Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, April 14, 2018

ግልባል አሊያንስ በቅርቡ ለተፈቱት የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች 160.000 ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታ አበረከተ !

በቅርቡ ለተፈቱት የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች የምስጋና ምሳ ግብዣ ተደረገ ፤ ግልባል አሊያንስ 160.000 ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታ አበረከተ !
--
ሰማያዊ ፓርቲ በቅርብ ከእስር የተፈቱ የፖለቲካ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ፣ጋዜጠኞች ፣የሙስሊም ማህበረሰብ የመፍትኄ አፈላላጊ ኮሜቴ አባላት እንዲሁም ጠበቆቻቸውን ጨምሮ ፤ "ጀግኖቻችን እናመሰግናለን" በሚል መሪ ቃል መጋቢት 16 ቀን 2010 ዓ.ም የምስጋና ምሳ ግብዣ በአዲስ አበባ አካሂዷል ።
--
በዝግጅቱ ላይ በርካታ ተዋቂ እና አንጋፋ ፖለቲኮኞ የተገኙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ፕ/ር መረራ ጉዲና ፣ መምህር በቀለ ገርባ ፣ አንዷለም አራጌ፣ ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ፣ ክንፈምካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ፣ ዮናታን ተስፋዬ፣ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር፣ ናትናኤል መኮንን እና ሌሎች በርካቶች በእለቱ ተገኝቷል ። ከሙስሊም ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ዑስታዝ አቡበክር አህመድ ፣ ሸህ መከተ ሙሄ ፣ ዑስታዝ አህመድ ሙስጠፋ ፣ ሙጂብ አሚኖ ሰኢድ እና ሌሎች የኮሚቴ አባላት የተገኙ ሲሆን፤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ፣ ጦማሪ በፍቃዱ ሀይሉ እና ዘላለም ወርቅአገኘው የፕሮግራሙ ተካፋይ የነበሩ ሲሆን "በመፈንቅለ መንግስት" ተከሰው ለ7 አመት በእስር የቆዩት ጀኔራል ተፈረ ማሞ እና ተመስገን ባየልኝ ተገኝቷል ። በዚሁ ዝግጅት ላይ የህሊና እና የፓለቲካ እስረኞች ጉዳይ በመያዝ የህግ ድጋፍ በመስጠት የሚታወቁት ፤ ጠበቃ አምሃ መኮንን፣ ወንድሙ ኢቢሣ፣ ሽብሩ በለጠ ፣ ገበየሁ ይርዳሁ እና ብርሃኔ ሞገሌ ሰማያዊ ፓርቲ ባዘጋጀው የምስጋና ምሳ ግብዣ ላይ በእንግድነት ተገኝተዋል ።
--
በእለቱ በተካሄደው ዝግጅት እንደተገለጸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው አርቲስት ታማኝ በየን የሚገኝበት ፤በውጪ ሃገር የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ያቋቋሙት ግልባል አሊያንስ /ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት/ የተሰኘው ትብብር በቅርብ ከእስር ለተፈቱ 16 እስረኞች የመጀመሪያ ዙር ለእያንዳንዳቸው አስር ሺህ ብር (10 ሺህ ብር ) በድምሩ አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ ብር (160,000) ስጦታ አበርክቷል ። ስጦታው በተለያየ ችግር ውስጥ የሚገኙ ቅድሚያ የሰጠ እንደሆነ ግልባል አሊያንስ የገለጸ ሲሆን፤ በቀጣይነት የሌሎችም እንደሚቀጥል ተገልጿል ።
--
የእለቱ ፕሮግራም አስመልክቶ ፕ/ር መረራ ጉዲና ፣ጀኔራል ተፈረ ማሞ ፣ ጠበቃ አምሃ መኮንን ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ ፣ኤልያስ ከድር እና ጦማሪ በፈቃዱ ሀይሉ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ የእለቱ ፕሮግራም አስመልክቶ እንዲሁም ቀጣይ የትግል አቅጣጫ በተመለከተ አጭር መልእክት በማስተላለፍ ፤በቅርብ ከእስር ለተፈቱ የምስክር ሰርተፍኬት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል ።
--
(ይድነቃቸው ከበደ)

No comments:

Post a Comment

wanted officials