Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, April 16, 2018

ቤተመንግሥት እራት የበላቹህ ምን አተረፋቹህ?


.
ከሁለት አመታት በፊት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበረው ባራክ ኦባማ ወደኢትዮጵያ በተጓዘበት ወቅት የወያኔ አመራሮች የእራት ግብዣ በማዘጋጀት ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥሪ ሲያስተላልፉ ሐገር ቤት ካሉ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል በወቅቱ በኢ/ር ይልቃል የሚመራው ሰማያዊ ፓርቲ በእራት ግብዣው ላይ መሳተፍ በንፁሃን ሞት ደም ለተዘጋጀው የፌሽታ ፕሮግራም እንዲዘጋጅ አይደለም የምንታገለው በሚል ኦባማ የተገኘበት የእራት ግብዣ ላይ ሳይሳተፍ ቀረ። በወቅቱ ከኢንጂነር ይልቃል ውጭ የተሳተፉ በርካታ ተፎጋጋሪ ፖለቲከኞች የነበሩ ሲሆን ሆኖም ኢንጂነሩ እንደግርማ ሰይፉ መስሏቸው ለኦባማ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ ይገኝ ዘንድ የህወሀት ሰዎች መልእክት ላኩ ቆፍጣናው ኢንጂነር ይልቃል ግን ህዝቤን እየገደሉና እያሰቃዩ ከሚገኙ ጋር እንዴት እራት እበላለው በማለት ግብዣውን ሰርዞታል። በወቅቱ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተግባሩን በማድነቅ ብራቮ ኢ/ር ድሮስ እንዴት በግ ከአራጁ ጋር ይውላል ብለው ነበረ።
በወቅቱ ኢ/ር ይልቃል ህዝቡን መርጦ የእራት ግብዣውን በመሰረዙ የቀሩበት ነገሮች
 አላሙዲን ሰክሮ ከማህደር አሰፋ ጋር ሲተሻሽ ማየት፣
 እድሜ ያላስተማረው ስብሀት ከኮረዳ ጋር ሲደንስ መመልከት፣
 ሀይለማርያም የኦባማን እጅ ለማስታጠብ ሲሯሯጥ አይቶ መታዘብ፣
 ደብረፅዮን በስካር መንፈስ ሆኖ ይልቃል የመጣበትን ጎሳ ሲሳደብ መስማት፣
 ሚሚ ስብሀቱና ሰራዊት ፍቅሬ ከህወሀት ሰዎች የተራረፈውን ለመብላት ሲሯራጡ አይቶ ማዘን፣
 ሬድዋን ሁሴን ውስኪውን ጨብጦ ሲነፋረቅ "ሙስሊም ሆኖ እንዴት አልኮል ይጠጣል" ብሎ ማዘን
 ደመቀ መኮንን ታማኝ የህወሀት አገልጋይ መሆኑን ለማሳየት ሳሞራን አዝሎ ሲጨፍር መመልከት........... እነዚህ ናቸው ኢንጂነር ይልቃል የቀሩበት። እንደይልቃል ላሉ ሀገር ወዳዶች ሀገር ማለት ህዝብ ነው
አሁን ላይ ደግሞ የአዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት ምክንያት በማድረግ በቤተመንግሥት በተዘጋጀ የእራት ግብዣ የተወሰኑ ፖለቲከኞች እና አርቲስቶች ተሳትፈው የነበረ ሲሆን በእራት ግብዣው ላይ በመገኘታቸው ምን እንዳተረፉ እና የእነርሱ እዛ መገኘት በሕዝቡ ነፃነት ትግል ላይ ምን እሴት እንደሚጨምር ቢነግሩን ደስ ይለኛል።
የሰሞኑ የፖለቲከኞቻችን ንግግር እና ተግባርን ለተመለከተ አሁንም ቢሆን ከኢንጂነር ይልቃል፣ ከፕሮፌሰር መረራ እና ከአንዳርጋቸው ፅጌ ጋር ሊነፃፀር የሚችል ፖለቲከኛ የለንም።

No comments:

Post a Comment

wanted officials