Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, April 16, 2018

የተሃድሶ መናፍቃንን የተወሰኑ ጥያቄዎች መልስ ቀጥሎ ሰለቀረበ ይማሩበት

ፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ:- የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችንን ወደ ፕሮቴስታንት ለማስለወጥ የሚጥሩ የሚያደርጉ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ስልት ተሃድሶ ፥ክህደታ ቸውም ሃራጥቃ ተብሎ ይጠራል። አስተምህሮአቸው በሙሉ የጴንጤ ነው። የኦርቶዶክስ ተዋህዶን እምነት የሚቀበል ለመምሰል ከሃይማኖት አበውና ከድጓ ከልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን መጻህፍት እየጠቀሱ ይናገራሉ፡ በግእዝ ልሳንም ጥቅሶችን ያቀርባሉ፥፥ ሆኖም ግን የሚጠቅሷቸውን መጻህፍት እንኳን በአግባቡ አይቀበሏቸውም፥፥ እነዚህ ተሃድሶዎች አባላቱ በኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በቂ የመጽሐፍ ቅዱስና የነገረ መለኮት እውቀት የሌላቸው ወይንም ደግሞ በመንፈሳዊ ተቋማቱ ገብተው የንጽጽር ትምህርት ሲሰጣቸው በዚያው ተምታትቶባቸው የሚቀሩ ቲዎሎጂያንም ሊሆኑ ይችላሉ። ስር እስኪሰዱ ድረስ ሰላማዊ ኦርቶዶክስ ይመስላሉ።ቀስ በቀስ ይሄ ቢቀር ምናለበት እያሉ ድብቁ አጀንዳቸውን ይረጫሉ።አስተምህሮአቸው በሙሉ የጴንጤ ፕሮቴስታንታዊ ነው።
የተሃድሶ መናፍቃንን የተወሰኑ ጥያቄዎች መልስ ቀጥሎ ሰለቀረበ ይማሩበት።

1. ክብር ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስን ይለምናል የሚሉ ናቸው እርሱ ግን በስሜ ትለምናላችሁ እንጂ እኔ ስለእናንተ አልለምንም አለን ዮሓ 16:26 

2. እኔና አብ አንድ ነን ብሎ የስላሴን አንድነት ነገረን ዮሐ10:30 ።ክርስቶስ አምላክ እንደሆነ ሮሜ 9:1

3. መንፈስ ቅዱስ ከወልድም ጭምር ይወጣል የሚል የካቶሊክ እምነት ያምናሉ ጌታ ግን መንፈስ ቅዱስን ከአብ የሚወጣ ብሎ አስተማረን ዮሓ 15:26

4. ድህነት በአጭር ጊዜ የሚፈጸም እንጂ በህይወት ጉዞ የሚገኝ ነው ብለው አያምኑም መጻህፍት ግን መዳናችንን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ እንፈጽም ብለው ነገሩን ፊሊ 2:12

5. ድህነት በእምነት ብቻ ይገኛል ብለው የሚያምኑ ናቸው ሐዋርያት ግን እምነትና ስራ ለድህነት ያበቃሉ ብለው ተናገሩን ያእ 2:26

6. ስጋውና ደሙ የጌታ ስጋና ደም ሳይሆን መታሰቢያ ብቻ ነው ብለው ያምናሉ ጌታ ግን ይህ ስጋየ ነው ብሎ ነገረን ማር 14: 12

