Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, April 12, 2018

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የሊቢያ አቻቸውን በደርሶ መልስ 15ለ0 አሸንፈዋል

ሉሲዎቹ የሊቢያ አቻቸውን በደርሶ መልስ 15ለ0 አሸንፈዋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ሉሲዎች ለአፍሪካ ዋንጫ በመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታ የሊቢያ አቻቸውን ዛሬ 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም አስተናግደው 7ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
ሎዛ አበራ አራት ግቦችን በ27ኛ፣ 51ኛ፣ በ82ኛ እና በ87ኛ ደቂቃ ላይ ስታስቆጥር፤ ህይወት ደንጊሶ በ13ኛ ፣ ረሒማ ዘርጋ በ45ኛ እና ሰናይት ቦጋለ በ73ኛ ደቂቃ ቀሪዎቹን ግቦች ለሉሲዎቹ አስቆጥረዋል።
በ2018 በጋና አስተናጋጅነት በሚካደሄው የቶታል አፍሪካ የሴቶች ዋንጫ በካይሮ ላይ በተደረገ የመጀመርያው ዙር የማጣርያ ጨዋታ የሊብያ አቻውን 8ለ0 አሸንፈው የነበረ ሲሆን አሁን በአጠቃላይ ውጤት 15ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ወደ ቀጠቀዩ ዙር ሉሲዎቹ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials