Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, April 14, 2018

በግብጽ ሕጻናትን ለገበያ ባቀረቡ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ


በግብጽ  ሕጻናትን በድረገጽ ለገበያ ባቀረቡ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ።
ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉት ግለሰቦች ጉዳይም በወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዲታይ መደረጉም ታውቋል።
እንዲህ አይነቱ ጉዳይ በፍርድ ቤት ቀርቦ ሲታይም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።
በግብጽ ፍርድ ቤት ሲቀርብ የመጀመሪያው ነው በተባለው ሕጻናትን በኦንላይን ለገበያ በማቅረቡ ጉዳይ ተሳታፊ ናቸው ባሏቸውን ግለሰቦች ላይ የግብጽ የሕግ አካላት ክስ መመስረታቸውን ነው ዘገባዎች ያመለከቱት።
የግብጽ ሴክሬተሪ ጄኔራል አዛ ኢል አሽማይ ለግብጽ መገናኛ ብዙሀን እንዳሉት ግለሰቦቹ  በኢንተርኔት አማካይኝነት ልጆቹን ለመግዛት ከሀገር ውስጥም ይሁን ከውጭ ፍላጎት ካላቸው አካላት ገንዘብ መቀበላቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እንደተገኘባቸውም የህግ ባለሙያዎቹ ተናግረዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ባለፈው ታህሳስ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲደረግባቸው መቆየቱ ነው የታወቀው።
ባለፈው ጥርም የሃገሪቱ ፓርላማ ሕጻናት ላይ ከሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶች ጋር በተያያዘ ጠንከር ያለ ውሳኔ ማሳለፉንመ ዘገባው አስታውሷል።
በሕጻናቱ ላይ አላግባብ ድርጊት የሚፈጽም ማንኛውም ግለሰብ ከ20 አመት እስራት እስከ ሞት የሚያድርስ ቅጣት እንደሚጠብቀውም ፓርላማው ባወጣው የማሻሻያ ሕግ ላይ ሰፍሯል።
ፓርላማው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰውም በዛች ሀገር በሕጻናት ላይ የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ድርጊቶች እየተበራከቱ በመምጣታቸው መሆኑ ታውቋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials