Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, January 30, 2018

በመተማ ዮሃንስ በቅርቡ የደረሰውን የቦንብ ጥቃት ተከትሎ የህወሃት ስብሰባ ተካሃደ

18 የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች እና የጦር አዛዦች በተለያዩ አካባቢዎች የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ስለሚከላከሉበት ሁኔታ መተማ ላይ መከሩ !!
የኢሳት አስታማማኝ ምንጮች እንደገለጹት በመተማ ዮሃንስ በቅርቡ የደረሰውን የቦንብ ጥቃት ተከትሎ 10 የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ለ5 ተከታታይ ቀናት ስብሰባ አካሂደዋል።
በሰብሰባው ላይ የተሳተፉት የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች፣ ከኮሎኔልነት በላይ ማዕረግ ያላቸው በሱዳን ድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሰው ጦር አዛዦእ እንዲሁም በጭልጋ፣ አዘዞ፣ ደባርቅና አካባቢዋ የሚንቀሳቀሰው ጦር አዛዦች ናቸው። የስብሰባው ዋና አጀንዳ በተለያዩ አካባቢዎች የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን እንዴት መመከት አለብን የሚል እንደነበር የሚገልጹት ምንጮች፣ ስብሰባው በከፍተኛ ሚስጢር እና በወታደራዊ ጥበቃ የተካሄደ ነው።
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ አካባቢ የተከሰተውን ግጭት ለማብረድና የህዝቡን የትግል ተነሳሽነት ማቅዘቀዝ እንዴት ይቻላል በሚለው ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። የክልሉን ህዝብ ተነሳሽነት ለመቀነስ ትኩረት ሊያስቀይሩ የሚችሉ አቅጣጫዎችን መጠቀም፣ በተለይም ህዝቡ በቅማንት እና በአማራ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ በማድረግ ከሰሜን ወሎ እንቅስቃሴ አይኑን እንዲያነሳ ስራዎችን መስራት ይገባል የሚል ሃሳብ በአማራጭነት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ትናንት ጥር 21 ቀን 2010 ዓም ደግሞ በከተማው ቦንብ ለወረወሩት ተቃዋሚዎች ገንዘብ አቀብለሃል፣ ቦንብ ገዝተህ ድርጊቱን ለፈጸሙት ሰዎች ሰጥተሃል የተባለ ተጠርጣሪ ተይዞ “ የግንቦት7 አባል ነኝ” ብለህ ተናገር ተብሎ ሲደበደብ ውሎአል። ወጣቱ ቦንቡን አለመወርወሩን ተናግሯል። “የወያኔ መንግስት በትጥቅ ትግል ካልሆነ በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንደማይወርድ በማመኔ በትጥቅ ትግል የሚዋጉትን እደግፋለሁ” በማለት በድፍረት ተናግሯል።
የአማራ ክልል በጉዳዩ ላይ ዘገባ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ ነው፣ በተጠርጣሪውና በፖሊሶች መካከል የነበረው ቃለምልልስ ከባድ ነበር የሚሉት ምንጮች፣ የግለሰቡ ጥንካሬ የሚገርም ነበር ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials