Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, January 2, 2018

በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች እንደሚፈቱ ተገለጸ





ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች እንደሚፈቱና ‹‹ማዕከላዊ›› በመባል የሚታወቀው የምርመራ ማዕከል እንደሚዘጋ ዛሬ አስታወቁ፡፡ አራቱ የኢሕአዴግ ብሔራዊ ድርጀቶች ሊቃነ መናብርት በጋራ በሰጡት መግለጫ እዚህ ውሳኔ ላይ መደረሱን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫው እንዳስታወቁት፣ በዓቃቤ ሕግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር ላይ የሚገኙና የተፈረደባቸው ፖለቲከኞችም ሆኑ የተለያዩ ግለሰቦች ይፈታሉ፡፡ ይህም የሚደረገው የተሻለ አገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዴሞክራሲ ምኅዳሩን ለማስፋት በማሰብ መሆኑን ገልጸው፣ ታሳሪዎቹ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በይቅርታ እንደሚለቀቁ አረጋግጠዋል፡፡

ማዕከላዊ የሚባለው የምርመራ ተቋም በደርግ ዘመን በእስር ቤትነት እስረኞችን ለማሰቃየት ይውል እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ግን ተዘግቶ ወደ ሙዚየምነት ይቀየራል ብለዋል፡፡

ስለሚፈቱ ፖለቲከኞችና ግለሰቦች ማንነት በዝርዝር ለጊዜው ባይገለጽም የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ጋዜጠኞችና የመሳሰሉት በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

የአራቱ የኢሕአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶች ሊቃነ መናብርት ዝርዝር መግለጫ ምሽት ላይ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል

በጋዜጣዉ ሪፓርተር

No comments:

Post a Comment

wanted officials