Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 10, 2018

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ፣ የሃይቲና የኤልሳልቫዶር ሀገራትን በማንቋሸሽ መናገራቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ቀሰቀሰ።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተቃውሞ ገጠማቸው


የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ፣ የሃይቲና የኤልሳልቫዶር ሀገራትን በማንቋሸሽ መናገራቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ቀሰቀሰ።
ትራምፕ ከአፍሪካ የመወሰኛ ምክር ቤት አባላትና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት ሀገራቱን ቆሻሻ ወይንም ውዳቂ ሲሉ መጥራታቸው በሲ ኤን ኤን ከተዘገበ በኋላ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ተቀባብለውታል።
የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
የቀድሞው የሃይቲ ፕሬዝዳንት በአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ታሪክ ያልታየ ድንቁርና ሲሉ ትራምፕን አውግዘዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዲቪ ሎተሪ ፕሮግራም ተጠቃሚዎችን ቁጥር በመቀነስ ሃይቲንና ኤልሳልቫዶርን የመሳሰሉ ሀገራትን ሕገወጥ ስደተኞች ህጋዊ ሆነው በጊዜያዊነት መቆየት የሚችሉበትን ሁኔታ በተመለከተ እቅድ ቀርቦላቸዋል።
እንዲሁም በአሜሪካ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች የሚገቡበትን ሁኔታም በተመለከተ ዕቅድ ሲቀርብላቸው ከሃይቲና ከአፍሪካ ሀገራት ተጨማሪ ሰዎች ምን ያደርጉልናል፣ኖርዌይን ከመሳሰሉ ሀገራት እንጂ በማለት እቅዱን አጣጥለውታል።
የቀረበውን ሃሳብ ከማጣጣላቸውም በላይ የአፍሪካ፣የሰሜንና የማዕከላዊ አሜሪካ ሀገራትን ቆሻሻ ወይንም ውዳቂ ሲሉ መጥራታቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ቀስቅሷል።
ታዋቂው የአሜሪካ ቴሌቪዥን ሲ ኤን ኤን ምንጮችን ጠቅሶ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ትላንት ሀሙስ የተናገሩትን ከዘገበና ከተቸ በኋላ የፕሬዝዳንቱን ድርጊት የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት ጭምር አወግዘዋል።
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ቃል አቀባይ ሩፔርት ኮልቪል “አሳፋሪና አስደንጋጭ” መግለጫ ሲሉ ዶናልድ ትራምፕን አውግዘዋል።
ዘረኛ ሲሉ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት የጠሩት ሩፔርት ኮልቪል ድርጊቱ ከአለም አቀፍ ሰብአዊ እሴቶች ተጻራሪ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
የሃይቲው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ላውረንት ሌሞዝ በአሜሪካ ታሪክ ያልታየ ድንቁርናና ክብረነክ ድርጊት ሲሉ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
ከአሜሪካ ምክርቤት አባላትና ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚደረገው ተቃውሞ እየተጠናከረ በቀጠለበት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቲውተር ገጻቸው ማስተባበያ ጽፈዋል።
እቅዱን በጠንካራ ቃላት የተቃወምኩ ቢሆንም ሀገራቱን ውዳቂ ብዬ አልጠራሁም ሲሉ አስተባብለዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials