“ሶስት ሺህ ብር እንድሚከፈለን በደላሎቻቸው አማካኝነት ሲነግሩን አሰተማሪዎች ሳይቀሩ ሰራቸውን ጥለው በፋብሪካ ውስጥ ተቀጥረው ነበር፣ ነገር ግን የእውነተኛ ክፍያው በወር አንድ ሺህ 50 ብር ብቻ ነው።” ኤች ኤንድ ኤም (H&M) ባንግላዴሽ በነበረው ፋበሪካው ውስጥ በደረሰ የመደርመስ አደጋ አንድ ሺህ 1 መቶ ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ፣ የሰራ ላይ የደህንነት ማረጋገጫዎችን ሰለማይተገብር ወቀሳ ደርሶበት ነበር። በተመሳሳይ በኢትዮጲያ ባለው ፋበሪካው መሰረታዊ የደህንነት ማረጋገጫዎችን አላሟላም በሏል የሲውዲኑ ባንክ።
ዋዜማ ራዲዮ– የሲውዲንን መንግስትን ከፊል የእርዳታ ገንዘብ ተቀብሎ ኢትዮጲያ ውስጥ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ከፍቶ ስራ የጀመረው ኤች ኤንድ ኤም (H&M) ኢትዮጲያ ለሚገኙ ሰራተኞቹ የክፍያ መሰፈርትን ሳያሟላ፣ አጀግ በጣም ዝቅተኛ ከሚባለው በታች እየከፈለ፣ አለማቀፍ የሆነውን የሰራተኞች ዝቅተኛ ክፍያ ባላሟሟላቱ ድርጅቱ ላይ ገንዘብ ያፈሰሰው የሲውዲኑ ኖርዲያ ባንክ ለኤች ኤንድ ኤም (H&M) የሰጠውን ገንዘብ አገተበት።
በሐዋሳ ኢንዱሰትሪ ፓርክ ከከትሙ በርካታ አለም አቀፍ ዝና ያላቸው የንግድ ተቋም መካከል የሆነው ኤች ኤንድ ኤም (H&M) በሐዋሳ ሰራ ከጀመረ ከሁለት አመታት በላይ አሰቆጥሯል፡፡ እንደ ኤች ኤንድ ኤም (H&M) ከሆነ አራት ሺህ ሰራተኞችን ቀጥሮ በአሁኑ ሰዓት እያሰራ ይገኛል፡፡
የሲውዲን የህዝብ ቴሌቨዥን ድርጅት ኤስ ቪ ቲ (SVT) ኤች ኤንድ ኤም (H&M) በኢትዮጲያ ውስጥ በሚገኛው የሐዋሳ ፋብሪካው ለሰራተኞች ዝቅተኛ ከሚባለው የዓለም አቀፍ ደረጃ ወርዶ በጣም ዝቅ ያለ ክፍያ እየከፈለ ይገኛል በሎ መዘገቡን ተከትሎ የሲውዲኑ ኖርዲያ ባንክ ለኤች ኤንድ ኤም (H&M)ክፍያውን አግዶበታል፡፡
በሰዓት ሲሰላ አራት ብር ከአርባ ሳንቲም በሐዋሳ በሚገኘው ፋብሪካው ለኢትዮጲያውያኑ ሰራተኞቹ የሚከፍለው የኽው ኤች ኤንድ ኤም (H&M) ድርጅት አገሪቷ ለሰራተኞቿ ከምትከፍለው ያነሰ ክፍያ አልከፈልኩም ብሎ ተከራክሯል፡፡
“እየተጠቀሙብኝ ነው። ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሰው ሃገር እንደሚሰሩ አይነት ሰዎች እንደሆንኩ ይስማኛል፡፡ ግን ይህ ሃገሬ ነው።” ስትል ለኤስ ቪ ቲ (SVT) ቴሌቭዥን ጣቢያ አሰተያየቷን ሰጥታለች አሁን በሐዋሳ ኢንዱሰትሪ ፋብሪካ ተቀጥራ በመሰራት ላይ ያለችው የባህርሰው ጥበቡ።
እንደ ኤች ኤንድ ኤም (H&M) እና ዘሃራ የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ስም እና ዝና ያላቸው ፋብሪካዎችን ወደ ሃገርቤት ለመሳብ የኢትዮጲያ መንግስት ርካሽ የሰው ጉልበት ሰለመኖሩ ቀስቅሶ የተለያዩ ኩባንያዎችን የሳበ ሲሆን፣ ጉትጎታው ሲተገበር ግን ኢትዮጲያ ለሰራተኞቿ የሰዓት ቁርጥ ክፍያ ያላመቻቸች ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዓለም ዝቅተኛ ክፍያ ለህዘቦቿ እንዲከፈል የምትፈቅድ ሆናለች። በዚህም ድርጊታቸው ዓለም አቀፍ ውግዘትን እንዳያሰከትልባቸው ሰጋት የገባቸው በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከሃላፊነት ለመሸሽ እንዲያመቻቸው ደርጅታቸውን ከቻይና ባለሐብቶች ጋር በማያያዝ ሰማቸውን ቀይረው በሐዋሳ ከትመዋል።
ሰራተኞች ከወርሃዊ ዝቅተኛ ክፍያ በተጨማሪ ድንገት ህመም ቢያጋጥማቸው አንድ ቀን ለቀሩበት ከወር ደሞዛቸው 20 በመቶ ይቆርጥባቸዋል ሲል ይኸው ኤስ ቪ ቲ (SVT) ቴሌቭዥን ዘግቧል።
ኤች ኤንድ ኤም (H&M) እንዴት አድርጎ ከሲውዲን መንግስት የተቀበለውን ገንዘብ እየተጠቀመበት እንደሆነ ለማጤን እና የሰነ ምግባር መሰረታዊ መሰፈርቶችን ማሟላታቸውን በትኩረት የሚያረጋግጠው ኖርዲያ ባንክ በተለይ ኤች ኤንድ ኤም (H&M) ኢትዮጲያ ባለው ፋብሪካው ለአካባቢ ተሰማሚነቱን፣ የውሃ አጠቃቀሙን፣የሰራተኞቹን ከፍያ እንዲሁም ደህንንት እና ከሰራ ሁኔታዎች ጋር የተያያዙ ችግሮቹን አስኪፈታ ገንዘቡን አግቶበታል።
ከሰራ ቀጣይነት፣ ቋሚነት ጋር በተያያዘ መሰረታዊ ችግር እንዳለበት የሚነገርለት ይኸው የልብስ ፋብሪካ ኤች ኤንድ ኤም (H&M) በኢትዮጲያ ለሰራተኞቹ የሚከፍልው ክፍያ “ለመኖር የሚያሰችሉ” ከሚባሉ የሰራ ክፍያዎች ውስጥ የማይመደብ ነው።
“ችግሩ መንግስት ምን ያህል ስራ እንደምንፈልግ ያውቃል። ከቀጣሪያችን ጋር በመሆን ምን ያህል ለእኛ መከፈል እንዳለበት ስምምነት አደርጓል” ትላለች የባህርሰው።
“ሶስት ሺህ ብር እንድሚከፈለን በደላሎቻቸው አማካኝነት ሲነግሩን አሰተማሪዎች ሳይቀሩ ሰራቸውን ጥለው በፋብሪካ ውስጥ ተቀጥረው ነበር፣ ነገር ግን የእውነተኛ ክፍያው በወር አንድ ሺህ 50 ብር ብቻ ነው።”
ኤች ኤንድ ኤም (H&M) ባንግላዴሽ በነበረው ፋበሪካው ውስጥ በደረሰ የመደርመስ አደጋ አንድ ሺህ 1 መቶ ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ፣ የሰራ ላይ የደህንነት ማረጋገጫዎችን ሰለማይተገብር ወቀሳ ደርሶበት ነበር። በተመሳሳይ በኢትዮጲያ ባለው ፋበሪካው መሰረታዊ የደህንነት ማረጋገጫዎችን አላሟላም በሏል የሲውዲኑ ባንክ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሐገሮችን የኢንቨስትመንት ምቹነት የሚያጠናው ሲልክ ኢንቨስት የተባለ ድርጀት በኢትዮጲያ በአሁኑ ሰዓት ከህንድ፣ ከሱዳን፣ ከጀርመን፣ ከጣሊያን፣ ከቱርክ፣ ከሳውዲዓረቡያ፣ ከየመን፣ ከእንግሊዝ፣ ከእስራኤል፣ ከካናዳ የመጡ አዳዲስ ፋበሪካዎችን በሃገሪቷ አቋቁመዋል። [ዝርዝር የድምፅ ዘገባ ከታች ተያይዟል]

No comments:
Post a Comment