Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, January 6, 2018

ፓትርያርኩ፣የተባረረው አስተዳዳሪ ወደሰዓሊተ ምሕረት እንዲመለስ ማዘዛቸው የምእመኑን ቁጣ አብሶታል


ሐራ ዘተዋሕዶ


በተባረረው አስተዳዳሪ፣ የፓትርያርኩ እና የሥራ አስኪያጁ በልዩነት መጠባበቅ ኹኔታውን እያከፋው ነው፤
ምእመናኑን፣ “ዱርዬዎች” የሚሉት ፓትርያርኩ፣የተባረረው አስተዳዳሪ እንዲመለስ ማዘዛቸው ተጠቁሟል፤
ሥራ አስኪያጁ፣ የክፍለ ከተማውን የፖሊስ ኃይል ድጋፍ በደብዳቤ እንዲጠይቅ በማዘዝ ምእመኑን በቆመጥ አስደበደቡ፤
በጽናት የተቋቋመው ምእመኑ፣ በጸሎተ ምሕላ እና በዝማሬ ጥበቃውን አጠናክሮ ውሏል፤የተባረረውን አስተዳዳሪ መመለሱ ይቅርና፣“ዛሬ ጠዋት በካቴድራሉ ውስጥና አካባቢ ታይቷል፤”መባሉ፤የምእመኑን ቁጣ አብሶታል፤ንቃቱንና ተቃውሞውን አጠናክሮታል፤



በጠዋቱ የምእመናኑ የጥበቃ መርሐ ግብር ቅይይር አጋጣሚ፣ ወደ ካቴድራሉ ከገባው የክፍለ ከተማው ፖሊስ ጋራ፣ደወል ቤቱን ቀድሞ ለመቆጣጠርና በነቂስ የወጣው ምእመን እንዳይገባ ለመግታት፣ፍጥጫና ትንቅንቅ ነበር፤ተኩስም ተሰምቷል፤
ምእመኑ፥“ቤተ ክርስቲያናችን እናታችን ናት፤ ከእርሷ የሚበልጥብን የለም፤” ብሎ በአቋሙ በመጽናት ካቴድራሉን በመቆጣጠሩና በማስከበሩ ቀጥሏል፤
†††

የክፍለ ከተማውን ፖሊስ ለማገዝ የተጠራ አድማ በታኝ ፖሊስ፣ እስከ ጊዜ ቅዳሴ በካቴድራሉ ዙሪያ ከበባ ቆይቷል፤
ካህናቱ እና የሀ/ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ከምእመናኑ አልተለዩም፤ ጸሎቱ እና ቅዳሴውም አልታጎለም፤
የምእመናኑ ተወካዮች፣ “ከሀገረ ስብከቱ ጋራ አነጋግሩን፤ መፍትሔ አሰጡን፤” ሲሉ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደርን ጠየቁ፤
ጥያቄውን መነሻ በማድረግ፣ የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ፣ ምእመኑን ወርዶ በማወያየት ችግሩን እንዲፈታ የፍትሕ እና ጸጥታ ቢሮ አሳሰበ፤
ሥራ አስኪያጁ፣ “በቂ የፖሊስ ኃይል ካልተመደበልኝ እኔስ ምን ዋስትና አለኝ፤” ብሎ ቢያንገራግርም፣የሀ/ስብከቱን ልኡካን ይዞ ምእመናኑን ለማነጋገር ተስማማ፤



ነገ ጧት፥የክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚ፣ የሀገረ ስብከቱን ልኡካንና ምእመናኑን በካቴድራሉ ያወያያል፤
ምእመናኑ፣ ከነገው የቋሚ ሲኖዶስ ሳምንታዊ ስብሰባም ትኩረትና ማጽናኛ እንጠብቃለን፤ ቢሉም ፓትርያርኩ “ተዉኝ፤ጣልቃ አትግቡብኝ፤ሥራ አስኪያጁ በሚያቀርብልኝ ሪፖርት ውሳኔ እሰጣለሁ፤”ብለዋል ላነጋገሯቸው ብፁዓን አባቶች፡፡Image may contain: one or more people, sky and outdoor

No comments:

Post a Comment

wanted officials