብር ዘመናይ ቪላዎችን የሠሩት ዓይን አልበላቸውም።

“ታዲያ የአፈወርቅ ስም እንደ ትኩስ ድንች እያንዳንዱ አፍ ውስጥ የሚገላበጥበት ምክንያት ምን ይሆን?” ብለን ብንጠይቅ መልሱ ሌላ ሆኖ እናገኘዋለን።

ጐንደር የሚገኘውን የአፄ ፋሲልን ግንብ የሚመስል ባለአንድ ፎቅ መኖሪያ ቤት ባለንበት ክፍለ ዘመን በመሥራቱ ነው ልዩው ነገር። ሌላ ሰው ቢያስብም ሥራ ላይ የማያውለውን ነገር አፈወርቅ ግን በመሥራቱ ነው።

የዚህ አይነት ቤት (ወይም ካስል) በመሥራት አፈወርቅ በዘመናችን የመጀመሪያውና የመጨረሻው ሰው ሳይሆን አይቀርም። ምክንያቱም ቤቱን የቀየሰው መሐንዲስ G. Boscarino እንዳለው፤

“እንዲህ ያለው ቤት ውስጥ ከአፈወርቅ በስተቀር ሌላ ሰው ቢኖርበት፣ ቤቱ አሁን ያለውን ዋጋና ጥቅም ሊሰጥ አይችልም”።

አዎን፣ ከአፈወርቅ በስተቀር እንዲህ የመሰለውን ቤት አልሞ የሚሰራ የለም። የሚሰጠውን ጥቅምም በይበልጥ የሚያውቀው እሱው ብቻ ነው።

እንዲህ የመሰለውን መኖሪያ ቤት ለመሥራት ምን እንዳሳሰበው፣ ከተሰራ በኋላ የሚሰጠውንም ጥቅም እንዲነግረኝ ጠይቄው ነበር። ለማናገር ፈቃደኛ ቢሆንም ጊዜ አልነበረውም።



አናጢዎቹ በየደቂቃው ይጠሩታል።

በተመለሰ ቁጥር “የአገራችን አናጢዎች ለምን አንድ መስመር በትክክል ለመሥራት አይችሉም?” በማለት ይገረም ነበር።

እነሱም በበኩላቸው እሱ አሁን በቅርብ ጊዜ የሠራውን የእንሥራ ተሸካሚ ሥዕል፤ በተለይ ወተት መስሎ በጃኖ ጥለት የታጠረውን ቀሚሷን፣ አለንጋ የመሳሰሉትን ጣቶቿንና ሕልም መሳይ ውበቷን አይተው መገረማቸው አልቀረም።

ገና ተመልሶ ቁጭ ከማለቱም ቀለም ቀቢዎች ይጠሩታል።

አዎን፣ “የሰሜን ተራራ” የተባለውን ሥዕል (ኅብረ ቀለሙ ልብ መስጦ፣ ዓይን ማርኮ፣ የአእምሮ ሰላም የሚፈጥረውን) የሠራ ሰው ለተራ ቀለም ቀቢዎች ችሎታ ልዩ አድናቆት ሊኖረው አይችልም።

አሁንስ አፈወርቅን የሚጠራው ሰው የለም ብዬ በመተማመን ጥያቄዬን ወርውሬ፣ ብዕሬን ከወረቀት ለማገናኘት ስቃጣ፣ አንድ ጽጌረዳ አበባ የት እንደሚተክሉ የቸገራቸው፣ ወይም አበባ የያዘውን ሳጥን የት እንደሚያስቀምጡ ግራ የገባቸው ለምክር ይጠሩታል። ሳያማክሩት ያስቀመጡት፣ ወይም የተከሉት እንደሆነ ኋላ ማንሳታቸው አይቀርም።

አፈወርቅ ደጋግሞ እንደሚለው፣

“ማንኛውም ነገር ከተፈጥሮ ጋር በመዋሀድ በኅብረ ቀለሙና በአቀማመጥ አቅዱ ለአእምሮ ዕረፍትና ሰላምን ካልሰጠ አእምሯችን ወደ ከፍተኛ ደረጃ የሚመራ ነገር የመፍጠር ችሎታ ሊኖረው አይችልም። ከተፈጥሮ ኅብረት ጋር ሥራችንንና ኑሯችንን ለማስተባበር ካልሞከርን ውበትን ለመፍጠር አንችልም። ለኔ ከፍተኛው ምኞቴ ይህ ነው – ኅብረት ከተፈጥሮ ጋር። ይህንን ከፍተኛ ምኞት ለመግለፅ የምፈልገው በምሠራቸው ሥዕሎች ብቻ ሳይሆን በአኗኗሬም ጭምር ነው”።

ሠራተኞቹም ደከሙ። ከአንድ ሰዓት ጀምሮ ያራውጣቸው ነበር።

ጥሪው እያነሰ ሄደ። ቁጭ ለማለት ቻልን።

“ይህን ቤት መሥራት ከጀመርኩ ወዲህ የተማርኩት ነገር ቢኖር የቤት ሥራ ምን ያህል ብስጭትና ድካም እንደሚያስከትል ለማወቅ መቻሌን ነው። ወደ ሰላማዊው የሥዕል ሥራዬ የምመለስበት ጊዜ በመቃረቡ ደስ ይለኛል” አለና እግሩን ዘርግቶ ወለሉ ላይ ዘፍ አለ።

በሁለት ወር ያልቃል ተብሎ የታሰበው ቤት አሁን አራተኛ ወሩን ሊጨርስ ነው። በአራት ወር ውስጥ አፈወርቅ ሦስት ሥዕሎች ብቻ ነበር ለመሥራት የቻለው። የቀረውን ጊዜ ያዋለው በቤቱ ሥራ ላይ ነበር።

“ቪላ አልፋ” የተሠራው በአሥር ዓመት ፕላን መሠረት ሲሆን ቤቱን ለመሥራት አፈወርቅ ከሚሸጣቸው ሥዕሎች ዋጋ አንድ ሦስተኛውን ለዚህ ፕላን ቆጥቦ ነበር። ሆኖም የቆጠበው ገንዘብ ስላልበቃው የአዲስ አበባ ባንክ ብድር ሰጥቶታል።

ይሁንና በኔ በጠያቂው በኩል ሃያ ስድስት በሃያ ስድስት ሜትር ካሬ መሬት ላይ የተሠራው አዲሱ ቤት ይህን ያህል የሚያስደንቅ ወጭ የሚጠይቅ መስሎ አልታየኝም። አፈወርቅም ስንት ገንዘብ እንደጨረሰ ትክክለኛ ዋጋውን ሊገልጽልኝ አልፈቀደም።

ቤቱን የአፄ ፋሲልን ግንብ አስመስሎ ለመስራት ያነሳሳውን ነገር ሲገልጽልኝ እንዲህ አለ፣

“ስለ አፄ ፋሲል ግንብ ያለኝን አድናቆት ለመግለጽና ይህ የጥንት ቅርሳችን ተሻሽሎ ለዘመናይ ኑሮ ለመዋል መቻሉን ለማሳወቅ ነው። አዎን የኮራና የከበረ ቅርስ እያለን የቤት ፕላን ከውጭ የምንቀዳበት ምክንያት አይታየኝም።”

አፈወርቅ ለሚሠራው ነገር ሁሉ ምክንያት አለው።

በቤቱ ውስጥ ያለ ምክንያት የሚደረግ ነገር የለም። የአበባ ማስቀመጫው እሱ በፈለገበት ቦታ እንዲኖር የተደረገው ያለ ምክንያት አይደለም። የቤቱ ቆርቆሮ ቀይ ቀለም የተቀባበት ምክንያት አለው። ቤቱ ነጭ ቀለም የተቀባበት ምክንያት አለው።

አንድ ሥዕል አንድ ግድግዳ ላይ በአንድ በኩል እንዲሰቀል የተደረገበት ያለ ምክንያት አይደለም። ቤቱ የተሠራው ለመኖሪያ ብቻ ሳይሆን ሌላ ምክንያት አለው። ቤቱም ቀለሙም አቀማመጡም – ሁሉም ባንድነት ተዋህደው ኅብረት መፍጠር አለባቸው።

“ይህን የመሰለ ቤት የሠራሁበት ምክንያት አለኝ። የሠራኋቸው ሥዕሎች በተሠሩበት አካባቢ እንዲታዩ ለማድረግ ሲሆን፣ እንዲሁም እንግሊዝ ሀገር ተማሪ ሳለሁና በታላላቅ አውሮፓ ከተማዎች እየተዘዋወርኩ ሥዕል በምሠራበት ወቅት፣ ብዙ ሠዓሊዎች ቤታቸው ይጋብዙኝ ነበር።”

“አሁንም በተራዬ እዚህ በመጋበዝ አንድ ኢትዮጵያዊ ሠዓሊ እንዴት እንደሚኖር ለማሳየትና ከዚህም አልፎ ከሀገራችን የታሪክ ቅርስ ጋር ለማስተዋወቅ ነው። እንግዶቼ በውብ ነገር ተከበው ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ ከማድረግ ሌላ የዕለት ኑሮዬን እንዴት እንደማሳልፍ እንዲያውቁም ጭምር ነው።”

“ከዚህ ቀደም ቤቴ በግንብ አጥር ተከቦ ታፍኜ ስኖር ነበር። አሁን ግን የቤቱ ሰገነት ወደ ውጭና ወደ እሩቅ ለመመልከት ያስችለኛል። ሰገነቱ ላይ ወጥቼ የአዲስ አበባ ተራራዎችን ለማየት እችላለሁ። ላንድ ሠዓሊ እንዲህ ያለው የመዝናናት ትዕይንት ጠቃሚው ነው።”

አዎን፣ ያለ ምክንያት የተደረገ ነገር የለም።

ቤቱ አንድ ሺህ ሜትር ካሬ ላይ መሠራቱ ምክንያት አለው። የመሬት ቁጠባን ለማስተማር ነው።

ሦስቱ መስኮቶች ሦስት አይነት ቀለማት የተቀቡበት ምክንያት አለው። የፀሐይዋን ዕለታዊ ጉዞ ተከትለው እንዲያንጸባርቁ ለማድረግ ነው።

የቤቱ ክፍሎች አቀያየስ ምክንያት አላቸው። ሃምሳ አራት ሥዕሎች ባንድ ጊዜ ለማሳየት እንዲቻል ታስቦ የተደረገ ነገር ነው። እንዲሁም እያንዳንዱ ክፍል ከየጠቅላይ ግዛቶች የሚገኙትን ጌጣጌጦች ማሳያ ሊሆን ይችላል።

የጸሎት ወይም የሀሳብ ማጠንጠኛ ክፍሉ የአክሱም ጽዮንን መልክ የያዘ ነው።

የምሥጢር በሩ ያለ ምክንያት አልተሠራም። አፈወርቅ ካንዱ ክፍል ወደ ሌላ ሳይታይ ለመዘዋወር እንዲችል ነው።

የጋራጁም ስፋትና ቀለም ያለ ምክንያት አልተደረገም። ሁለት መኪናዎች እንዲይዝ ከመሆኑም በላይ የጋራጁ ቀለም ከመኪናዎቹ ቀለም ጋር ተዋህዶ ኅብረትን ለመፍጠር እንዲችል ታስቦ ነው።

አዎን፣ በአፈወርቅ ቤት ያለ ምክንያት የተደረገ ነገር የለም።

በዓሉ ግርማ

በዓሉ ግርማ ፋውንዴሽን መልካም ፈቃድ ለአንድምታ የቀረበ

.

[ምንጭ] – መነን (ሚያዝያ ፳፱፣ ፲፱፻፷፩)፤ ገጽ ፲፮-፲፯።

አሞራ … የዳዊት አሞራ” (ግጥም)

https://andemta.com/

አሞራ … የዳዊት አሞራ” (ግጥም)


“አሞራ … የዳዊት አሞራ”

በዣን ተኵላ

.
[1400 ዓ.ም]
.
Dawit 1
Dawit 2
Dawit 3
Dawit 4
Dawit 5
Dawit 6
.
.

በዘመናችን አማርኛ …

(ትርጉምና አሰናኝ)
በዕውቀቱ ሥዩም
.
.
“አሞራ የዳዊት አሞራ
ተከተለኝ ከኋላ፤
.
ላቅርብልህ ሥጋ ብላ
ላጠጣህ ወይ ደም መራራ
ተከተለኝ እኔ ልምራ፤
.
እየመተርሁ በካራ
እየወጋሁ በጦር ጣምራ።
.
ብንበላብህ አደራ
በገላችን ጦር ይዘራ፤
ክንፍ አውጥተን ብንሸሽም
ቀስትህ ትውጋን ተወርውራ።
.
ምንም ሆድ ቢብሰን እኛ አንበላም መሐላ
ገላችን ይምሰል እንጂ የፈጠጋር አምባራ
አፋችን ይምሰል እንጂ ባልቴት ምትሞቀው እንሶስላ
ጣታችንም ይምሰል ጭራ የጎረሰ ደም አበላ፤
.
ጭፍሮች ነነ የዣን ተኵላ
እኛስ አንበላም መሐላ!”
.
.
.

[በ1400ዎቹ አማርኛ በድጋሚ]

.
“አሞራ የዳዊት አሞራ
ተኸተለኝ በኋላ፤
.
ሥጋ አበላኽ ሐበላ (ከበላ)
የደም አጠጣኽ ነተራ (መራራ)
ተኸተለኝ በኋላ፤
.
ወግዕቼ በቃራ (በካራ)
ሰኽቼ በጸመራ። (በጣምራ)
.
እኛስ ብንበልዓኽ መሐላ
ለጾር ይስጠን ለወርወራ፤ (ውርወራ)
የከንፍ ብናደርግ ጽላ
ለቀስት ይስጠን ለቀፈራ። (ለወጠራ)
.
ምን ከበአሰን ንበልአኹ መሐላ (እንበላለን)
ገላችን ከመሰል የፈጠጋር እምብላ (አምባር)
አፈችን ከመሰል በዓልቴት የገባች እንሶስላ
ፀዓታችን የመሰል በደም የዘራ ጭራ (ጣታችን)
.
ስማችን የዣን ተኵላ
አንበልዓም መሐላ። (አንበላም)
.

የዣን ተኩላ

[ከአፄ ዳዊት ሠራዊቶች የአንዱ ስም]


አዲስ አበባን የለዉጥ ማዕከል እናድርግ -የአማራና የኦሮሞ ወጣቶች የተላከ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ-ታህሳስ 10 / 2010 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከሚኖሩ የአማራና የኦሮሞ ወጣቶች የተላከ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ !! 
[ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሼር ያድርግ]
እኛ በርዕሰ ከተማ በአዲስ አበባ የምንኖር የአማራና የኦሮሞ ወጣቶች ለበርካታ ወራት በህቡዕ በመደራጀት ወያኔን በምን መንገድ መቃወም እንዳለብን እየተገናኘን ስንነጋገር ቆይተናል ፡፡ በስተመጨረሻም ወያኔን በህዝባዊ ተቃዉሞ ለመታገል በመወሰን ለታህሳስ 10 / 2010 ዓ.ም ከጧቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ ታላቅ ህዝባዊ አመፅና የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ወስነናል ፡፡
በመሆኑም በወያኔ መንግስት ግፍና በደል የደረሰበት ማንኛዉም የአዲስ አበባ ነዋሪ ከላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት በመስቀል አደባባይ እንዲገኝ የእናት ሃገር አድን ጥሪያችንን ከወዲሁ እናስተላልፋለን ፡፡
በመሆኑም ነጋዴዉ ፣ ተማሪዉ ፣ አስተማሪዉ ፣ የመንግስት ሰራተኛን ጨምሮ በአጠቃላይ ሁሉም የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ወጣት መልዕክታችንን ሼር ያድርግ ዘንድ እንጠይቃለን ፡፡
አንድነት ሃይል ነዉ !
የህዝብ ትግል ያሸንፋል !
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
Image may contain: text

Monday, October 23, 2017

American woman becomes a princess after marrying Ethiopian prince she met in nightclub





Ariana Austin marries Joel Makonnen at lavish Orthodox Christian wedding with 13 priests
Tom Embury-Dennis
Independent

Fairytales are not known for beginning in a Washington DC nightclub, but for one American woman it was where she met the Ethiopian prince who would go on to become her husband.

Ariana Austin, now 33, was on a night out with a friend when they were approached by Joel Makonnen in the Pearl nightclub.

“I said: ‘You guys look like an ad for Bombay Sapphire’,” he told The New York Times about their first encounter.
“Not even five minutes later I said: ‘You’re going to be my girlfriend’.”

What he didn’t reveal that night 12-years ago, was that plain old Joel was actually Prince Joel, the great-grandson of Haile Selassie I, Ethiopia’s last emperor.

But after the couple started dating seriously, Mr Makonnen, who works as a lawyer, eventually revealed his royal heritage

Sunday, October 22, 2017

Ethiopia, Sudan and Egypt discuss divergences over dam construction


Water ministers of Ethiopia, Sudan and Egypt Wednesday discussed in Addis Ababa, ways to address the outstanding issues after a study done by consultancy firms over the Renaissance Dam filling period.

The planned Grand Ethiopian Renaissance Dam project (AP)
Egypt, actually, still fears that the power production of the High Aswan Dam be affected by the reduction of water volume in Lake Nasser when begins the filling of the GERD which is expected to hold 74 billion cubic metres of water.
Ethiopia sought to dissipate Egyptian concerns over its share of water by repeating they only want to produce power and they have no intention to use water or to divert to other projects pointing to its location at 17 km from the Sudanese border.
During the meeting, the ministers addressed reservations raised particularly from Cairo after the International Panel of Expert’s (IPoE) submitted its recommended studies to governments of the three countries.
The water ministers concluded their discussions by drafting guidelines to be provided to the consultancy firms on ways how to move forward on the pending issues.
Prior to the meeting, ministers of the three countries paid a visit to the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) which the horn of Africa’s nation is building along the Nile River near the Sudanese border.
“The visit to the dam project is in a bid to further boost the level of existing transparency and in turn uplift, the confidence among the three countries with regard to the Dam,” said the office of Spokesperson of the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia.
According to the Ethiopian Foreign Ministry, Addis Ababa’s leading role in the establishment of IpoE is stemmed from its desire to strengthen its relationship with the lower riparian countries and build trust among the countries.
The two studies will be conducted as per the agreements reached by the three countries with the two French firms as well as based on the Declaration of Principles signed by leaders of the three countries.
In 2011, Ethiopia launched the construction of grand Renaissance dam and hence Egypt has demanded the halt of the project arguing the hydro-power dam will eventually diminish its historic water shares from the Nile river.
Currently, the $ 4.8 billion dam project is 60 % complete.
(ST)

