Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, April 27, 2018

የሰሜንና የደቡብ ኮሪያ መሪዎች ተገናኙ


ሚያዚያ 19 2010
ኪም ጆንግ ኡን እ.አ.አ ከ1953 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የደቡብ ኮሪያን ግዛት የረገጡ የሰሜን ኮሪያ መሪ ሆነዋል፡፡
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የደቡብ ኮሪያ አቻቸው ሙን ጄይ ኢን ዛሬ ተገናኝተዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች የሰላም ስምምነትና በኒዩክለር ጦር መሳሪያዎች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አሜሪካ በበኩሏ የሁለቱ መሪዎች ውይይት ወደ ሰላምና ብልጽግና ይወስዳቸዋል የሚል ተስፋ እንዳላት ገልጻለች፡፡
ምንጭ:- ቢቢሲ

Thursday, April 26, 2018

የዘመኑ የፕሮቴስታንት ነብያቶች ሀሰተኛ ከሚያደርጓቸው ነገር (ክፍል)3


Image may contain: 9 people, people smiling, text


ማንም ሰው ሲናገር እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር ተብሎ በተጻፈው ቃል መሰረት....የዘመኑን ውሸታም ነጣቂ ተኩላዎችን እንዲህ እንተርካቸዋለን...በቃሉ


በዚህን ጊዜ....ከኢየሱስ ወይም ከመጽሀፍ ቅዱስ ቃል ይልቅ የነብያቶችን ኮቴ በመከተል....ለሀሰተኞች ነብያቶች መስፋፍያ የሆነችው ብቸኛዋ ቤተ እምነት 👉የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይዋ ምዕመን ስትሆን

እንደ ፕሮቴስታንቶች አባባል.....መንግስተ ሰማያት የምንገባው 👉እኛ ብቻ ነን

ከፕሮቴስታን ውጪ ያሉት ቤተ እምነቶች የዘለአለም 👉ፍርድ ተፈርዶባቸዋል

ስለሆነም....ወደ እኛ ተቀላቀሉና የመንግስቱ ወራሽ ሁኑ የሚለውን ጥሪ ስታቀርብ የምትስተዋል ቸርች ስትሆን

ትውልድን ማርካ ወደ እራሷ የምትስብበት ብቸኛ መንገድ.....ደግሞ...ከመብልና ከመጠጥ ያልዘለለ 👉ተአምራት በማድረግ ነው

ስለሆነም....የፕሮቴስታንት ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው...በመድረካቸው ላይ በሚፈጸመው👉ጥንቆላዊ የውሸት 👉ተአምራት አማካኝነት እንደሆነ ብዙዎቻችን ሳናውቅ የቀረን አይመስለንም

የሆነው ሆኖ ግን....በአንድ ቤተ እምነት ውስጥ የተከታይ ቁጥር ስላደገ....አልያም ደግሞ ስላነሰ የዝያን ቤተ እምነት እርግጠኛነትን አያረጋግጥልንም

ነገር ግን.....እንደ መጽሀፍ ቅዱስ እውነታ ስንሄድ....የሰው መንፈሳዊ ጥንካሬ የሚታየው

አምላኩን....በማወቅ ውስጥ ያለው ጥንካሬ እና ላወቀው አምላክ የመታዘዙ ጥንካሬ ነው መስፈርት ውስጥ በመግባት ትክክለኛ ቤተ እምነት መሆኑ የሚረጋገጠው
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
"፤ ቃል ኪዳኑን የሚበድሉትንም በማታለል ያስታል፤ ነገር ግን አምላካቸውን የሚያውቁ ሕዝብ ይበረታሉ፥ ያደርጋሉም። "
(ትንቢተ ዳንኤል 11: 32)

ነገር ግን እነዚህ ከላይ የተነሱት ነጥቦች በጭራሽ በፕሮቴስታንት ቸርች ውስጥ አይስተዋሉም

ያም ማለት.....የፕሮቴስታን እምነት ተከታዮችን ትኩረት የወሰደው....አምላክን በማወቅ ዙርያ ላይ የሚደረገው ስብከት ሳይሆን....ስለ ብልፅና ብቻ የሚሰበከው ስብከት

እና የሚደረገው የውሸት ተአምራት.....ኢየሱስን....ወይም ከጥንት ጀምሮ ብቻውን ያለውን አምላክ እግዚአብሔርን እንዳያውቁ እና እንዳይበረቱ እንቅፋት ሆኖባቸዋል

ለዚህም....ነው.....እግዚአብሔርም ሆነ...ነብያት....እንዲሁም...ሀዋርያቶች የማያውቁትን ስላሴ የተባሉ 3 አማልክቶችን ከኦርቶዶክስ ተንበርክካ በመቀበል

እርኩሱን....ከቅዱሱ ጋር ለማዋሀድ በቅታ....ዛሬ የማንም አጭበርባሪ ነብይ እግር መረገጫ የሆነችው

ስለሆነም....ዛሬ በዋናነት ልናየው የሚያስፈልገው ትልቁ....ርዕሳችን....👉የፕሮቴስታንት 👉ቤተ እምነት ከተለያየ 👉ሀጥያቶች እና 👉ከተለያየ እርክሰቶች መላቀቅ አቅቷት የክርስትና ፍሬ የማይታይባት ለምንድነው???

የሚለውን ጽንሰ ሀስብ ለማየት እንሞክራለን

ይህንን ፖስት የምታነቡ ፕሮቴስታንቶች....ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ እንደሚባለው ተረት....ለራሳችሁ ስትሉ...ይህንን ፖስት በማስተዋል በማንበብ.....ራሳችሁን መርምሩ እንደ እግዚአብሔር ቃል

👇👇👇👇👇
መልካም ንባብ

👉የዛሬውን አያድርገውና ድሮ ድሮ 👉የፕሮቴስታንት እምነት ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ.....የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ፕሮቴስታንቶችን ለመሳደብ አላስፈላጊ የሆነ ፒክቸሮችን ሲለጥፉ....እኛን ለማንቋሸሽ ሆን ብለው የሚያቀነባብሩት ነገር ነው በማለት ነገሩን በቸልታ አልፈው ነበር

ነገር ግን እየዋልን ስናድር.....ነገሩ የእውነት መሆኑን በገዛ አይኔ እንዳይ እና ነገሩን ተረድቼ እንዳሰላስል ኢየሱስ ረዳኝ

ያም ማለት ግልጽ በሆነ አነጋገር.....በፕሮቴስታን ውስጥ የሚማርክ ስማሬ እና የሚማርክ ስብከት ቢሰማም

በዚህ አገልግሎት ውስጥ የሚሳተፉ የፕሮቴስታን አገልጋዮች.....እግዚአብሔርን የመፍራት እና ቃሉን የማክበር....ፍላጎቱ የላቸውም

ለምሳሌ....ከዘማርያን መካከል.....ዘማሪ 👉ሶፍያ ሽባባውን እና 👉ዘማሪ ተከስተ ጌትነትን ብንመለከት....

👉ዘማሪ ሶፍያ ሽባባው ማለት....እጅግ በጣም የምወዳት እና ዝማሬዎችዋን በፍቅር የማዳምጥላት....እህታችን ናት

ነገር ግን...ይቺ እህታችን የኃላ ታሪኲ ተጠንቶ....እንደ እግዚአብሔር ቃል ሲታይ...የሰውን ባል አፋታ ያገባች ሴት በመሆንዋ አመንዝራ ትባላለች

ምክንያቱም....ዘማሪ 👉ሶፍያ ሽባባውን ያገባ....ወንድም...ዶክተር ወዳጄነህ የተባለ 👉ፓስተር ሲሆን

ይህ ሰው አስቀድሞ ያገባትን ሚስት ፈቷት...👉ሶፍያን በማግባቱ ምክንያት ሚስቱ ላቀረበች ክስ የሰጠው 👉ምላሽ

እሷ....አስማተኛ ነት....ሌሊት ሌሊት ላይ ትሰለባለች...ከዚህም የተነሳ ፈትቻት....ሶፍያን አገባሁ....የሚል ምላሽ የሰጠበትን መጽኤት ያነበብኩት...ገና እዝያው እምነት ውስጥ እያለሁ ነው

ስለሆነም....በዝማሬ እና በመጋቢነት አገልግሎት የተሰማሩ እነዚህ ሁለት ጥንዶች የእግዚአብሄርን ቃል አክብረዋል ወይስ ንቀዋል???

