Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, April 19, 2018

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ያቀረቧቸው አዳዲስ እና ነባር ሚኒስትሮች ሹመት ፀደቀ


ከነበሩበት ሚኒስትር መስሪያ ቤት እንዲሸጋሸጉ ከተደረጉት መካከል አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ - የትራንስፖርት ሚኒስትር፣
ዶ/ር ሂሩት ወልደማርያም - የሰራተኛ እና ማህራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
አቶ ሽፈራው ሽጉጡ - የግብርና እና የእንስሳት ሐብት ሚኒስትር
አቶ ሙቱማ መቃሳ - የሐገር መከላከያ ሚኒስትር
ሆነው ተሹመዋል…
አዳዲስ ከተሾሙት መካከል...
አምባሳደር ተሾመ ቶጋ - የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚንስትር
አቶ ኡመር ሁሴን - በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
ወ/ሮ ኡባ መሀመድ - የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሚንስትር
ዶ/ር አምባቸው መኮንን - የኢንዱስትሪ ሚንስትር
ወ/ሮ ፎዚያ አሚን - የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር
አቶ አህመድ ሺዴ - የመንግስት ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር
አቶ ጃንጥራር አባይ - የከተማ ልማትና ቤቶች ሚንስትር
አቶ መለስ አለም - የማዕድንና ኢነርጂ ሚንስትር
አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ - ጠቅላይ አቃቤ ህግ
ወ/ሮ ያለም ጸጋዬ - የሴቶችና ህጻናት ሚንስትር
አቶ መላኩ አለበል - የንግድ ሚንስትር
ዶ/ር አሚር አማን - የጤና ጥበቃ ሚንስትር...
በተያያዘ መረጃ…
አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ በገዛ ፈቃዳቸው ያቀረቡትን የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፀደቀው፡፡
ለሁለት የስራ ዘመናት ተመርጠው በአፈ ጉባኤነት ሲያገለግሉ የቆዩት አባዱላ ገመዳ የስራ መልቀቂያቸውን ቀድመው ለፖለቲካ ድርጅታቸው ማቅረባቸው ተጠቅሷል፡፡
ኢሕአዴግ የአቶ አባዱላ ገመዳን መልቀቂያ በመቀበሉ ፓርላማው አቶ አባዱላን ከሀላፊነት እንዲያሰናብታቸው የግንባሩ ሊቀ መንበር የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ እንደራሴዎቹን ጠይቀዋል፡፡
ምንም እንኳ ሁለተኛው የስራ ጊዜያቸው ባያልቅም ሕግ በሚፈቅደው መሰረት ከአፈ ጉባዔነታቸው እንዲሰናበቱ የምክር ቤቱን ድጋፍ አግኝተዋል፡፡
አቶ አባዱላ ገመዳን ተክተው አፈ ጉባኤ እንዲሆኑ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ተመርጠዋል፡፡
በስልጣን ርክክቡ ወቅት የቀድሞ አፈ ጉባኤ አባዱላ ሕገመንግስቱንና ሥነ ሥርዓት ማስከበሪያ መዶሻውን ለአፈ ጉባኤ ሙፈሪያት ካሚል አስረክበዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials