Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, February 26, 2018

የዋልድባ መነኮሳት ክስ አሁንም እንደቀጠለ ነው

ጠበቃ አማሃ መኮንን የሕግ መርህ ተጥሷል እያሉ ነው ።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬው እለት የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት፤ በእነ ተሻገር ወ/ሚካኤል ላቀው የክስ መዝገብ ስር የተከሰሱት የዋልድባ ገዳም መነኮሳት አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም ካሴ እና አባ ገ/ስላሴ ወ/ሀይማኖት። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቅርቦት የነበረውን የሽብርተኝነት ክስ አሁንም እንደቀጠለ ነው ። መነኮሳቱ የሃይማኖት ልብሳቸውን እንዲያወልቁ መገደዳቸውና መደብደባቸውን አስመልክቶ ለሚደርስባቸው ኢሰብዓዊ ድርጊት ቀደም ብሎ ለችሎቱ በጽሁፍ ያቀረቡትን አቤቱታ አስመልክቶ ፣ ፍርድ ቤቱ በጽሁፍ ለቀረበለት አቤቱታ የሚመለከተው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ምላሽ እንዲሰጥ ለየካቲት 30/ 2010 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን፤ በመነኮሳቱ ላይ ለቀረበው ክስ የዐቃቤ ሕግ ሦስት የሰው ምስክሮች ለመስማት ለመጋቢት 18 ቀን 2010 ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በእነ ተሻገር ወ/ሚካኤል ላቀው የክስ መዝገብ 38 ተከሳሾች የተከሰሱ ሲሆን የ35ቱ ክሱ ሲቋረጥ፤ መነኮሳቱን ጨምሮ የአንድ ሰው ክስ እንደቀጠለ ነው። ይህን በተመለከተ የዋልድባ መነኮሳት ጠበቃ የሆኑት አማሃ መኮንን በደንቦኞቼ ላይ የህገ መንግስቱ ዋንኛ መርህ የሆነው ” ሰዎች ሁሉ በሕግ ፊት እኩል ናቸው” የሚለውን በይፋ በሚጣረስ መልኩ ፤ የዋልድባ መነኮሳት ላይ የሕግ አድሏዊነት እየተፈጸመባቸው ነው። ያሉ ሲሆን፣ አያይዘውም ” በተመሳሳይ መዝገብ፣ በተመሳሳይ ክስ የሚገኙትን እየለዩ አንዱን መፍታት ሌላውን ማሰር የትኛውም አይነት የሕግ ድጋፍ የለውም ” ብለዋል ።

የዋልድባ መነኮሳት ለባለፈው አንድ አመት ከአንድ ወር በእስር ላይ ይገኛሉ። መነኮሳቱ “መንግሥት” የዋልድባ ገዳም ይዞታ በሆነው አካባቢ የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም ማቀዱ እና ዕቅዱ በገዳሙ መነኮሳት ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን ከ 2004 ዓ.ም ጀምሮ መነኮሳቱ ለእስር እስከተዳረጉበት ድረስ አቤቱታቸውን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ በተደጋጋሚ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።

(ይድነቃቸው ከበደ )

No comments:

Post a Comment

wanted officials