ምክንያቱም....ከሴት ጋር ሚያመነዝርም ሆነ የተፈታውን የሚያገባ ሰው አመንዝራ እንደሚባል ቃል በግልጽ ይናገራል

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

(የማቴዎስ ወንጌል 5 )
=====================
31፤ ሚስቱን የሚፈታት ሁሉ የፍችዋን ጽሕፈት ይስጣት ተባለ።
32፤ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።

ሲቀጥል.....ተወዳጁን....የፕሮቴስታንት ዘማሪ 👉ተከስተን ስንመለከት

እርሱም...ከሴት ጋር ሆቴል ተቀጣጥሮ....ከሚስቱ ውጪ...ከሌላ ሴት ጋር በዝሙት ከወደቀ በኃላ ቤተ ክርስትያን በመሄድ እውነቱን በገዛ አንደበቱ ተናግሯል

ይህ ሰው....በዝሙትና በምንዝርና ነው የወደቀው

ሚስት እያለችው ሌላ ሴት ጋር በመሄዱ....👉አመንዝሯል

ካላገባት ሴት ጋር አንሶላ በመጋፈጡ ዘምቷል

ነገር ግን....የእግዚአብሔር ቃል ዝሙትን እንዲህ ሲል ያወግዘዋል

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6 )
=====================
18፤ ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል።

19-20፤ ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?

በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።

ሲቀጥል....ነብይ ነኝ እያለ የሚያጭበረብረው....ነብይ 👉በላይ ስንት ሚስቶች አግብቷል ቢባል 2 የሚለውን መልስ እናገኛለን

የሆነው ሆኖ ግን....ይህንን ስል በሰው ላይ እየፈረድኩኝ ሳይሆን....መንግስተ ሰማይ የእኛ ናት ማንም አይገባባትም ያለ እኛ እያለች....የምትፎክረዋ ፕሮቴስታንት....ከእንደዚህ አይነት እርክሰቶች ሳትጸዳ መንግስቱን የምትመኘው

እውን 👉የእግዚአብሔር መንግስት 👉የዝሙተኛ እና የአመንዝራ ክምችት ቦታ ነውን???

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
"፤ ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ "
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6: 9)

መቼም ቢሆን እነዚህን ጥያቄዎች ለፕሮቴስታንቶች ብናቀርብ የሚመልሱልን መልስ እንዲህ የሚል መልስ ነው

👉በነጻነት ልንኖር 👉ክርስቶስ ነጻ አወጣን የተባለውን ቃል አላነበባችሁምን??

እግዚአብሔር ልብን ያያል....እናም ይቅር ባይ አምላክ ነው በማለት....በክርስቶስ የተገኘውን ጸጋ የእርክሰት መሸፈኛ ለማድረግ ጥቅስ ይጠቅሱልናል

ነገር ግን በነጻነት ልንኖር በክርስቶስ ነጻ አወጣን የተባለው ቃል.....ራስን ለስጋዊ ሀጥያት በማለምልመድ በተለያየ እርክሰት ውስጥ ተዘፈቁ የሚለውን መልእክት ለማስተላለፍ ነውን?!!!!

አንሳት! አንሳት ! በእግዚአብሄር ቃል አይዘበትበትምና....እርክሰት ውስጥ ተዘፍቀን....በክርቶስ ያገኘነውን አርነት ወይም 👉ጸጋን ለክፋት መሸፈኛ አናድርገው!!!

ምክንያቱም.....እግዚአብሔር አምላካችን ባለ ብዙ ምህረት እንደሆነ ሁሉ....በዝያው ልክ ቁጣውም የበዛ....ግርማው የሚያስፈራ

አምላክ በመሆኑ....እንደ እርሱ ቃል የማይመላለሱትን ሰዎች ከመበቀል ወደ ኃላ አይልም!!!

(ትንቢተ ኢዮኤል 2 )
=====================
11፤ እግዚአብሔርም በሠራዊቱ ፊት ድምፁን ይሰጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ ቃሉንም የሚያደርግ እርሱ ኃያል ነውና፤ የእግዚአብሔርም ቀን ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ ነውና ማንስ ይችለዋል?

12፤ አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ።
13፤ ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቁጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።

ስለሆነም......በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻ ያወጣን....በተለያየ እርክሰት ውስጥ በመግባት የእግዚአብሄርን ምህረት ተለማምደን....እድሜ ልካችንን በሀጥያት እየተጨማለቅን እንድንኖር አይደለም

ምክንያቱም....ማንም ሰው በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት በመሆኑ.....ስለ ስጋ ማሰብን...ትቶ.....በመንፈሳዊ ነገር በመበርታት....የአምላኩን ልብ በማስደሰት ወደ ሚቀድስ እግዚአብሔር ይጠጋል....በእምነት

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
(ወደ ሮሜ ሰዎች 6 )
=====================
6፤ ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።
...
13፤ ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

የሆነው ሆኖ ግን.....እንደዚህ አይነት እርክሰቶች በፕሮቴስታንት ውስጥ ብቻ ነው ሚከሰተው ለማለት ሳይሆን

የመንግስቱ ወራሽ ነኝ የምትለዋ ፕሮቴስታንት በምንም አይነት መልኩ ወራሽ የማትሆን....

በእርክሰት ውስጥ ተጠላልፋ ያለች #ባቢሎን በመሆንዋ...የነብያቶችን የጥንቁልና ተአምራት በማየት ወደዚህ እርክሰት ውስጥ የምትጨመሩ ሰዎች አስተውሉ!!!

በማለት....ፕሮቴስታንት ከዚህ እርክሰት መላቀቅ ያልቻለችው እንዴት ነው???....የሚለውን እንመለከታለን

ፕሮቴስታንት ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ እያለች በስሙ ብትጓደድም

በስሙ ተአምራት በማድረግ የሚያስደምማት....መጋቢዎች እንጂ...

በክርስቶስ ማንነት ላይ ያተኮረ አስተምህሮትን በማስተማር....ከእውነተኛው ጌታ ኢየሱስ ጋር አስተዋውቆ.....ክርስቶስን የሚተርክ መጋቢ ወይም እረኛ ስለሌላውቸ

...ከማይጠፋው ዘር ባለመወለዳቸው ምክንያት....የሀጥያት ባርያዎች ለመሆን ችለዋል

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

"፤ ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው። "
(የዮሐንስ ወንጌል 8: 34)

በጣም የሚገርመው እና....ይህ ነገር እውነት ነው....ማለትም....ፕሮቴስታንት በተለያየ እርክሰት ውስጥ ያለች ያልተለየች መሆንዋን

የሚመሰክሩት....የገዛ ፓስተሮቻቸው እና ነብያቶቻቸው ናቸው

ተአምራት አድራጊ ነን ባዮቹ ነብያቶች አጋንንት ሲያወጡ የሰማ ሰው ካለ

እንዲህ በማለት ነው...

አንተ 👉በጫት የገባህ መንፈስ ውጣ! ብዬሀለሁ! ውጣ!

እንግዲህ...ይህ ሰው....ጌታን ሲቀበል...እጁን ወደ ላይ አድርጎ....አለምንና ሰይጣንን ክጄ አንተን ተቀብያለሁ....ብሎ በፓስተሮቹ አማካኝነት የተናዘዘውን ኑዛዜ ረስቶ....ጫት ወደ መቃም የመራው መንፈስ....ተንበርክኮ የተቀበለው ኢየሱስ ነው ማለት ነው???

አሁንም...👉ነብዩ ወይም 👉ፓስተሩ ከሌላኛው ሰው ላይ ሲያወጣ ደግሞ እንዲህ ይላል

ውጣ! ውጣ! ብዬሀለሁ....አንተ 👉በሺሻ የገባህ

ይህም ሰው ተንበርክኮ ጌታን ከተቀበለ በኃላ ነው እንግዲህ 👉ሺሻ ለመሳብ ሔዶ ሰይጣን ስቦ የሚመጣው

ታድያ የፕሮቴስታን ቸርች እውነተኛ በእግዚአብሄር ቃል ላይ የታነጸች የመንግስቱ ወራሽ ከሆነች....በተለያየ ሀጥያት ውስጥ ተዘፍቃ....ወንጌልን የምታሰድብ....ክርስትናን የምታንቊሽሽው ለምንድነው?? ለሚለው ጥያቄ

ከእውነተኛ ጌታ ኢየሱስ ጋር አስተዋውቆ....እውነተኛውን ወንጌልን በመግለጥ ስለ ሰማያዊ መገለጥ የሚሰብካት እረኛ ስለሌላት ነው

እረኞች አሏት.....ነገር ግን ወደ እውነት የሚመሩ እረኞች ሳይሆኑ....የእግዚአብሄርን ምህረት ለምዕመናኑ በማለማመድ

ትውልዱ....ከድፍረት ሀጥያት ተላቆ እግዚአብሔርን በማክበር እንዳይኖሩ ትልቅ አስተዋዕጾ እያደረጉ ነው

ለምሳሌ....ህልም አለምን አልያም ደግሞ ጌታ ተገለጠልን የሚሉ ነብያቶቻቸው....እንዲህ ይላሉ

ሁለት ወጣት ሴቶች አላችሁ....እዚህ ጉባኤ ውስጥ

ዝሙት ፍጽማችሁ ነው የመጣችሁት....እንድያውም ምልክት ልስጣችሁ

የውስጥ ልብሳችሁ ይህን ይህንን ይመስላል......

ጸጉራችሁ....ረዘም ይላል....ቁመናችሁ መካከለኛ ነው

እና የመሳሰሉትን ምልክቶች በመጥቀስ....ጠንቊዮቻቸው አስቀድመው...አይተው የነገሯቸውን ቃላት በመድገም...እነዝያ ወጣቶች ዝሙት ሰርተው ጉባኤ የገቡ መሆናቸውን

በማሳወቅ....እግዚአብሔር ምሬአችኃለሁ እና ተመለሱ ይላችኃል በማለት....ያልሰሙትን ድምጽ ያስተጋባሉ

ነገር ግን እግዚአብሔር ተናግሮአቸው ሳይሆን ከሌው መፍፈስ የሰሙትን ድምጽ ነው ሚያስተብቡት

ምክንያቱም....እግዚአብሔር አምላክ....ፍርዱ ቅን ነው

ክርስቶስ ኢየሱስን ከማወቁ በፊት ሰው ለሚሰራው ሀጥያት ደሙ ጠበቃ እንደሆነ....1ኛ ዮሐ 1፥7-8 አልሸሸገንም

ነገር ግን....ሰው ክርስቶስን አውቄ አምኜበት ዳግም ተወልጃለሁ....ብሎ ተመልሶ ሀጥያት ውስጥ ከወደቀ...ያ ሀጥያተኛ ለሰራው ስጋዊ ሀጥያት....መስዋዕት አልያም ዋጋ ሳይከፍል...እንዲሁ ምህረት አያገኝም

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

(ወደ ዕብራውያን 10 )
=====================
26፤ የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥

27፤ የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ።

ሲቀጥል....በሀዋርያቶች ዘመንም....አንድ ሰው እውነት ገብቶት በክርስቶስ ካመነ በኃላ...በስጋዊ ሀጥያት ውስጥ ቢዘፈቅ.....ያ ሰው ከመሀላቸው እንዲወጣ ነው ሚደረገው እንጂ

እሹሩሩ እያለ የሚመልሰው እግዚአብሔር የለም

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5 )
=====================
1፤ በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና።

2፤ እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ።
...
5፤ መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።

ምክንያቱም.....እግዚአብሔር ከሀጥያተኛ ጋር አይተባበርም....

ማንም ሰው በክርስቶስ ከሆነ አይተላለፍ የሚል ትዕዛዝ ሰጠ እንጂ

እኔ መሀሪ ነኝና እለት እለት በሀጥያት እየተጨማለቃችሁ ኑይ ይቅር እላችኃለሁ አይልም በጭራሽ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

"፤ ነገር ግን በክርስቶስ ልንጸድቅ የምንፈልግ ስንሆን ራሳችን ደግሞ ኃጢአተኞች ሆነን ከተገኘን፥ እንግዲያስ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ነዋ? አይደለም። "
(ወደ ገላትያ ሰዎች 2: 17)

ስለሆነም.....የመንግስቱ ወራሽ ነን በማለት በተአምራት ሰዎችን በመማረክ...ትውልድን ገደል እየከተተች ያለችዋ ፕሮቴስታንት

የእግዚአብሔርን ቃል በመግለጥ ለእውነት የሚማርክ እረኛ....ሳይሆን

ስለ ብልጽግና በመስበክ.....የእግዚአብሔርን ምህረት እያለማመደ ሰዎችን ከእውነት ፈቅቅ የሚያደርጉ የበግ ለምድ ለባሾች ከበዋት ስላሉ ነው

እናም......የሚለማመዱት ሀጥያት ምንጩ መድረግ ያልቻለው....ከማይጠፋ ዘር ባለመወለዳቸው ምክንያት ነው

ስለሆነም....ኢየሱስን አገኘሁ በማለት የፕሮቴስታንትን ደጅ ምታካልሉ ሰዎች አስቡበት

ሀሰተኛው ኢየሱስ የነገሰበት ቤተ እምነት ነውና....ለራሳችሁ
ስትሉ ነገሮቹን ለማስተዋል ሞክሩ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
"፤ እናንተ የእግዚአብሔር ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፥ እልፍ በሉ፥ ከዚያ ውጡ፥ ርኩስን ነገር አትንኩ፥ ከመካከልዋ ውጡ፥ ንጽሐን ሁኑ። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 52: 11)

ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘለአለም አለም ያድናል አሜን

wanted officials