Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, April 13, 2018

የዋልድባ መነኮሳትን ጨምሮ የ114 ሰዎች ክስ ተቋረጠ


የዋልድባ መነኮሳትን ጨምሮ የ114 ሰዎች ክስ ተቋረጠ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 03 ቀን 2010 ዓ/ም)
 በሃሰት ወንጀል ተከሰው በስቃይ ላይ የነበሩ የዋልድባ መነኮሳትን ጨምሮ ሌሎች 114 እስረኞች ክስ ተቋርጦ ከእስር እንደሚፈቱ አቃቢ ህግ ለፍርድ ቤት ባቀረበው ማመልከቻ አስታውቋል።
ጥያቄው ለፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የቀረበ ሲሆን፣ ተከሳሾች ከዛሬ ጀምሮ ይፈታሉ።
የዋልድባ መነኮሳቱ በአፋጣኝ እንዲፈቱ ኢትዮጵያውያን በማህበራዊ መገነኛ ብዙሃን ጫና ሲያደርጉ ቆይተዋል። ከሚፈቱት መካከል በቂልንጦ ቃጠሎ የተከሰሱት የህሊና እስረኞች ይካተቱ ወይም አይካተቱ የታወቀ ነገር የለም።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ መምህር ስዩም ተሾመንና አቶ ታዬ ደንደዓን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እስረኞች አሁንም በግፍ እስር ላይ ናቸው።
Image may contain: 2 people, people standing

No comments:

Post a Comment

wanted officials