Saturday, October 21, 2017

አቶ በረከት ስምኦን ከስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን መንግስት አመነ

አቶ በረከት ስምኦን

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 7/2010) አቶ በረከት ስምኦን ከስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን መንግስት ማረጋገጫ ሰጠ።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ስለ አቶ በረከት ከስልጣን የመልቀቅ ጥያቄ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ የምናውቀው ነገር የለም ብለው ነበር።
ነገር ግን ከአንድ ቀን በኋላ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ አቶ በረከት የመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን ለመንግስትና ለፓርቲ መገናኛ ብዙሃን አረጋግጠዋል።
ከሳምንት በፊት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበርነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ ከያዙት መንግስታዊ ስልጣናቸው ሃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት አቶ በረከት ስምኦን የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል በተባለው ተቋም በአቶ አባይ ጸሐዬ ስር በምክትል ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ እንደነበርም ታውቋል።
መልቀቂያም ያቀረቡት ከዚህ ሃላፊነታቸው ለመነሳት እንደሆነም መረዳት ተችሏል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 7/2010 ለፓርቲና ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንዳረጋገጡት አቶ በረከት ስምኦን የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አስገብተዋል።
ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ከአንድ ቀን በፊት ግን ስለ አቶ በረከት ከስልጣን የመልቀቅ ጥያቄ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ የምናውቀው ነገር የለም ብለው ነበር።
መንግስት የቀረበውን የስራ መልቀቂያ እየተመለከተው መሆኑን የገለጹት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊው ዶክተር ነገሬ ሌንጮ አቶ በረከት ስራ ለመልቀቅ ስለፈለጉበት ምክንያት የታወቀ ነገር አለመኖሩንም ጠቁመዋል።
አቶ በረከት ስምኦን በአቶ አባይ ወልዱ ከሚመራውና በጄኔራል ሳሞራ ድጋፍ ከሚደረግለት የሕወሃት አንጃ ጋር ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን ምንጮች ይገልጻሉ።
የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የመቀሌ ስብሰባ ላይ በአቶ ስብሐት የሚመራው አንጃ አባላት በአንጋፋ አመራርነት ስም መጋበዛቸውን ተከትሎ በፓርቲው ውስጥ ያለው የሃይል አሰላለፍ ለአቶ በረከት ከንግድ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢነት መባረር ምክንያት እንደሆነ ይጠቀሳል።
እሳቸውም ቀሪ ቦታዎቻቸውን በፈቃዳቸው መልቀቅ እንደመረጡም ተመልክቷል።
ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አቶ በረከት ስምኦን ስልጣን ለመልቀቅ ስላቀረቡት ጥያቄ ለየትኛውም መገናኛ ብዙሃን መግለጫ አልሰጡም።
እሳቸውም ህዝቤንና ድርጅቴን ብአዴንን ከውርደት ለመጠበቅ ስል ስልጣን ለቀኩ የሚል መግለጫ እንደአባዱላ ይሰጣሉ ተብሎም በመጠበቅ ላይ ነው።

የብሔረሰቦችን ተዋጽኦ መሰረት ያደረገ የስራ ቅጥር እንዲካሄድ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

Bildergebnis für ብሔረሰቦችን

 በፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የብሔረሰቦችን ተዋጽኦ መሰረት ያደረገ የስራ ቅጥር እንዲካሄድ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ።
አዋጁ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ፖልሲን ይቃርናል ተብሏል።
በወረቀት ላይ የሰፈረው ፖሊሲ በሲቪል ሰርቪስ ውስጥ የሚኖር የምልመላና የእድገት ስራ በግለሰቡ ብቃት ላይና በዚሁ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያዛል።
አሁን ለፓርላማው የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ደግሞ ከዚህ በተለየ መልኩ በፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የሚደረገው የስራ ቅጥር የብሔረሰቦችን ተዋጽኦ መሰረት ያደረገ እንዲሆን የሚያስገድድ ነው።
ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ ሊኢሳት አስተያየታቸውን የሰጡ የዘርፉ ሙያተኞች አሁን የቀረበው ህግ የፊዴራል የሲቪል ሰርቪስ ፖሊሲን የሚጥስ እንደሆነ ገልጸዋል።
በወረቀት ላይ ከሰፈረውና በግለሰቡ ብቃት ላይ ተመስርቶ ይካሄድ ከሚለው ፖሊሲ ጋር በፍጹም የማይገናኝ ነው ይላሉ አስተያየት ሰጭዎቹ።
በአሁኑ ሰዓት ይህንን መሰረታዊ መርሆ ለመጣስ የተፈለገው ሲቪል ሰርቪሱን በፖለቲካዊ አቋማቸው የገዢው ፓርቲ አባላት የሆኑትን ለመሙላትና የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆችን ለመጉዳት እንደሆነ አስታውቀዋል።
የብሔረሰቦችን ተዋጽኦ መሰረት ያደረገ የስራ ቅጥር እንዲካሄድ የሚያስገድደው ረቂቅ አዋጅ በሃላፊነት ቦታዎች ስለሚኖረው የብሔረሰብ ስብጥር ግን ያነሳው ነገር የለም።
ረቂቅ አዋጁ ከዚህም ሌላ በሙስናና በአስገድዶ መድፈር ተሳታፊ ሆነው የተገኙና የተፈረደባቸው ግለሰቦች በመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች እንዳይቀጠሩ የሚያስገድድ ሀሳብንም አካቷል ።
በሙስና፣በእምነት ማጉደል፣በስርቆት፣በአስገድዶ መድፈር፣በማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተፈረደበት ግለሰብ በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ እንዳይሰራ የሚከለክለው ይህው ረቂቅ አዋጅ በመንግስት መስሪያ ቤቶች የብሔረሰብ ተዋጽኦን ለማመጣጠን በሚደረገው ሒደት አነስተኛ ውክልና ያላቸውን በልዩ ድጋፍ ቁጥራቸውን ስለመጨመር ይዘረዝራል።
ባለፈው ሳምንት ለፓርላማ የቀረበው ይህው የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ ለሴት ሰራተኞች በወሊድ ጊዜ ይሰጥ የነበረውን የሶስት ወራት ግዜ ወደ አራት ከፍ አድርጓል።



የአርበኞች ግንቦት 7 ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እዝ መቋቋሙን ስለማሳወቅ!

የአርበኞች ግንቦት 7 ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እዝ መቋቋሙን ስለማሳወቅ!
በአሁኑ ሳዓት የጀመርነው የነፃነት ትግል ፍሬዎችን እያፈራ ማየት ጀምረናል፡፡
የምንታገለው አደገኛ ከሆነው ጠላታችን ህወሐትና እንዲሁም ለሆዳቸው ካደሩ ከሀዲና ባንዳዎች ጋር በመሆኑ የትግል ስልቱ እንደየ አካባቢው ይለያያል ማለትም ተለዋዋጭ ይሆናል፡፡
በመሆኑም ላለፋት 8 ወራት አግ7 የሰሜን ዕዝ በርካታ ስራዎችን በከተማ እና በገጠር ሲሰራ እደቆየ እና አሁንም በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት ጠላት በሰሜን ዕዝ ላይ ያለ የሌለ ኃይሉን በመጠቀም ትግሉን ለማኮላሸት እየሰራ ይገኛል፡፡
ባሐፈው ግምገማችን ስርዓቱ (ጠላት) አግ7 የሰሜን ዕዝ የሚለውን በከፍተኛ ደረጃ እደሚሰጋው እና በልዩ አወቃቀር ለማጥፋት ከፍተኛ እቅስቃሴ ሲያደርግ ተስቶውላል፡፡
ስለሆነም አሁን ባለው 2 ተጨባጭ ነጥቦች ማለትም 1፡ የትግሉ እንቅስቃሴ ወደ መሀል መድረሱ 2፡ የሰሜን ዕዝ ብቻውን መቀጠሉ በመሀል እና በአዲስ አበባ ዙሬያ ያሉ አባሎቻችን ሌላ ዕዝ በተጨማሪ እዲቋቋም መጠየቃቸው ታውቃል፡፡
በመሆኑም የትግሉ ደረጃ ከፍ ማለቱና መሀል እና ዙሪያው ያለው እንቅስቃሴ በጥሩ ደረጃ መገኘቱን ገምግመናል በዚህ መነሻ ከዛሬ ጥቅምት 10 /2010 ዓ/ም ጀምሮ "አርበኞች ግንቦት 7 ማዐከላዊ ኢትዮጵያ ዕዝ" በይፋ ተመስርቷል፡፡
ለጊዜው ከልምድና ከትስስር አኳያ እንዲሁም የመሀሉን ትግል እየመሩና እየሰሩ ያሉት የአግ7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ታጋዬችና የድርጅታችን ከፍተኛ አመራሮች በመሆናቸው አመራሩ ለጊዜው በዚህ ይቀጥልና በቀጣይ ጠንካራ አመራሮች ይመደባሉ፡፡
የአግ 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ!

Friday, October 20, 2017

የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ለ2ተኛ ጊዜ ሕገመንግስቱን በመጣስ ተራዘመ


Bildergebnis für የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ
በኢትዮጵያ ዘንድሮ መካሄድ የነበረበት የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ለ2ተኛ ጊዜ ሕገመንግስቱን በመጣስ መራዘሙ ተነገረ።
የሕዝብ ቆጠራው እንዲራዘም የተወሰነው በሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ነው ተብሏል።
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የሕዝብ ቆጠራው እንዲራዘም የተፈለገው ሀገሪቱ ባልተረጋጋችበት ሁኔታ ማካሄዱ ሌላ ቀውስ ይፈጥራል በሚል ነው።
ከሶስት ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተመድቦለት በህዳር 2010 ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ሀገሪቱ ባልተረጋጋችበት ሁኔታ ማካሄድ እንደማይቻልና ህገ መንግስቱን መጣስ አማራጭ የሌለው መሆኑን የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ መወሰኑን የኢሳት የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።
የአመቱን የመንግስትና የድርጅት እቅድ ለማውጣት በመቀሌ ተሰብስቦ የነበረው የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ብአዴን፣ኦህዴድና ደኢሕዴን ያቀረቡትን አስተያየት ከግምት በመውሰድ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ እንዲራዘም መወሰኑ ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የአመቱን የመንግስት ስራዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚያቀርቡበት ሰአት የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ላይ ትኩረት እንዳይሰጡ ትእዛዝ በመተላለፉ ህገ መንግስቱን ለመጣስ መገደዳቸው ተነግሯል።
የኢህአዴግ ህገ መንግስት አንቀጽ 103 ንኡስ አንቀጽ 5 የሕዝብ ቆጠራ በየአስር አመቱ ይካሄዳል ይላል።
የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ መራዘም ቢኖርበት እንኳን የሕገ መንግስት ማሻሻያ እንዲደረግ የሚጠይቅ በመሆኑ ይህ ቅድመ ሁኔታ ሳይሟላ ቆጠራው መራዘሙ መንግስትን እንደሚያስጠይቀው ኢሳት ያናገራቸው የህግ ምሁራን ተናግረዋል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የቀድሞ ፓርላማ አባል ለኢሳት እንደገለጹት ቆጠራው የተራዘመበት ምክንያት ከሙስናና ከሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገልጸዋል።
ለቆጠራው ያስፈልጋሉ ተብለው የተገዙት ከ180 ሺ በላይ ዲጂታል ታብሌቶችና ኮምፒዩተሮች ጋር ተያይዞ የተፈጸመው ሙስና እንዲሁም ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸው የተገዙ ቁሶች ደብዛ መጥፋት ለመራዘሙ ተጨማሪ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬተር አቶ ቢራቱ ይገዙ በሀገር ውስጥ ለሚታተሙ ጋዜጦች ቆጠራው መራዘሙን አረጋግጠዋል።–ቆጠራው የተራዘመበትን ምክንያት ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።
በህወሃት ኢህአዴግ ዘመን የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ከምርጫ ክልል አወሳሰን፣ከበጀት ድጎማ፣ከሃይማኖትና ከብሔረሰቦች ማንነት እንዲሁም ከብዛት ጋር የተያያዘ በመሆኑ የፖለቲካ ውሳኔ እንደሚያርፍበት ይገለጻል።
በቀጣይ የሚካሄደው ቆጠራ ላይ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መሪ ተዋናይ መሆኑ የቆጠራው ውጤት ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሚያርፍበት አመላካች መሆኑ ተገልጿል።

በአሜሪካ በዲሞክራሲና ነጻነት ላይ የሚሰራ ድርጅት ባልደረባ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አሰቡ

Bildergebnis für HR 128

በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በጸረ ሽብርተኝነት አጋርነት ከአሜሪካ ጋር መተባበሩን እንደመደበቂያነት ተጠቅሞ እየፈጸመ ካለው የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲቆጠብ በአሜሪካ በዲሞክራሲና ነጻነት ላይ የሚሰራ ድርጅት ባልደረባ አስታወቁ።
በአሜሪካ ኮንግረስ ተረቆ የሚገኘውን ኤች አር 128 በሚባል የሚታወቀውን ህገ ውሳኔ አሜሪካ በአስቸኳይ ማጽደቅ አለባት ሲሉም ተናግረዋል።
በአሜሪካ በዲሞክራሲና ነጻነት ላይ በሚሰራው ፍሪደም ሀውስ በተባለው ድርጅት ውስጥ የአፍሪካ ፕሮግራም ኦፊሰር የሆኑት ዮሴፍ ባድዋዛ በድርጅቱ የመረጃ መረብ በለቀቁት ጽሑፍ በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የጸረ ሽብር አጋር ስለሆነ ብቻ በተቃዋሚዎቹ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያና እስር አሜሪካ በዝምታ ማለፍ የለባትም።
ኤች አር 128 የተባለውን ሕገ ውሳኔ በአፋጠኝ በማሳለፍ አገዛዙ እየፈጸመ ላለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠያቂ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በገዛ ዜጎቹ ላይ ወንጀል የሚፈጽም እንዲሁም በአገዛዙና በሕዝቡ መካከል ጤናማ ግንኙነት በሌለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ የአሜሪካ የጸጥታ አጋር መሆን አትችልም ብለዋል።
ኤች አር 128 ሕግ የሚወጣ ከሆነ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን የጸረ ሽብር ትብብር ታቋርጣለች በማለት በቅርቡ በአገዛዙ እየተሰጠ ያለውን የውሸት ማስፈራሪያ አሜሪካ ቸል በማለት ጠንካራና የማያወላውል አቋሟን ማሳየት አለባት።
ይህም በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለመጠበቅና እያንዣበበ ያለውን ቀውስ ለመከላከል ወሳኝ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ሲሉ ዮሴፍ ባድዋዛ ጽፈዋል።
ሕጉን በማጽደቅ አሜሪካ ኢትዮጵያ ላለው አገዛዝ ጠንከር ያለ መልዕክት ልታስተላልፍ ትችላለች ሲሉም አስፍረዋል።
የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የጸረ ሽብር ትብብር አቆማለሁ የሚለውን የኢትዮጵያ መንግስትን የውሸት ማስፈራሪያ ወደ ጎን በመተው ሕጉን በአስቸኳይ ማጽደቅ አለባቸው ብለዋል።
በአሜሪካ ኮንግረስ የኮሎራዶ ተወካይ ማይክ ኮፍማን በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውን አምባሳደር ባናገሩበት ወቅት ሕጉ የሚጸድቅ ከሆነ ሀገሪቱ የጸረ ሽብር ትብብሯን ታቋርጣለች እንዳሏቸው በኮሎራዶ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት መናገራቸውን ጽሑፉ አስታውሷል።
ጸሐፊው ሲያጠቃልሉም በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ መቼም ቢሆን እንዲህ አይነቱን ማስፈራሪያ እስከመጨረሻው ገፍቶበት አያውቅም። በጸረ ሽብሩ ላይ ላለመተባበር ቢወስን ማን እንደሚጎዳ ጠንቅቆ ያውቃል ብለዋል።

የራያና የወልዲያ ህዝብም ጣናን ለመታደግ ወደባህርዳር እየተጓዘ ነው።

የራያ ህዝብም ጣናን ለመታደግ ወደባህርዳር እየተጓዘ ነው።የወልዲያ ህዝብ ጣናን ለመታደግ ወደባህርዳር እየተጓዘ ነው፤ የሕወኃት ባሪያ የሆነው ብአዴን አሁንም ተኝቷል
No automatic alt text available.Image may contain: outdoor

በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

Image may contain: car and outdoor

 በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው ተቃውሞ ተባብሶ ቀጥሏል።
ትላንት ምሽት የተጀመረው የገብረጉራቻው አመጽ በርካታ የመንግስት ተሽከርካሪዎችን በእሳት በማቃጠል ተካሂዷል።
ዛሬ በአምቦና በወለጋ ሆሮጉድሩ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት የህወሃት መንግስት ከስልጣን እንዲወርድ ጠይቋል።
ሕዝባዊ ተቃውሞው በተለያዩ አካባቢዎች በመደረግ ላይ ነው።
ከ20 በላይ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለው። በርካታ ቤቶች በእሳት ወድመዋል። ህዝቡ ይህን እርምጃ ሲወስድ በተጠናና በስልጣን ላይ ካለው ስርዓት ጋር ግንኙነት ካላቸው ጋር የተያያዘውንና የመንግስት ታርጋ ያላቸውን እየለየ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ገብረጉራቻ ከትላንት ጀምሮ በህዝባዊ አመጽ ውስጥ ናት። ሙከጡሪ፣ ፍቼን ይዞ ያለው መስመር ጠንካራ የህዝብ ተቃውሞ በመካሄድ ላይ ነው።
ትላንት ገብረጉራቻ ላይ የተቃጠሉት በርካታ ተሽከርካሪዎች የህዝብ ምሬት የደረሰበትን ደረጃ ያሳያል የሚለው አስተያየት ከየአቅጣጫው እየተሰማ ነው። ሰላማዊው ህዝብ እንዳይጎዳ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል የሚሉ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች በስልጣን ላይ ላለው ስርዓት ግልጽ መልዕክት የተላለፈበት እንደሆነም ገልጸዋል።
ዛሬም በአካባቢው ያለው የህዝብ ተቃውሞ እንደቀጠለ ሲሆን ብዛት ያለው የአጋዚ ሰራዊት እንዲገባ መደረጉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በሌላ በኩል የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የህወሀት አገዛዝ እንዲያከትም በመጠየቅ በግቢያቸውና በአምቦ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ተቃውሞ ማድረጋቸው ታውቋል።
በአምቦ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ታስቦ የተጀመረውን ተቃውሞ የከተማው ህዝብ በመቀላቀሉ ወደ አደባባይ ሊወጣ መቻሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በወለጋ ሆሩ ጉድሩም በተመሳሳይ ህዝባዊ ተቃውሞ መካሄዱን የገለጹት የኢሳት ምንጮች የህወሃት መንግስት እንዲወርድና ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል በሰሜን ሸዋ በገብረጉራቻ ሙከጡሪና ፍቼ እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ ኩታ ገጠም በሆኑ የአማራ ክልል ከተሞችና መንደሮች ትኩሳት በመፍጠር ላይ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በሙከጡሪ ከተማ ተገንጥለው ያሉት ቆላማዎቹ ለሚ እና መርሃቤቴ ከተሞች ፣ በጎጃም ደጀን ሉማሜ ከተሞች ህዝባዊ አመፁ ዳር ዳር እያለባቸው እንደሆነ እየተነገረ ነው።
ከአዲስ አበባ ዳርቻ ከሱሉልታ እስከ ጉሃፅዩን ድረስ የተዛመተው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ ጎጃምና ሰሜን ሸዋ እንዳይዛመት በመስጋት የህወሀት አገዛዝ ሰራዊቱን በብዛት ማስፈሩን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
ከኦሮሚያ ክልል ወደ አማራው የሚወስዱ መስመሮች በተቃውሞ ምክንያት በመዘጋታቸው የትራንስፖርት አገልግሎት በአብዛኛው መቋረጡም ታውቋል።

ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ እየተማከሩ ነው




ሰበር ዜና - ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ በቃል ጠየቁ፤ ጫና ለማሳደር የታሰበ ስልት መኾኑ ተጠቆመ

(ሐራ ተዋሕዶ)

• ከሥልጣን የመገለል ስጋት ባይኖራቸውም፣ተገቢነታቸው ብርቱ ጥያቄ እየተነሣበት ነው
• “በአቅም ማነስ ያጡትን ተቀባይነት ለመመለስ፣ ከአማካሪዎቻቸው ጋራ የወጠኑት ነው፤”
• ለብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ምክር የሰጡት ምላሽ፣ ብዙዎችን ቢያሳዝንም ሊያግዷቸውም ዛቱ
• የተወነጀሉት ብፁዕነታቸው፣ በምልአተ ጉባኤ እና በሕግም እንደሚጠይቋቸው ተጠቆመ
• በሀ/ስብከታቸው ተቀባይነት ያጡት ብፁዕ አባ ማርቆስ፣በቦታቸው ለመተካት እየሠሩ ነው
†††


ታማኝነታቸውና መንፈሳዊ አባትነታቸው ተቀባይነት እያጣ መምጣቱ በብርቱ አሳስቧቸዋል የተባሉት ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ “መሥራት አልቻልኩም፤” ሲሉ ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ፣ ለመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በቃል ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ፡፡

ፓትርያርኩ ጥያቄውን ያቀረቡት፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ አውጭና ወሳኝ አካል ከኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ እና ከሥራ አስፈጻሚው የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደራዊ አካል ጋራ ያላቸው ግንኙነት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደገባ እየታየ ባለበት ወቅታዊ ኹኔታ ውስጥ ነው፡፡

“መፍትሔ ሊሰጠኝ ይገባል፤” በማለት በሓላፊነታቸው ለመቀጠል እንደተቸገሩ በቃል ለከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት መናገራቸውንና በቅርቡም በጽሑፍ እንደሚያሳውቁ ነው፣ ምንጮች የጠቆሙት፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የፓትርያርኩ ሢመትና ርደት ጉዳይ የሚወስነው ቅዱስ ሲኖዶስ ኾኖ ሳለ፣ ጥያቄያቸውን ለባለሥልጣናት ማቅረባቸው፣ በቅዱስ ሲኖዶስና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዘንድ በአስከፊ ኹኔታ እያጡ የመጡትን ተደማጭነትና ተቀባይነት በተጽዕኖ ለመመለስ፣ ከአማካሪዎቻቸው ጋራ የወጠኑት መኾኑን እንደሚያሳይ ተነግሯል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶሱ፣ የመጀመሪያ ዓመታዊ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ፣ ከነገ በስቲያ፣ ጥቅምት 12 ቀን እንደሚጀመር እያወቁ፣ ከሓላፊነት ለመልቀቅ ጠይቀዋል መባሉ ይህንኑ ጫና የማሳደር ስልታዊነቱን እንደሚያረጋግጥ ነው የተገለጸው፡፡

ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ በተያያዘ የሚያቀርቡት የእግድ አጀንዳ በቅዱስ ሲኖዶሱ አካላት(ቋሚ ሲኖዶስ እና ምልአተ ጉባኤ) ውድቅ መደረጉ፤ ቡድን ፈጥረው እየመከሩ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ የሚያስተላልፉት መመሪያ መሸራረፉ ሕመም እንደኾነባቸው ነው የተስተዋለው፡፡

የማኅበሩ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ሥርጭት ከቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ ውጭ እንዲታገድ ያስተላለፉት መመሪያ ተፈጻሚነት ሲያጣ፣ ከአጠቃላይ ጉባኤው 36ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ተሳትፎ እንዲታገድ ወደ ማዘዝ ቢሸጋገሩም እንዳሰቡት ሳይሳካላቸው ቀርቶ፣ በተፃራሪው የማኅበሩ የማዕከልና የአህጉረ ስብከት ሥራዎች በጉልሕ እንዲስተጋቡ ምክንያት ኾኗል፡፡

በአጠቃላይ ጉባኤው መክፈቻ ምሽት፣ የማኅበሩ ተወካዮች እንዳይሳተፉ በማድረጋቸው፣ “የእኛን ሥልጣን ማወቅ አለባቸው፤ ሥልጣናችንን መረዳት አለባቸው፤” በማለት ከእነብፁዕ አባ ሩፋኤል፣ ብፁዕ አባ ማርቆስ እና ብፁዕ አባ ቶማስ ጋራ ውሎውን የገመገሙ ቢኾንም፤ በቀጣዩም ቀን ማኅበሩ ከአህጉረ ስብከት ጋራ በመቀናጀት ያከናወናቸው ተግባራት በድምቀት እየተነገሩ በመዋላቸው፣ በጋራ መግለጫና ቃለ ጉባኤው ላይ፣ ቴሌቭዥኑ ሕገ ወጥ እንደኾነና እንዲዘጋ የሚጠይቅ አንቀጽ በጣልቃ እንዲገባ አርቃቂዎቹን አዘዋል፡፡ ሐሳቡን የተቃወሙ የአርቃቂ ኮሚቴው ሦስት አባላት፣ “የማኅበር ተላላኪዎች” ተብለው በሰብሳቢው የተዘለፉ ሲኾን፣ ሥርዋጹም በግድ እንዲገባና በድፍረት እንዲነበብ ተደርጓል፡፡

በአጠቃላይ ጉባኤው ያልተነሣ ጉዳይ በቃለ ጉባኤ የውሳኔ ሐሳብ ተብሎ መስፈሩ አግባብነት እንደሌለው ወዲያውኑ ከጉባኤተኛው ተቃውሞ የተሰማበትና በምክትል ሰብሳቢው ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁም ተቃውሞ ቢሰነዘርበትም፣ ርእሰ መንበር የኾኑት ፓትርያርኩ ግን ሕገ ወጥነቱን የተከላከሉት፡፡ “የመዝጊያ ንግግር እንዳደርግ ስለ ፈቀዱልኝ አመሰግናለሁ፤” በማለት ስሕተቶችን በፍጥነት እያረሙ የአጠቃላይ ጉባኤውን ሒደት በጥብቅ እየተቆጣጠሩ ምክራቸውን ያፈረሱባቸውን ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን፣ በማጠቃለያ ቃለ ምዕዳናቸው በአሽሙር መናገራቸውም ተሰብሳቢዎችን ፈገግ አሰኝቷል፡፡

የቤቱን ፈገግታ ያከሰመው፣ የፓትርያርኩ ክብረ ነክ ንግግር ግን ወዲያው ነበር የተሰማው፡፡ “ተናግሮ አናጋሪ የትላንቱ ሰውዬ” ባሏቸው ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ላይ ለአጠቃላይ ጉባኤውም ለመንበረ ፕትርክናውም በማይመጥን ንግግር፥ ደጋፊዎቻቸውን ጭምር ነበር ያሳፈሩት፡፡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በእጅጉ አዝነዋል፤ ጥቂት የማይባሉትም ቁጣቸውን በግልጽ አሳይተዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል፣ ፓትርያርኩ በሚሰጧቸው ሕገ ወጥና ረብሕ የለሽ መመሪያዎች እንዲጠነቀቁ፣ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን አቅርበው ማነጋገርን እንዲያስቀድሙ ነበር ምሳሌያዊ ምክር የሰጡት፤ ቅዱስ ሲኖዶሱንም ያሳሰቡት፡፡ እንደተለመደው ግን፣ በዚያው ዕለት ማምሻውን፣ በተጠቀሱት ክፉ አማካሪዎች ምሳሌያዊ ምክሩ በአሉታ እየተነተነ የፓትርያርኩ ቁጣ እንዲጋጋም መደረጉ ተጠቅሷል፡፡

“አቡነ ፋኑኤል፣ በፈንጅና ጭስ መስለው የተናገሩትን [አማካሪዎቻቸው]ይዘው፣ ቅዱስነትዎ የሚጽፉት ደብዳቤ ከዚህ ግቢ ውጭ የማይሠራና አቅም የሌለው እንደኾነ፤ ምንም ቢጽፉ የትኛውም አካል የማያስፈጽመው ነው፤ ነገር ግን መነጋገርያ ብዙ ሰው እያደናገረ ነው፤ ብለው ተርጉመውላቸዋል፤ ይህም ሕመም ፈጥሮባቸው አድሯል፤”

ነውረኛ ንግግራቸው በአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊዎች ላይ የፈጠረውን ፍጻሜ ስሜት ቢያዩም፣ ይብሱኑ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከሀገረ ስብከታቸው ለማገድ ነው እየዛቱ የሚገኙት፡፡ በዚህ ረገድ በሀገረ ስብከታቸው ተቀባይነት ያጡትና የመባረር ዕጣ የሚጠብቃቸው ብፁዕ አባ ማርቆስ፣ “ሀገረ ስብከቱን ለማኅበረ ቅዱሳን አሳልፎ ሰጥቶታል፤” እያሉ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን በማሳጣት በቦታቸው ለመተካት ፓትርያርኩን እየገፋፉ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡ “ምን ሲኖዶስ አለ፤ ሲኖዶስ እኛው ነን፤” በሚል ፓትርያርኩ ሌሎችንም አባቶች እንዲያስተባብሩ እንዳሉ ተገልጿል፡፡

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በበኩላቸው፣ ለተሰነዘረባቸው ውንጀላ ፓትርያርኩን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ደረጃ እንደሚጠይቁና በስም ማጥፋትም እንደሚከሷቸው ነው የተጠቆመው፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ርእሰ አበው እንደመኾናቸው መጠን፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቀው ለቤተ ክርስቲያኒቱ አጠቃላይ አመራር የመስጠት ግዴታ አለባቸው፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ እንደተደነገገው፣ በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰኑና ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋራ እየተማከሩ መሥራት የሚጠበቅባቸው ቢኾንም፣ ከዚህ ውጭ እየመከሩ የሚከተሉት ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ አካሔድ፣ ታማኝነታቸውና መንፈሳዊ አባትነታቸው በካህናትና በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ፤ በባለሥልጣናትም ዘንድ አቅም ቢስ ተደርገው እንዲታዩ አድርጓቸዋል፡፡ የመንግሥት ሹማምንትን ባገኙ ቁጥር፣ “ማኅበሩን ዝጉልኝ” የሚለው የዘወትር ውትወታቸው በእጅጉ እንዳስናቃቸውና ተደማጭነት እንዳሳጣቸውም ተጠቁሟል፡፡

በቃል አሳውቀውታል የተባለውና በቀጣይም በጽሑፍ እንደሚያቀርቡ የተጠቆመው ከሓላፊነት የመልቀቅ ጥያቄ መነሻዎች ባለሥልጣናቱን እያነጋገረ እንደሚገኝ ተነግሯል፤ ከሥልጣን ለመልቀቅ ፍላጎት እንዳላቸው ከማሳየት ይልቅ፣ ከመንግሥት ያጡትን ትኩረት ለመመለስ በዚህም፣ በቀጣዩ ሰኞ በሚጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ጫና ፈጥረው ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም፣ ከእኩይ መካሪዎቻቸው ጋራ የወጠኑት ስልት ሊኾን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ኾኖ የተሾመ አባት ከመዓርጉ የሚወርደው፡- ሃይማኖትን የሚያፋልስ፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የማይጠብቅ፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ፤ በተሾመበት ቀን የፈጸመውን ቃለ መሐላ ካልጠበቀ፤ ታማኝነቱና መንፈሳዊ አባትነቱ ተቀባይነት ያጣ ከኾነና ይህም በተጨባጭ ተረጋግጦ በቅዱስ ሲኖዶስ ሲወሰን እንደኾነ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 33/1(ሀ) እና (ለ) ተደንግጓል፡፡

wanted officials