7. የጌታን ስጋ መቀበል ለድህነት ግድ አይደለም ይላሉ መጽሐፍ ግን ስጋውን ያልበላ ደሙንም ያልጠጣ የዘለአለም ህይወት የለውም አለን ዮሓ 6:54
8. ጥምቀት ለመዳን የግድ አይደለም ለክርስትናችን ማረጋገጫ እንጅ ይላሉ ጌታ ግን ያመነና የተጠመቀ ብቻ ይድናል አለን ማር 16:16
9. ሁሉም ሰው ካህን ነው ብለው ያምናሉ ጌታ ግን ሓዋርያትን ብቻ መርጦ ስልጣን ሰጣቸው ማር 3:15 ማቴ 18:18
10. የአዋጅ ጾምን ይቃወማሉ ሐዋርያት ግን የታወቀ የጾም ወቅት ነበራቸው ጌታም የፈሪሳዊያንን የአዋጅ ጾም ሳይሆን አጿጿማቸውን ነው የነቀፈው ሐዋ 27:9 ዘካ 8:19 ማቴ 6:16
11. ትውፊት አያስፈልጉም ባዮች ናቸው መጽሓፍ ቅዱስ ግን በትውፊት የተገኙ ነገሮችን መዝግቦ ይዞ ይገኛል ሐዋርያትም ትውፊታቸውንና ወጋቸውን እንድንይዝ መከሩን 2ኛ ተሰ 2:15
12. ድንግል ማርያምን ከጌታ ሌላ ልጆች አሏት ይላሉ መጽሓፍ ቅዱስ ግን ማርያም ሌላ ልጆች ነበሯት አይልም /ሙሉ መጽሓፉ/
13. የቅዱሳንን መታሰቢያ ማድረግን ይከለክላሉ/ይነቅፋሉ መጽሓፍ ቅዱስ ግን የጻድቃን መታሰቢያ ለበረከት ነው ይላል    ምሳ 10:7 
14. ቅዱሳን ከሞቱ በኋላ የተረሱ ናቸው ይላሉ መጽሓፍ ቅዱስ ግን የጻድቃን መታሰቢያል ለዘለአለም ይኖራል ይላል       መዝ 112:6
15. ቅዱሳንን ማመስገን ባእድ አምልኮ ነው ይላሉ መጽሓፍ ቅዱስ ግን ጻድቃን ሆይ ደስ ይበላችሁ ለቅኖች ምስጋና ይገባል ይልባቸዋል መዝ 33:1
16. ለቅዱሳን ክብር መስጠት የጸጋ ስግደት መስገድ ሓጥያት ነው ይላሉ ጌታ ግን ለደጉ ካህን ከእግሮችህ በታች ይሰግዱልሃል ይለዋል ራእ 3:9
17. ቅዱሳን ከሞቱ በኋላ አያውቁም ይላሉ መጽሓፍ ግን የሚሞተው የሰው ስጋ እንጅ ነፍስ ዘለአለማዊ እንደሆነች ይነግረናል መክ 12:7
18. ሰው ከሞተ በኋላ መለመን አይችልም ይላሉ ጌታ ግን እንኳን ቅዱሳን ሃጥአን እንኳን እንደሚለምኑ አስተማረን ሉቃ 16:19 25
19. ለሞተ ሰው መጸለይ ትርፉ ድካም ብቻ ነው ይላሉ መጽሓፍ ግን ማንም ስለ ወንድሙ ቢለምን ይማርለታል ይላል 1ኛ ዮሓ 5:16
20. ስእል አያስፈልግም እንዲያውም ጣኦት ነው ይላሉ የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ግን ቅዱሳት ስእላት ነበሩ 1ኛ ነገ 6:29
21. ታቦት አስፈላጊያችን አይደለም ይሉናል ቤተ ክርስቲያን ግን በሰማይ ባለው ቤተ መቅደስ አምሳያ ራሷን እንዳነጸች ማስተዋል አይፈልጉም ራእ 11:19
22. ገድላትና ድርሳናት የሰዎችን ታሪክ ስለሚተርኩ አስፈላጊ አይደሉም ይሉናል:: መጽሓፍ ቅዱስ ግን የቅዱሳንን ገድል ጽፎ እናገኘዋለን:: እግዚአብሔር በቅዱሳኑ በኩል የሚያደርገውን ጸጋም ያስተምረናል:: ሓዋ 5:15 ዕብ 13:7
23. ቃል ኪዳን የሰዎች ፈጠራ ነው ለድህነትም ሆነ ለክርስትና ጥቅም የለውም ይላሉ መጽሓፍ ግን እግዚአብሔር ለቅዱሳን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ለትውልዳቸው እንደሚተርፍ ጽፎ ያሳየናል:: ዘዳ 8:18 መሳ 2:1 1ኛ ነገ 11፡32
24. ተዋህዶ በልሳን ስለማትናገር መንፈስ ቅዱስ የለባትም ይላሉ በመጽሓፍ ቅዱስ ግን ሁሉም ክርስቲያኖች በልሳን ይናገሩ ነበር አይልም:: 1ኛ ቆሮ 14:26 ዛሬ የሚነገረው ልሳንም የመንፈስ ቅዱስ እንዳልሆነ ብዙ ማስረጃዎች
አሉ::*
25. የመስቀሉ ቃል ለማያምኑት ሞኝነት ለኛ ለምንድን ግን የ እግዚአብሄር ሃይል ነው። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:18

                    ወስብሐት ለእግዚአብሄር ልዑል ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር+++                                                                     

አሜን
በአብርሃም  
https://1ethiopia.wordpress.com/2018/04/16/who-is-tehadso/
Image may contain: mountain, outdoor and nature

No comments:

Post a Comment

wanted officials