Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, February 23, 2018

በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የተከሰሱ የጦር አለቆች ከእስር ተፈቱ

 በእነ ጀ/ል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ‹‹የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል›› ተብለው የተከሰሱት ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ ጄነራል አሳምነው ፅጌ፣ ኮ/ል አበረ አሰፋ፣ ኮ/ል ሰለሞን አሻግሬ በዛሬው ዕለት ከእስር መለቀቃቸው ተሰምቷል፡፡ በተጨማሪም ሻለቃ መኮንን ወርቁ፣ ሻለቃ መሰከረ ካሳ፣ ሻለቃ ምስጋናው ተሰማ፣ ኢንስፔክተር አመራር ባያብል፣ ዋና ሳጅን ጎበና እና ሳጅን ይበልጣል ብርሀኑ የተባሉ ፍርደኞች ከእስር ቤት መውጣታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከየካቲት ወር 2000 ጀምሮ በቁጥጥር ስር ውለው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ክስ የተመሰረተባቸው የጦር መኮንኖቹ፤ ከእስር የተፈቱት ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ሲሆን፤ በእስር ላይ እያሉ ፈታኝ ጊዜ እንዳሳለፉ ከዚህ ቀደም ሲነገር ቆይቷል፡፡ ተከሳሾቹ በተመሰረተባቸው ክስ እስከ ዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸው ነበር፡፡ ለእስር የተዳረጉትም በ1998 መንግስትን ‹‹በመፈንቅለ መንግስት ለመገልበጥ አሲረዋል›› ተብሎ እንደነበር መረጃዎች ያስታውሳሉ፡፡

በዚሁ የክስ መዝገብ ከተከሰሱ የጦር መኮንኖች ሁለቱ ትላንት ከእስር መፈታታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በአገዛዙ ላይ ጫና ያሳደረው በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ መሆኑ ተደጋግሞ ተነግሯል፡፡ አገዛዙ ህዝብ ባሳደረበት ጫና የህሊና እስረኞችን ለመፍታት ቢገደድም፤ እስካሁን ድረስ የተፈቱ ሰዎች ቁጥር፣ በፖለቲካ ክስ ከታሰሩ ሰዎች ቁጥር አንጻር ሲታይ አነስተኛ መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ለአገዛዙ እየቀረበ ያለው ጥሪ እና ማሳሰቢያ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል፡፡
BBN News February 22, 2018

No comments:

Post a Comment

wanted officials